No summary available.
ጥር 27 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ Aብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ዎተር Aክሽን - ጠበቃ ተስፋዬ ብርሃኔ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ይልማ Aሰፋ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው ተጠሪ ከAመልካች ጋር የነበረውን የሥራ ውል ያቋረጠው ከሕግ ውጭ ስለሆነ ወደ ሥራው ላመለስ ይገባል በማለት የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት Aመልካች ቅሬታ በማቅረቡ ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ ተጠሪ በAመልካች ላይ በAላባ ቁላቶ መ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ በድርጅቱ ውስጥ ሕገወጥ ድርጊቶችን በመቃወሜ ከጥር 15 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ ተከሣሽ ከሥራና ከደመወዝ ያገደኝ ስለሆነ ወደ ሥራ Eንድመለስና ከታገድኩበት ጊዜ Aንስቶ ያለው ደመወዜ Eንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቋል።
የከሣሽ ክስና ማስረጃ ለተከሣሽ ደርሶ በሰጠው መልስ ከሥራና ከደመወዝ ከሣሽን ማገዱን Aምኖ ይህም ላሆን የቻለው ከሣሽ Aስቀድሞ ሲሰራበት ከነበረው þሮጀክት ወደ ልላ þሮጀክት ተዛውሮ Eንዲሰራ ተወስኖ ወደተዛወረበት þሮጀክት በመሄድ ሥራ ለመጀመር ፈቃደኛ ባለመሆኑ Eገዳው ትክክል ስለሆነ ወደ ሥራ ለመመለስም ሆነ ውዝፍ ደመወዝ ይከፈለኝ በማለት ያቀረበው ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
369 370 የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክሩን መርምሮ የተከሣሽ ድርጅት Aንድን ሰራተኛ Aስፈላጊ በሆነ ጊዜ ከAንድ የሥራ ቦታ ወደ ልላ የሥራ ቦታ Aዛውሮ ማሰራት Eንደሚችል በድርጅቱ የAስተዳደር ማኑዋል ላይ በግልጽ የተመለከተ ስለሆነ በዚሁ መሰረት ከሣሽ ወደተዛወረበት ቦታ በመሄድ ሥራ መጀመር ሲገባው Aለመሄዱ Aግባብነት የለውም ካለ በኋላ ከሣሽ ከተዛወረበት ጊዜ Aንስቶ ለAምስት የሥራ ቀናት በሥራ ላይ ባይገኝ ያለማስጠንቀቂያ በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 27(1)(ለ) መሰረት ተከሣሽ የሥራ ውሉን ማቋረጥ ቢችልም የሥራ ውሉ መቋረጡን በመግለጽ ለከሣሽ ያስታወቀው በሕጉ ላይ የተቀመጠው የ5 ቀን ጊዜ ሣይደርስ ስለሆነ የሥራ ውሉ የተቋረጠው ከሕግ ውጭ ነው ብሎ ከሣሽ ወደሥራው ተመልሶ Aዲስ በተመደበበት ቦታ ሄዶ Eንዲሰራ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የAላባ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የቀረበው Aቤቱታ ከሥራ ማገድን የሚመለከት ሆኖ ሣለ የወረዳው ፍ/ቤት በዚሁ ነጥብ ላይ ተመስርቶ ውሣኔ መስጠት ሲገባው የሥራ ውል መቋረጥን Aስመልክቶ ክርክር ሣይደረግበት ውሣኔ መስጠቱ በAግባቡ Aይደለም በማለት የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሯል።
በመቀጠልም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በበኩሉ Aከራክሮ Aመልካች Aዲስ ወደተመደበበት ቦታ በመሄድ ከጥር 8 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ Eንዲገኝ ከተገለፀለት በኋላ ከሥራ መሰናበቱን የሚገልጽ ደብዳቤ የደረሰው ደግሞ ከጥር 5 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ ስለሆነ ከጥር 8 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ በተመደበበት ሥራ ላይ ስላለመገኘቱ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ Aስቀድሞ የተደረገው የሥራ ስንብት ሕገወጥ ነው በማለት የከፍተኛውን ፍ/ቤት ውሣኔ በመሻር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትን ውሣኔ Aጽንቷል።
ይህ ሰበር ችሎትም Aመልካች ያቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ ተጠሪ ባለበት ተጣርቶ ላወሰን Eንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባቸው የጉዳዩ ጭብጦች Aመልካች ተጠሪን ከሥራ Aግዷል ወይንስ Aሰናብቷል? Aሰናብቷል የሚባል ቢሆን ስንብቱ ሕጋዊ ነው ወይንስ Aይደለም የሚሉት በመሆ“†¨< Eነዚህን ጭብጦች በመያዝ Aቤቱታው Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተም ተጠሪ በAመልካች ላይ ክስ የመሰረተው ያለAግባብ ከሥራና ከደመወዝ ያገደኝ ስለሆነ ወደሥራዬ Eንድመለስና ውዝፍ ደመወዝም Eንዲከፈለኝ èc”M˜ በማለት ነው።
Aመልካችም ተጠሪን ከሥራና ከደመወዝ ማገዱን ሣይክድ ተጠሪ ከሥራ ተሰናብቷል ባልተባለበት ሁኔታ ወደ ሥራ የመመለc<ም ሆነ የክፍያ ጥያቄው ያለAግባብ ስለሆነ ተቀባይነት ላኖረው Aይገባም በማለት ተከራክሯል።
ይሁንና Aመልካች ለተጠሪ በፃፈው ደብዳቤ ከሥራና ከደመወዝ መታገዱን Eስካስታወቀ ድረስ የሥራ ውሉ መቋረጡንና የሥራ ስንብት መደረጉን የሚያስገነዝብ ከመሆኑም በላይ በA/ቁ/377/96 Aንቀጽ 27/4/ ላይ የሰራተኛው የሥራ ውል Eንዲቋረጥ ከመደረጉ በፊት ሰራተኛውን ከሥራ Aግዶ ለማቆየት ስለሚቻልበት ሁኔታ በኀብረት ስምምነት ላወስን Eንደሚችል የተመለከተ ስለሆነ በዚህ መልኩም የተደረገ የኀብረት ስምምነት ስለመኖሩ ያልተረጋገጠ በመሆኑ Aመልካች በተጠሪ ላይ የፈፀመው የሥራ Eገዳ ሣይሆን የሥራ ስንብት መሆኑ ይህ ችሎት ተገንዝቧል።
No topics extracted.
ተጠሪ ከሥራ መሰናበቱ ከተረጋገጠ ስንብቱ ሕጋዊ ነው? ወይንስ Aይደለም? የሚለው 2ኛው ጭብጥ ሲታይ Aመልካች ለተጠሪ በፃፈው ደብዳቤ ከጥር 8 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ Aዲስ ወደተዛወረበት ቦታ በመሄድ ሥራ መጀመር Eንደሚገባው Aስታውቆት ወደዚሁ ቦታ ሄዶ ሥራውን ያልጀመረ ከመሆኑም በላይ ከጥር 8 ቀን 1998 ዓ.ም በፊትም ቀድሞ ሲሰራበት በነበረው መ/ቤት ከጥር 5 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ Eንዳልተገኘና በAጠቃላይም ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ያለበቂ ምክንያት በሥራ ገበታው Aለመገኘቱ የተረጋገጠ ስለሆነ ይህ ሁኔታ በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 27(2)(ለ) መሰረት በAሰሪው Aነሣሽነት የሥራ ውልን ለማቋረጥ የሚያበቃ 371 372 Eንደመሆኑ መጠን በዚሁ መሰረትም Aመልካች የሥራ ውሉን ባቋረጠበት ሁኔታ የበታች ፍ/ቤቶች ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት ተጠሪው ወደሥራ Eንዲመለስ በማለት የሰጡት ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የAላባ ቁላቱ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. A1A73 በመጋቢት 29 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ Eንደዚሁም የደቡብ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ.ቁ. 15679 በየካቲት 27 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
Aመልካች ተጠሪን ከሥራ ያሰናበተው ከሕግ ውጭ ስላልሆነ ተጠሪ ወደ ሥራ ለመመለስ ያቀረበው Aቤቱታ ተቀባይነት የለውም።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።