No summary available.
ጥቅምት 15 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ መስፍን Eቁበዮናስ ተሻገር ገ/ስላሴ Aብዱራሂም Aህመድ Aመልካች፡ የIትዮጵያ ንግድ ባንክ Aቶ ሳሙኤል ገዛኸኝ ቀረቡ ተጠሪ፡- 1ኛ. Aቶ ዋለልኝ Aያልው ቀረቡ 2ኛ. ወ/ሮ ለመች ላቀው ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል
የሰበር Aቤቱታው የቀረበው የAማራ ብሕራዊ ክልልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ ታህሳስ 24 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ላታረምልኝ ይገባል በማለት ዝርዝር ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
የAሁን 1ኛ ተጠሪ የፍርድ ባለመብት 2ኛ ተጠሪ ባለEዳ ሆነው በምE/ጐጃ መስተዳደር ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት በAፈፃፀም መ/ቁ. 8291 በሆነው መዝገብ ላይ የAፈፃፀም ክሱ Eየታየ ባለበት ጊዜ የAሁኑ Aመልካች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.418 ን መሰረት በማድረግ ጣልቃ ገብቶ ተከራክሯል።
ጣልቃ ለመግባት ያቀረበውም ምክንያት የፍርድ ባለመብት Eንዲረከብ ትEዛዝ የተሰጠበትን የባለEዳዋን ንብረት Aስቀድሜ ያስከበርኩት ስለሆነ ቤቱን ባለመብቱ Aንዲረከብና ስመ ንብረትነቱም Eንዲዛወርለት የተሰጠው ትEዛዝ ቀሪ Aንዲሆንልን ይታዘዝልን የሚል ነው። በማስረጃነትም በዚሁ ንብረት ላይ የማስከበሪያ ትEዛዝ ጥቅምት 28 ቀን 1995 ዓ.ም ያሰጠበት መሆኑንና ባለEዳ በተባለችው በAሁን 2ኛ ተጠሪ ላይ በዋስትና ግድታ ምክንያት ከሶ ፍርድ ያሰጠበት መሆኑን የሚገልፅ የሰነድ ማስረጃ Aቅርቧል።
በዚሁ Aቤቱታ ላይ መልስ የተሰጠበት መሆኑን የሥር ፍ/ቤት ከገለፀ በኋላ የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ ምንም Eንኳን የAሁን Aመልካች በዚሁ ንብረት ላይ የማስክበሪያ ትEዛዝ ያሰጠበት መሆኑ ቢረጋገጥም ማስከበር ብቻውን የቀዳሚነትን መብት የሚያሰጥ ሆኖ Aላገኘነውም ስለሆነም የቀረበው የAፈፃፀም ክስ ይቋረጥልኝ Aቤቱታ ውድቅ ነው በማለት በይኗል።
በዚህም ብይን የAሁን Aመልካች ቅር ተሰኝቶ የይግባኝ Aቤቱታ ለክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት Aቅርቧል።
ፍ/ቤቱም በጉዳዩ ላይ ግራ ቀኙን Aከራክሮ ታህሳስ 24 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችሎት በግራ ቀኙ መካከል የተነሳው Aከራካሪ ነጥብ ክርክር ባስነሳው ቤት ላይ የቀዳሚነት መብት ያለው ወገን ማን ነው? የሚለው መሆኑን ለይቶ በጭብጥነት ከያዘ በኋላ ምንም Eንኳ የIትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2ኛ ተጠሪ ላይ Aስቀድሞ ክስ ያቀረበ Eና Aስወስኖ የAፈፃፀም ክስ ያቀረበ መሆኑ ቢረጋገጥም 1ኛ ተጠሪ Aቶ ዋለልኝ Aያልው ለ2ኛዋ ተጠሪ በወ/ሮ ለመች ላቀው ብር 80,000.00/ሰማንያ ሺህ/ ብድር ሲሰጡ ይህ የብድር ገንዘብ በተባለው ጊዜ ውስጥ ባይመለስ የክርክሩ መንስኤ የሆነውን ቤት ለማስረከብ የውል ግድታ የገቡ መሆናቸውንና Eንደ ግድታቸው የገንዘብ መክፈያ ጊዜው የብድሩን ገንዘብ መመለስ Aለመቻላቸው ተረጋግጦ በሥር ፍ/ቤት ጥቅምት 10 ቀን 1997 ዓ.ም በዋለው ችሎት ይኸው በ2ኛ ተጠሪ ስም ተመዝግቦ በፍኖተ ሰላም ከተማ ቀበል 02 በቁጥር መ/1/1984 ተመዝግቦ የሚገኘውን ቤት Eንዲረከቡ ተወስኗል። የAሁን Aመልካች የIትዮጵያ ንግድ ባንክ የAፈፃፀም ክስ ያቀረበውም ከዚሁ ንብረቱን ይረከብ የሚለው ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በመሆኑ Eና ንግድ ባንክ በቀጥታ ክሱ ጊዜ ይኸው ንብረት ታግዶ Eንዲቆይ ማስደረጉም የፍርድ ባለመብት በቤቱ ላይ ያገኝውን መብት የሚያሳጣ ሆኖ ባለመገኘቱ የAመልካች ቅሬታ ተቀባይነት 42 43 ያለው Aይደለም። Eንዲሁም Aንድ ንብረት በፍርድ ቤት ተከብሮ የመያዙ Eውነታም ንብረቱ ከመያዙ በፊት ገንዘብ Eንዲከፈላቸው በባለሀብቱ ላይ ያስፈረደ ወገን በቀረበ ጊዜ የተያዘውን ንብረት ለመውሰድ Eንደማይከለክል የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ፍ/ቁ.403 ይደነግጋል። Aመልካች የIትዮጵያ ንግድ ባንክ ቤቱን በመያዣ የያዘው ባለመሆኑም ቀድሞ ክስ ማቅረቡ ብቻውን የ1ኛ ተጠሪን የAቶ ዋለልኝ Aያልውን መብት የሚያስቀር Aይደለም የሚሉትን ምክንያቶች በመንተራስ የሥር ፍ/ቤትን ውሳኔ Aፅንቷል። የAመልካችም የሰበር Aቤቱታ ፍሬ ቃል፡የሥር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ለውሳኔው የሰጠው ምክንያት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.403 የተመለከተውን ድንጋጌ ትክክለኛ ትርጉም የተከተለ Aይደለም።
ከ1ኛ ተጠሪ ይልቅ ክርክር ባስነሳው ንብረት ላይ ቀድመን መብታችንን ያስጠበቅን መሆኑ Eየታወቀ Eና በዚህም የተነሣ በሥነ ሥርAት ህጉ የተሰጠን ዋስትና Eያለ ይህ ታልፎ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን ያሳያል።
ይህም Eንኳ ቢታለፍ የፍርድ ባለመብት Eንደመሆናችን መጠን የባለEዳዋ ንብረት ተሽጦ Eንደየድርሻችን መከፋፈል ሲገባን ለ1ኛ ተጠሪ ብቻ Eንዲሰጥ መደረጉ የህግ ድጋፍ ያለው ባለመሆኑ ይኸው ይታረምልን የሚል ነው።
No topics extracted.
ተጠሪዎችም የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዳኝነት ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን በመግለፅ ውሳኔው ላፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
Eኛም ጉዳዩን መርምረናል። Eንደመረመርነውም የAሁን 1ኛ ተጠሪ የብድር ውልን መሰረት Aድርጎ ክስ ከማቅረቡ Eና ከማስወሰኑ በፊት የAሁን Aመልካች በ2ኛዋ ተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ምክንያት ጥቅምት 28 ቀን 1995 ዓ.ም ይኸው ክርክር ያስነሳው ንብረት በማናቸውም መንገድ ቢሆን ወደ ሦስተኛ ወገን Eንዳይተላለፍ ያሳገደው ለመሆኑ በግራ ቀኙ መካከል የተካደ ፍሬ ነገር Aይደለም። ይህም መሆኑ ከተረጋገጠ በAመልካች በኩል የተፈፀመው ተግባር በ2ኛ ተጠሪ ላይ የገንዘብ ክስ AቅርቤAለሁ፤ Eንደ ክሱ ባስፈርድ ፍርዱ ውጤት ያገኝ ዘንድ የተከሳሽ ንብረት ወደ ሦስተኛ ወገን Eንዳይተላለፍ በማለት ተከብሮ ይቆይልኝ የሚል በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 3044 Eንደተመለከተው ይህ የማሳገድ ተግባር ከፍርድ የመነጨ የመያዣ መብት መሆኑን ያመለክታል። ይኸውም ፍርድ ቤቱ የሰጠው ፍርድ ተፈፃሚነት Eንዲያገኝ ለማረጋገጥ Aንዱ ወገን ለልላው ወገን በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ከሚያሰጠው የማስከበሪያ ትEዛዝ Aንዱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.154 መሰረት ግራ ቀኙ በክርክር ላይ Eያሉ ከፍርድ በፊት በንብረት ላይ የሚሰጠው የማገጃ ትEዛዝ ነው። ከላይ Eንደተመለከተው Aመልካች በዚሁ መሰረት የ2ኛዋ ተጠሪ ንብረት በማናቸውም መንገድ ቢሆን ወደ ሦስተኛ ወገን Eንዳይተላለፍ ተከብሮ Eንዲቆይ ያስደረገ ለመሆኑ የተለየ ሆኖ ካልተገኘ Aመልካች በዚሁ ክርክር ባስነሳው ንብረት ላይ የመያዣ መብት ያገኘ መሆኑን Aረጋጋጭ ነው። Eንደ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ትንተና የመያዣ መብት ሁልጊዜ ከውል ብቻ Eንደሚመነጭ ተደርጎ የተሰጠው ትርጉም ስህተት ነው። በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3041 Eንደተደነገገው መያዣ ከውል ብቻ ሳይሆን በቀጥታ ከሕግ ወይም በፍርድ ላቋቋም ይችላል። በዚህ መሰረት Aመልካች ከፍርድ ቤት ትEዛዝ የመነጨ የመያዣ ውል ያለው መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ ይህ በመያዣ የተያዘውን ንብረት ገንዘብ ጠያቂ ያስያዘው Eንደሆነ ከንብረቱ ዋጋ ላይ የሚጠየቀው ገንዘብ ከልሎች ገንዘብ ጠያቂዎች በፊት ለEርሱ በቀዳሚነት Eንዲከፈለው የመጠየቅ መብት ያለው ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.3059/1/ የተደነገገ በመሆኑ Aመልካች የጠየቀው ዳኝነት ህጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ Eያለ ለጉዳዩ Aግባብነት ያለው ህግ ከሚደነግገው ውጭ በሥር ፍ/ቤት መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈፀሙን ያሳያል።
Aንድ ንብረት በፍርድ ቤት ትEዛዝ ተከብሮ የመያዙ Eውነታ ንብረቱ ከመያዙ በፊት ገንዘብ Eንዲከፈላቸው በንብረቱ ባለሀብት ላይ ያስፈረዱ 44 45 ወገኖች በቀረቡ ጊዜ የተያዘውን ሀብት Ÿመውcድ Eንደማያግዳቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 403 ተደንግጓል በሚል በሥር ፍ/ቤት የተሰጠውን ትንታኔም ተመልክተናል። በመሰረቱ የዚህ ድንጋጌ Aግባብነት ከድንጋጌው ርEስ Eንደምንመለከተው የAንድ የፍርድ ባለEዳ ንብረት በEርሱ ላይ የቀረቡትን ገንዘብ ጠያቂዎች ፍላጐት የሚያሟላ ሆኖ ከተገኝ ይኸው ንብረቱ በEነዚህ ገንዘብ ጠያቂዎች መካከል Eንድት Eንደሚከፋፈል የሚደነግግ Eንጂ Eንደ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት Aባባል Aንደኛው ገንዘብ ጠያቂ ብቻውን ጠቅልሎ Eንዲወስድ የሚያስችል Aይደለም። የድንጋጌውም ተፈፃሚነት የፍርድ ባለEዳው” ንብረት በተራ ባለገንዘቦች መካከል ማከፋፈል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የተወሰነ Eንጂ የቀዳሚ መብትነት የሚመለከት Aይደለም። በዚህ ሁሉ ምክንያት የሥር ፍ/ቤቶች ከፍርድ የመነጨ የመያዣ ውል የመኖሩን Eውነታ ወደ ጐን በመተው ንብረቱን በሚመለከት በንብረቱ ላይ ያስወሰነው 1ኛ ተጠሪ ነው የሚለውን ብቻ መሰረት በማድረግ ለዚሁ 1ኛ ተጠሪ በንብረቱ ላይ የቀዳሚነት መብት Eንዲኖረው በማድረግ የሰጡት ዳኝነት መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ Aግኝተነዋል።