No summary available.
መ/ ግንቦት 14 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ብርሃኑ Aመነው መድሕን ኪሮስ ፀጋዬ Aስማማው ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ - ነገረ ፈጅ ቀርቧል።
መ/ሰጪ፡- ወ/ት ደብሪቱ ወልደሃና - ጠበቃዋ ቀርቧል።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገን የቤት ኪራይ ውል የሚመለከት ነው።
ለዚህ የሰበር Aቤቱታ መነሻ የሆነው የAሁን Aመልካች በስር የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረበው Aቤቱታ በቀድሞ ወረዳ 21 ቀበል 01 ክልል ውስጥ የሚገኘውንና የቤት ቁጥር 288/1-5 የሆነውን ቤት ለመኖሪያ Aገልግሎት በወር ብር 22 (ሃያ ሁለት ብር) የኪራይ ዋጋ ለAንድ ዓመት ጊዜ በ1977 ዓ.ም ለመልስ ሰጪ Aከራይቶ የነበረ መሆኑን በመግለጽ መልስ ሰጪ በቤቱ ከAንድ ዓመት በላይ የተገለገለች በመሆኑ የኪራይ ውሉ ላልተወሰነ ጊዜ Eንደተደረገ የሚቆጠር በመሆኑ ውሉ Aመልካች ለመልስ ሰጪ በሰጠው ማስጠንቀቂያ መሰረት ፈርሷል። ስለሆነም መልስ ሰጪ ቤቱን Eንዲያስረክበኝ ይወሰንልኝ ሲል በመጠየቁ ነው።
ጉዳዮን በቅድሚያ ያስተናገደው የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት መልስ ሰጪ በኪራይ ምክንያት የያዘውን መኖሪያ ቤት ለAመልካች ላያስረክብ ይገባል?
ወይስ Aይገባም? የሚል ጭብጥ መሥርቶ የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ ምንም Eንኳን የተደረገው የኪራይ ውል ላልተወሰነ ጊዜ Eንደተደረገ 98 99 የሚቆጠር ቢሆንም Eና የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 2966 ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የኪራይ ውል ማስጠንቀቂያ በመስጠት Eንዲያበቃ ለማድረግ Eንደሚቻል ቢደነግግም ግራ ቀኙ ከዚህ በፊት ለተወሰነ ጊዜ (ለAንድ Aመት) ባደረጉት የኪራይ ውል ላይ ውሉ የሚፈርስበትን (የሚበቃበትን) ሁኔታዎች የዘረዘሩ በመሆኑና ከEነዚህ ዝርዝር ሁኔታዎች ውስጥ መ/ሰጪ Aንዱንም ያላፈረሰች በመሆኑ ወይም ደግሞ በውሉ Eንደተገለፀው ቤቱ ለመንግሥት Aገልግሎት ስለመፈለጉ Eና ምትክ ቤት ለመስጠት የተዘጋጀ ስለመሆኑ Aመልካች ያላስረዳ በመሆኑ Aመልካች ለመልስ ሰጪ ማስጠንቀቂያ ሰጥቼ ውሉን ያቋረጥኩ ስለሆነ ቤቱን ልረከብ ይገባል በማለት ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ Aድርጓል። በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኘው የAሁኑ Aመልካች የይግባኝ Aቤቱታውን ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ጉዳዮን በይግባኝ የተመለከተው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ጉድለት የልለበት ነው በማለት የAመልካችን የይግባኝ Aቤቱታ ሳይቀበለው ቀርቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም የስር ፍ/ቤቶች በውሳኔያቸው ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የፈፀሙ በመሆናቸው Eንዲታረም በሚል ነው።
ይህ የሰበር ችሎትም የስር ፍ/ቤት Aመልካች ከመልስ ሰጪ ጋር ያደረገውን የኪራይ ውል Aመልካች ለመልስ ሰጪ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ብቻ ማቋረጥ Aይችልም፤ ውሉ ላቋረጥ የሚችለው ቤቱ ለመንግሥት ሥራ ሲፈለግ ብቻ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ በAግባቡ መሆን Aለመሆኑን ለማጣራት ሲባል Aቤቱታውን ለሰበር ችሎት በማስቀረብ የግራ ቀኙን የጽሁፍ ክርክር መርምሯል።
በተያዘው ጉዳይ በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የAሁኑ መልስ ሰጪ ለክርክሩ መንስኤ የሆነውን የመኖሪያ ቤት ለAመልካች ላያስረክቡ Aይገባም የሚል መደምደሚያ ላይ ላደርስ የቻለው በዋናነት በግራ ቀኙ መካከል ከዚህ ቀደም የተደረገ የቤት ኪራይ ውል የነበረ በመሆኑና በዚህ ውል ላይ ተከራካሪዎችቹ በመካከላቸው ያደረጉት የኪራይ ውል ቀሪ ላሆን የሚችልባቸውን ምክንያቶች የዘረዘሩ መሆኑንና ከEነዚህ የውል ማፍረሻ ምክንያቶች ውስጥ መልስ ሰጪ Aንዱንም ያላፈረሱ መሆኑን ከግምት በማስገባት ነው። ከዚህም Aልፎ ግራ ቀኙ ባደረጉት ውል መሰረት ቤቱ ለመንግሥት Aገልግሎት የተፈለገ ከሆነ Eንኳን Aመልካች ምትክ ቤት በመስጠት ብቻ መልስ ሰጪን ከቤቱ ላያስለቅቅ Eንደሚችል የተስማሙ በመሆኑ የAመልካች ቤቱን ልረከብ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በሚል ነው።
ይሁን Eንጂ ለተያዘው ጉዳይ Aግባብነት ያለው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2966 ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገን የኪራይ ውል ለማብቃት Aከራዩ ተከራዩን ለማስታወቅ ወይም ተከራዩ Aከራዩን ለማስታወቅ ይችላል በማለት በግልጽ ደንግጓል። በዚህ የሕግ ድንጋጌ መሰረትም በተዋዋዮች መካከል የተደረገው የኪራይ ውል የጊዜ ገደብ ያልተበጀለት በሆነ ጊዜ ከተዋዋዮቹ Aንደኛው ወገን ውሉ Eንዲያበቃ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉ ፍፃሜ Eንዲያገኝ ለማድረግ Eንደሚችሉ መገንዘብ ይቻላል።
ይሁንና የስር ፍ/ቤት ግራ ቀኙ ቀደም ሲል ለተወሰነ ጊዜ ያደረጉትን የኪራይ ውል መሰረት በማድረግ በውሉ የተጠቀሰው የኪራይ ጊዜ ካለቀ በኋላና የውሉ Aይነት ወደ ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የኪራይ ውል ከተቀየረ በኋላ መልስ ሰጪ ቀደም ሲል ለተወሰነ ጊዜ በተደረገው ውል መሰረት ግድታቸውን የፈፀሙ (ያላፈረሱ) በመሆኑ Aመልካች የኪራይ ውሉን ማስጠንቀቂያ በመስጠት በቻ ለማፍረስ (ለማብቃት) Aይችልም። ውሉ ላቋረጥ የሚችልበት ብቸኛ ምክንያት ቤቱ ለመንግሥስት ሥራ ሲፈለግ ነው። ይህም ቢሆን Aመልካች ለመልስ ሰጪ ምትክ ቤት ሰጥቶ ነው ውሉን ለማቋረጥ የሚችለው በመሆኑም Aመልካች ማስታወቂያ ሰጥቼ ውሉን ያቋረጥኩ ስለሆነ ቤቱን ልረከብ ይገባል በሚል ያቀረበው Aቤቱታ ተቀባይነት የልለው ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ የሕጉን መንፈስና ዓላማ ሙሉ በሙሉ ያላገናዘበ በመሆኑ መታረም የሚገባው ሆኖ Aግኝተነዋል።
No topics extracted.
100 101 ጉዳዮን በይግባኝ የተመለከተው የፍ/ከ/ፍ/ቤትም ቢሆን የሥር ፍ/ቤትን ውሳኔ በሚገባ ሳይመረምር Eንዳለ ተቀብሎ ማጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ት E ዛ ዝ