No summary available.
መ/ቁ. 236A9 ታህሣሥ 15ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልዱ መስፍን Eቁበዮናስ ሒሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ Aመልካች፡- የIትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ ዘውዱ Aላ - ቀረቡ ተጠሪ፡- Aቶ Aሰበወርቅ ዘገየ - Aልቀረበም
በሰበር Aቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዳይ የጀመረው በፍ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው።
ተጠሪ ለሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ Aመልካች መ/ቤት የሥራ ውላቸውን ያላግባብ ስላቋረጠባቸው ውዝፍ ደሞዝ የተጠራቀመ የዓመት Eረፍት፣የቦነስ ክፍያ፣ Aበል፣ የEቃ ማጓጓዣ ፣የኤርፖርት ታክስ፣የካሣ ክፍያ የማስጠንቀቂያ ክፍያ Eንዲከፍላቸው ጠይቀዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ከስራ የተሰናበቱት ያለAግባብ በመሆኑ ውዝፍ ደመወዝ፣ የEረፍት ጊዜ በገንዘብ ተለውጦ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ Eና የAገልግሎት ካሣ የ6 ወር ደመወዛቸውን Eንዲከፈላቸው ወስኗል። የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህንኑ ውሣኔ Aጽንቷል።
የAሁኑ የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ሲሆን ይህ ችሎትም የAመት Eረፍትና የAገልግሎት ካሣ Eንዲከፈላቸው የተሰጠውን ውሣኔ ሕጋዊነት ለመመርመር Aቤቱታው ለሰበር ችሎት Eንዲቀርብ Aድርጓል።
ተጠሪም ቀርበው ክርክራቸውን በጽሁፍ Aቅርበዋል።
Aመልካች በሰበር Aቤቱታው ውዝፍ ደሞዝ በተመለከተ ቀደም ሲል ከሰው ተወስኖላቸው የወሰዱ በመሆኑ በድጋሚ ላከፈላቸው Aይገባም፣ 2120 Aመልካች የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት ከፍተኛ Eምነት” የሚጠይቅ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸው በድርጅቱ ላይ ከፍ ያለ ጉዳት ላያደርሱ ስለሚችሉ በፍ/ሕ/ቁ. 2577 መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ላሰናበቱ ችለዋል። ከስራ የተሰናበቱት በጥፋት ስለሆነ ካሣ ላከፈላቸው Aይገባም ብሐል። ተጠሪም የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ በAግባቡ ነው ሲK< ዝርዝር መልስ ሰጥተዋል። ይህ ችሎትም መዝገቡን Eንደሚከተለው መርምሯል።
ተጠሪ ያለAግባብ ከሥራ ተሰናብቻለሁ በማለት ላከፈላቸው የሚገባውን ክፍያ ዘርዝረው ክስ Aቅርበዋል ከመዝገቡ Eንደተረዳነውም Aመልካች የተጠሪን የሥራ ውል ያቋረጠው ጥፋት ፈጽመዋል በሚል ቢሆንም ጥፋት መፈፀማቸውን Eንዳላስረዳ የሥር ፍ/ቤቶች Aረጋግጠዋል ።
ጥፋት መኖር Aለመኖሩ ደግሞ የፍሬ ነገር ክርክር በመሆኑ በዚህ ሰበር ችሎት በድጋሚ የሚታይ Aይሆንም። በመሆኑም የተጠሪ የሥራ ውል ያለበቂ ምክንያት ከተቋረጠ ተጠሪ ላያገኙ የሚገባቸው ክፍያዎች ምንድናቸው የሚለውን መመለከት ተገቢ ነው። በተለይ Aመልካች ቅሬታ ያቀረበባቸው ክፍያዎች የተጠራቀመ ደመወዝ፣ የዓመት Eረፍት፤
የማስጠንቀቂያና የካሣ ክፍያዎችን የሚመለከቱ በመሆናቸው Eነዚህ ክፍያዎች ለተጠሪ ላከፈሉ ይገባል ወይስ Aይገባም የሚለውን ተመልክተናል። ተጠሪ የሥራ መሪ በመሆናቸው የሣቸው ጉዳይ የሚታየው በፍትሐብሕር ሕጉ Eንደመሆኑ የተያዘው ጉዳይ ስለሥራ ውል በፍ/ብ/ሕጉ ከተደነገጉት ድንጋጌዎች Aኳያ ተመርምሯል።
የካሣን ጥያቄ በተመለከተ ከፍ ሲል Eንደተገለፀው Aመልካች የተጠሪን የሥራ ውል ያቋረጠው ተጠሪ ጥፋት ፈጽመው ነው ቢልም ይህንን Eንዳላስረዳ የሥር ፍ/ቤቶች Aረጋግጠዋል በመሆኑም የተጠሪ የሥራ ውል የተቋጠረው ከሕግ ውጪ መሆኑን ተገንዝበናል። Aሰሪው ውሉን ቀሪ ለማድረግ በቂ ምክንያቶች የልለው Eንደሆነ ለሰራተኛው ተገቢ የሆነ ኪሣራ ለመክፍል Eንደሚገደድ በፍ/ሕ/ቁ. 2573 ሥር ተመልክቷል። በመሆኑም Aመልካች ተጠሪ ከሥራ የተሰናበቱት በጥፋት ስለሆነ ካሣ ልከፍል Aልገደድም በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም።
የኪሣራውን ልክ በተመለከተ ግን ለሰራተኛው የሚከፈለው ባለፈው 3 ወር ከተቀበለው ደመወዝ ላበልጥ Eንደማይችል በፍ/ህ/ቁ. 2574(2) ሥር የተመለከተ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች የ6 ወር ደመወዝ በካሣ መልክ Eንዲከፈል መወሰናቸው ተገቢ Aይደለም።
ልላው የማስጠንቀቂያ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን Aሰሪው ውሉን ቀሪ ለማድረግ Aስቀድሞ ማስጠንቀቂያ መስጠት Eንደሚገባው በፍ/ሕ/ቁ.
257A/2/ ሥር ተቀምጧል። የሥራ ውሉ ከAንድ Aመት በላይ ቆይቶ ከሆነ ማስጠንቀቂያው ቢያንስ ከ2 ወር Aስቀድሞ ላሰጠው ይገባል (የፍ/ህ/ቁ.257(2) ይመለከታል) ። Aመልካች ማስጠንቀቂያ ላሰጥ Aይገባም የሚለው ስራው ልዩ ችሎታንና ከፍተኛ Eምነት የሚጠይቅ ነው በማለት የፍ/ሕ/ቁ. 2577 ን መሰረት Aድርጎ ሲሆን የተጠሪ የሥራ Aስኪያጅነት ሥራ ግን በዚህ Aንቀጽ የሚሸፈን ባለመሆኑ የAመልካች ክርክር ተቀባይነት የለውም።
የተጠራቀመ ደሞዝን በተመለከተ Aመልካች በሰበር Aቤቱታው ለተጠሪ በባንክ ሂሣባቸው ደመወዛቸውን ገቢ ሲያደርግ ቆይቶ ደመወዝ ለተጠሪ ላከፈል Eንደማይገባ ሲረዳ ከሂሣባቸው ወጪ Aድርጎ በመውሰዱ Aመልካቹ የወሰደውን ገንዘብ Eንዲመልስ ተጠሪ ክስ Aቅርበው ስላስወሰኑበት በAፈፃፀም ገንዘቡን የተቀበሉ በመሆኑ በድጋሚ ደመወዝ ላከፈላቸው Eንደማይገባ ገልጿል። ይህ ችሎቱም መዝገቡን Eንደመረመረው ተጠሪው Aመልካች ወደ ሂሣባቸው ገቢ Aድርጎ መልሶ የወሰደውን ገንዘብ Eንዲመልስ በልላ መዝገብ ክስ መስርተው Aስወስነውበት ገንዘቡን የተቀበሉ መሆኑን፣ ይህም ገንዘብ የተጠሪ ደመወዝ መሆኑን ለመገንዘብ ችለናል። በመሆኑም Aመልካች የተጠሪን ደመወዝ Eንዲመልስ በልላ መዝገብ ተወስኖበት ከከፈለ በኋላ ተጠሪ በድጋሚ ውዝፍ ደመወዝ K=ŸðL†¨< የሚገባበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
የመጨረሻው ነጥብ የዓመት Eረፍትን የሚመለከት ነው ተጠሪ የሚከራከሩት የዓመት Eረፍት ካልተወሰደ ተጠራቅሞ ሰራተኛው በሚመቸው ጊዜ Eንደሚወስደው ካልወሰደ ግን በገንዘብ ተቀይሮ Eንደሚከፈለው Eና ከ9A ቀናት በላይ Eረፍቱ Aይተላለፍም የሚለው ክርክር የሕግ ድጋፍ Eንደልለው ነው። Aመልካች በበኩሉ በወቅቱ የነበረው የብሕራዊ ባንክ መመሪያ Eረፍት ከ9A ቀናት በላይ ላተላለፍ Eንደማይችል ይገልፃል፣ ያም ቢሆን ተጠሪ Eረፍታቸውን ተጠቅመውበታል፣ Aላቸው ቢባል Eንኳን በፍ/ሕ/ቁ. 2562 (3) መሰረት ከ2A ቀናት በላይ ያለው Eረፍት ተቀባይነት የለውም በማለት ይከራከራል የሥር ፍ/ቤት የAመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረገው የብሕራዊ ባንክ መመሪያ Aልቀረበም፣ ቢቀርብም በፍ/ሕጉ ላይ ገደብ የማያስቀምጥ በመሆኑ ተቀባይነት ላኖረው Aይችልም በሚል ነው። ነገር ግን የፍ/ሕጉ የዓመት Eረፍት ላልተወሰነ ጊዜ Eንደሚተላለፍ ያስቀመጠው ነገር ስለልለ መመሪያው በፍ/ሕጉ ላይ ገደብ Aስቀምጧል ለማለት Aይቻልም። በልላ በኩል ተጠሪ የብሕራዊ ባንክ መመሪያ Eረፍት ከ9A ቀናት በላይ ላተላለፍ Aይችልም በማለት ያስቀመጠው ገደብ የለም በማለት በግልጽ ያቀረቡት የተቃውሞ ክርክር የለም። በፍ/ሕጉ ላይ ያልተመለከቱ ነገሮች” ደግሞ ¾መ/ቤቱ Aስተዳደር መወሰኑ ሕገ - ወጥ ነው ለማለት Aያeችልም። በልላ በኩል ግን Aመልካች ተጠሪ Eረፍታቸውን በሙሉ ተጠቅመዋል ይባል Eንጂ የሥር ፍ/ቤት የተጠሪን ማህደር Aስቀረቦ ተጠሪ ያልወሰዱት Eረፍት መኖሩን ስላረጋገጠ በዚህ በኩል የቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም በመሆኑም ተጠሪ የተጠራቀመ የ9A ቀን ብቻ ላሰጣቸው ሲገባ የሥር ፍ/ቤት 522 ቀናት Eረፍት Eንዲያገኙ መወሰኑ ስህተት ነው።
ው ሣ ኔ 1/ የፍ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 1759/87 ሐምል 3A ቀን 1993 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 4624 ታህሣሥ 7 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሻሽሐል።
2/ ለተጠሪ የተጠራቀመ ደመወዝ Eንዲከፈል የተሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
3/ Aመልካች ለተጠሪ የ3 ወር ደመወዝ ካሣ ክፍያ Eንዲከፍላቸው ተወስኗል፡ 4/ Aመልካች ለተጠሪ የ2 ወር ደመወዝ የማስጠንቀቂያ ክፍያ ይክፈላቸው።
5/ Aመልካች ለተጠሪ የ9A ቀን የዓመት Eረፍት በገንዘብ ቀይሮ ይክፈላቸው።
6/ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ።