No summary available.
ኀዳር 26 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ጌታቸው ምህረቱ Aሰግድ ጋሻው ሒሩት መለሰ Aብዱራሂም Aህመድ Aመልካች፡- ወ/ት Aዜብ ሽፈራው - Aልቀረቡም።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ታየች ንጉሴ - ቀረቡ።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ የጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ነው።
በሥር ፍ/ቤት ተጠሪ ከሣሽ ሲሆኑ Aመልካች ደግሞ 1ኛ ተከሣሽ ነበሩ።
ተጠሪ ባቀረቡት ክስም በወረዳ 21 ቀበል 24 ውስጥ የሚገኘውን ቁጥር 646 የሆነውን ቤት ለAሁኗ Aመልካች የሰጧት ሲሆን ቁጥር 643 Eና 644 የሆኑትን ቤቶች ግን Aመልካች Aጠቃልዬ Eገዛቸዋለሁ በማለት ተረክበው ለሥር 2ኛ Eና 3ኛ ተከሣሾች በማከራየት Eየተጠቀሙ በመሆኑ ቤቶቹን ለቀው Eንዲያስረክቡኝ የቤቶቹን ኪራይም Eንዲከፍሉ በማለት ጠይቀዋል።
የAሁኗ Aመልካችም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና ለፍሬ ጉዳዩም መልስ የሰጡ ሲሆን በመልሣቸው ላይ መጋቢት 2 ቀን 1985 የተደረገው የሽያጭ ውል Eነዚህን ቤቶችንም የሚጠቀልል ነው በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የAመልካችን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ ካደረገ በኋላ በመ/ቁ. 2793/88 ተጠሪ የሽያጩ ውል Eንዲፈርስ ባቀረቡት ክስ ፍ/ቤቱ የቤ/ቁ 643 Eና 644 በተመለከተ የቀረበው ክስ ዳኝነት ያልተከፈለባቸው Eና በሽያጭ ውሉ ያልተካተቱ በመሆኑ በልላ መዝገብ በመክሰስ የመጠየቅ መብታቸው የተጠበቀ ነው በማለትና የሽያጭ ውሉ ግን ላፈርስ Eንደማይገባ በሰጠው ውሣኔ ላይ ቤቶቹ በሽያጩ ውል ላይ Eንዳልተካተቱ ከተረጋገጠ Aመልካች ቤቶቹን Aስረክበው ኪራዩንም Eንዲከፍሉ በማለት ወስኗል። ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የፍ/ከ/ፍ/ቤትም ይህንኑ ውሣኔ Aጽንቶታል።
የAሁኑ የሰበር Aቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ ችሎትም ቀደም ሲል በቀረበው ክስ Aሁን ክርክር የተነሣባቸውን ቤቶች በተመለከተ ተጠሪ የዳኝነት ከፍለው Eንዲጠይቁ በተሰጠው ውሣኔ ትችት ላይ ቤቶቹ በሽያጭ ውሉ Aለመካተታቸው መገለፁን ምክንያት በማድረግ ብቻ Aመልካች ቤቱን Eንዲለቁ ¾¨c’¨< በAግባቡ መሆን Aለመሆኑን ለመመርመር Aቤቱታው ለሰበር ችሎት Eንዲቀርብ በማድረÑ< ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሁፍ Aቅርበዋል። መዝገቡንU Eንደሚከተለው መርምሯል።
ከፍ ሲል Eንደተገለፀው የAሁን ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት ክስ የመሰረቱት Aመልካች ቁጥር 646 የሆነውን ቤት ሲገዙ ክርክር የተነሣባቸውን ቤቶችም Aጠቃለው Eገዛለሁ ብለው የተረከቡ በመሆኑ Eነዚህን ቤቶች Eንዲመልሱላቸው ነው። Aመልካች ደግሞ መጋቢት 2 ቀን 1985 ዓ.ም. የተደረገው የሽያጭ ውል Eነዚህን ቤቶች የሚያጠቃልል መሆኑን በመግለጽ ላለቁ Eንደማይገባ ተከራክረዋል። ተጠሪ የቤ/ቁ 646” የሸጡ መሆኑን Aልካዱም። Eንደውም ይህ የሽያጭ ውል Eንዲፈርስላቸው በመ/ቁ. 2793/88 ክስ Aቅርበው ውሉ ላፈርስ Eንደማይገባ ውሣኔ ያገኘ መሆኑ” u¡`¡\ ሂደት ተገንዝበናል። Aሁን በዚህ መዝገብ የተነሣው ክርክር ይህ የሽያጭ ውል ክርክር የተነሣባቸውን የቤት ቁጥር 643 Eና 644ን ያጠቃልላል Aያጠቃልልም? የሚለው ነው። የሥር ፍ/ቤት Aመልካች ቤቱን ለተጠሪ Eንዲያስረክቡ የወሰነው የሽያጭ ውሉ Eንዲፈርስ ክስ በቀረበበት ጉዳይ ላይ Eነዚህ ሁለት ቤቶች በሽያጩ Aለመካተታቸው ተረጋግጦ ተወስኗል በማለት ነው።
ውሣኔ ማለት ተከራካሪዎቹ ወገኖች ያቀረቡትን ክስና መልስ Eንዲሁም ማስረጃዎቹን መርምሮ ስለተከራካሪዎቹ ወገኖች መብትና ስለክሱ Aወሳሰን ፍ/ቤቱ የሚሰጠው ውሣኔ ለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕጉ ለውሣኔ ከሰጠው ትርጉም መረዳት ይቻላል። በተያዘው ጉዳይ ግን ፍ/ቤቱ በቀድሞ ክስ ተጠሪ ተገቢውን ዳኝነት ከፍለው ÃÖÃl ከማለት በቀር Aሁን ክርክር የተነሳባቸውን ቤቶች በተመለከተ ክሱ”ና መልሱን Eንዲሁም ማስረጃዎቹን መርምሮ ስለተጠሪም ሆነ ስለ Aመልካች መብት የሰጠው ውሣኔ የለም። ግራ ቀኙ ተከራክረው ውሣኔ ባልተሰጠበት ጉዳይ ደግሞ ቤቶቹ በሽያጩ ውል ላይ Aልተካተቱም በሚል በውሣኔ ትችቱ ላይ መÓለፁ ብቻ በጉዳዩ ላይ ውሣኔ መሰጠቱን Aያመለክትም። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት ክርክር ተደርጎ ውሣኔ ያልተሰጠበትን ጉዳይ Eንደተሰጠበት በመቁጠር ለውሣኔው መሰረት ማድረጉ Aግባብ ሆኖ Aላገኘነውም። ፍ/ቤቱም ቀድሞ ውሣኔ ተሰጥቶበታል ወደሚለው መደምደሚያ በመድረሱም ግራ ቀኙ በቤቶቹ ላይ ያላቸውን ክርክርና ማስረጃ በAግባቡ ሣይመረምር ውሣኔ መስጠቱን ተገንዝበናል። Eኛ መዝገቡን Eንደመረመርነው ተጠሪ መጋቢት 2 ቀን 1985 በተደረገ የሽያጭ ውል በወረዳ 21 ቀበል 24 የሚገኘውንና የቤት ቁጥር 646 የሆነውን ቤት መሸጣቸውን ተረድተናል። የሽያጭ ውሉን Eንደተመለከትነውም በከተማ ቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ቁጥር 21/A87AA በስማቸው የተመዘገበውንና በፕላን ቁጥር 96/57 በቦታ ይዞታ 3A8 ካ.ሜ. ላይ በ56 ካ.ሜ. ቦታ ላይ የሰፈረውን ቤት Aዋሳኞቹን በመጥቀስ በብር 62,AAA(ስልሳ ሁለት ሺ) ለAመልካች ሸጠዋል። ይህ በሽያß ውሉ ላይ በተገለፀው የከተማ ቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ላይ ደግሞ የተጠቀሱት ቁጥር 643፣ 644 Eና 646 የሆኑ ቤቶች ናቸው። የሽያጭ ውሉ Eና የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተሩ Aንድ ላይ ተገናዝበው ሲታዩም ተጠሪ ለAመልካች የሸጡት ሦስቱን ቤቶች በሙሉ መሆኑን መረዳት ይቻላል። በተለይ በሽያጭ ውሉ ላይ ተጠሪ የቤ/ቁ 646” ብቻ ለይተው Eንደሸጡ የገለፁት ነገር Aለመኖሩ ሲታይም የሽያጭ ውል በባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተሩ ላይ የተጠቀሱትን ቤቶች በሙሉ የሚያጠቃልል መሆኑን ያመለክታል። በልላ በኩል ተጠሪ Aሁን ክርክር የተነሳባቸውን ቤቶች ለAመልካች ያስረከብኩት ወደፊት ቤቶቹን Aጠቃልዬ Eገዛለሁ ስላሉኝ ነው ያሉ ቢሆንም ይህ ፍሬ ነገር Eውነት ለመሆኑ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ነገር Aላገኘንም።
No topics extracted.
በAጠቃላይ ከላይ Eንደተመለከተው Aመልካች ቤቱን የያዙት መጋቢት 2 ቀን 1985 ዓ.ም. በተደረገው የሽያጭ ውል መሰረት ገዝተው በመሆኑ ቤቱን ለተጠሪ Eንዲያስረክቡ የተሰጠው ውሣኔ ስህተት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 37/94 በሐምል 26 ቀን 1994 ዓ.ም Eና በፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 158AA በግንቦት 23 ቀን 1996 ዓ.ም የተሰጡት ውሣኔ ተሽረዋል።
Aመልካች ቤቶቹን የያዙት ገዝተው በመሆኑ ቤቶቹን ላለቁም ሆነ ኪራዩን ላከፍሉ Aይገባም።
ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ።