No summary available.
ሚያዝያ 14 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ሬቫ Iንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር - ጠበቃ ንጉሴ ገዛኸኝ ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
Aከራካሪው ጉዳይ በAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ Aዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት የሚታይን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የAሁኖቹ ተጠሪዎች ከሣሾች ነበሩ። በAመልካች ላይ ክስ የመሰረቱትም በAናጺነት ሥራ ተሰማርተን Aንድንሰራ በውል ተቀጥረን ስንሰራ የቆየን ቢሆንም፤ ሥራው ሳያልቅ ከሕግ ውጪ የሥራ ውላችን ተቋርጦብናል። ስለዚህ ወደ ስራችን Eንድንመለስ፤ የማንመለስ ከሆነም ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት ተገቢው ክፍያ ተከፍሎን Eንሰናበት ዘንድ ይወሰንልን በማለት ነው። Aመልካች ደግሞ ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪዎች የተቀጠሩት ጊዜያዊነት ላለው ሥራ Aገልግሎት Eንዲሰጡ ነው። በዚህ መሰረት ተመድበው ቢሰሩም ደመወዝ የሚከፈላቸው በቀን Eየታሰበ ነው። በመጨረሻም ስራው ስላለቀ በAዋጁ Aንቀጽ 24/1/ መሰረት ተሰናብተዋል። በመሆኑም የሥራ ውላችን ሕገወጥ በሆነ መንገድ ተቋርጦAል የሚሉበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት መከራከሩን ከመዝገቡ ተመልክተናል። ክሱን ያስተናገደው ፍ/ቤት የግራ ቀኝ ወገኖችን ክርክር ከሰማ በኋላ፣ ተጠሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ Eንደተቀጠሩ ማረጋገጡን ገልጾ፣ በልላ በኩል ግን ስንብቱ የተከናወነው በAዋጅ Aንቀጽ 3A/1/ መሰረት ነው የሚል ምክንያት በመስጠት Aመልካች የዓመት Eረፍት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ Eና ክፍያ በመዘግየቱ ላከፈል የሚገባው ነው ያለውን ደመወዝ ለተጠሪዎች Eንዲከፍል ወስኖAል። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሣኔው ጉድለት የለበትም ብሎAል። የሰበር Aቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
ይህ ሰበር ችሎትም Aመልካች መጋቢት 7 ቀን 1999 ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰም…ል።
በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ቀርበው ክርክራቸውን ያሰሙት በ5ኛ፣ በ6ኛ Eና በ1Aኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተጠሪዎች ብቻ ሲሆኑ፣ ልሎቹ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ስላልቀረቡ ክርክሩ Eነሱ በልሉበት ተሰምቶAል። Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲታይ የተወሰነው ተጠሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ናቸው የመባሉን Aግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
በመዝገቡ ከቀረበው ክርክር መገንዘብ Eንደቻልነው Aመልካች በኮንስትራክሽን ሥራ ዘርፍ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን፣ ተጠሪዎችን ቀጥሮ 381 382 ያሰራው የተወሰነ የግንባታ ሥራ ማለትም ሃያ /2A/ ቤቶችን ሲሰራ በነበረበት ወቅት ነው። የተቀጠሩበት ስራም የAናጺነት ስራ ነው። ቤቶች ሲገነቡ ከሚያስፈልጉት ሥራዎች Aንዱ የAናጺነት ስራ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም፤
ይህ ስራ Eስከ መጨረሻው ይዘልቃል ወይም ያስፈልጋል ማለት ግን Aይደለም። በEርግጥ Aመልካች በኮንስትራክሽን የሥራ ዘርፍ የተሰማራ የንግድ ድርጅት Eንደመሆኑ የኮንስትራክሽን ስራዎች Eስካሉ ድረስ በዚሁ የሚቀጥል ቋሚ ድርጅት መሆኑ የሚያከራክር Aይደለም። ድርጅቱ ቋሚ ነው ከተባለ ደግሞ Aብረውት የሚዘልቁ ቋሚ ሰራተኞች ማለትም በተወሰነ ሰዓት ሥራ ገብተው በተወሰነ ሰዓት የሚወጡ /መደበኛ የሥራ ሰዓት ያላቸው/ በየወሩም በፔይሮል ደመወዝ የሚከፈላቸው Eንደሚኖሩት ይታወቃል። ድርጅቱ Aንድ የተወሰነ የግንባታ ስራ በሚሰራበት ጊዜ በተጨማሪነት የሚቀጥራቸው ሰራተኞች ግን ግንኙነታቸው ከተቀጠሩበት የተወሰነ የግንባታ ስራ ጋር በመሆኑ በቋሚነት ከተቀጠሩት የድርጅቱ ሰራተኞች በተለየ ሁኔታ መታየት Eንዳለባቸውም ላያከራክር የሚችል /የሚገባ/ Aይደለም።
ወደያዝነው ጉዳይ ስንመለስ ተጠሪዎች የተቀጠሩት ሃያ ቤቶች በሚሰሩበት ወቅት የAናጺነት ሥራ Eንዲሰሩ በመሆኑ ቅጥራቸው በAዋጁ Aንቀጽ 1A/1/ሀ/ Eንደተመለከተው ለተወሰነ ሥራ ነው። ይህም ከሥራው ባሕርይ Aንፃር ግልጽ ስለሆነ Aመልካች የተቀጠሩት ለተወሰነ ሥራ መሆኑን Aላስረዳም የሚባልበት የሕግ ምክንያት የለም። ክሱን የሰማው የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በውሣኔው ላይ Eንዳመለከተው የቤቶቹ ስራ ተገባዶ የነበረ ሲሆን፣ ተጠሪዎች ከሥራው Eንዲሰናበቱ የተደረጉትም ያኔ ነው። ከላይ Eንዳመለከትነው የAናጺነት ስራ የራሱ ባሕይር ያለው በመሆኑ ቤቶቹ ፍጹም ተጠናቀው ለመኖሪያነት ብቁ Eስከሆኑ ድረስ የሚዘልቅ Aይደለም። በመሆኑም የቤቶቹ ስራ ተገባዶ ነበር Eስከተባለ ድረስ ተጠሪዎች የተቀጠሩበት የAናጺነት ስራ Aልተጠናቀቀም ወይም ቀጣይነት ነበረው ወደሚለው ÉUÇT@ መድረስ የሚቻልበት ምክንያት የለም። የስር ፍ/ቤቶች ለውሣኔያቸው መሰረት ያደረጉት የAዋÌ Aንቀጽ 3A/1/ም መታየት ያለበት ከላይ በዝርዝር ከተገለጸው የAመልካች የስራ ባሕርይ Aንፃር ነው። በዚህ መሰረት ሲታይም የቤቶቹ ግንባታ Eያለቀ ሲሄድ ለሚቀረው ስራ Aስፈላጊ የሆኑት ሰራተኞች ብቻ ቀርተው ባለቀው ስራ ላይ ሲሰሩ የነበሩት ይሰናበታሉ /ይቀነሳሉ/ የሚል ትርጉም ነው የሚኖረው። ተጠሪዎች የተሰናበቱት የተቀጠሩበት የAናጺነት ሥራ በመጠናቀቁ በመሆኑም ለክርክሩ Aወሳሰን ተገቢነት ያለው የAዋጁ Aንቀጽ 24/1/ ነው። በመጨረሻም የሥራ ውሉ በመቋረጡ ምክንያት የሚከፈሉ ክፍያዎች ካሉም መታየት ያለባቸው ከዚሁ Aንፃር ነው። ሲጠቃለል ተጠሪዎች የተቀጠሩት ላልተወሰነ ጊዜ ነው Eንደዚሁም ለክርክሩ Aወሳሰን ተገቢነት ያለው ድንጋጌ የAዋጁ Aንቀጽ 3A/1/ ነው በማለት የስር ፍ/ቤቶች የደረሱበት መደምደሚያ የሕግ መሰረት ያለው ሆኖ Aላገኘነውም። ከዚህ የተነሣም Aቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
522A6 የካቲት 28 ቀን 1999 ዓ.ም. በሰጠው ትEዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮAል።
በAመልካች Eና በተጠሪዎች መካከል የነበረው የሥራ ውል የተቋረጠው በAዋጁ Aንቀጽ 24/1/ Eንደተመለከተው በሕግ በተደነገገው መሰረት ነው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ።
መዝገቡ ይመለስ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ