No summary available.
ግንቦት 19 ቀን 2AAAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ታፈሰ ይርጋ መድሕን ኪሮስ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- ዋልያ Aገር Aቋራጭ Aውቶቡስ ድርጅት - ምንተስኖት ተፈሪ /ነገረ ፈጅ/ ቀረበ።
ተጠሪ፡- ብርሃኔ Aላማ ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ ሰበር Aቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ በAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ Aዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት የሚታይ የስራ ክርክርን የሚመለከት ነው።
ክርክሩ ሲጀመር ከሣሽ የነበረው የAሁኑ ተጠሪ ነው። Eሱም ለAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ባቀረበው ክስ የAዋጁን Aንቀጽ 29 በሚቃረን መልኩ በሰራተኛ ቅነሳ ሰበብ የሥራ ውል ተቋርጦብኛል Eና ወደ ስራዬ Eንድመለስ ይወሰንልኝ የሚል ነው። Aመልካችም በበኩሉ ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪ ከስራው የተሰናበተው ድርጅቱ በመክሰሩ የተነሣ ሰራተኞችን መቀነስ Aስፈላጊ /ግድታም/ ሆኖ በመገኘቱ ነው። ተጠሪ ድርጅቱን ለማዳን /Eንዳይዘጋ ለማድረግ/ ሲባል በተደረገው የመዋቅር ለውጥ የሚመጥነው የስራ መደብ Aልተገኘም። ቅነሳው የተካሄደው ሕጉን ተከትሎ የድርጅቱ ሰራተኛ ማኀበርም በተሳተፈበት ሁኔታ ነው በማለት ተከራክሯል። ክሱ የቀረበለት የAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርዱም ክርክሩን ከመረመረ በኋላ ቅነሳው ሕጉን የተከተለ ነው በማለት የተጠሪን ክስ ውድቅ AድርጎAል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ውሣኔውን በመቃወም ለAማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ በማለቱ ክርክሩ በድጋሚ ተሰምቶAል። በመጨረሻም ፍ/ቤቱ የቦርዱን ውሣኔ በመሻር ተጠሪ ወደ ስራው Eንዲመለስ ወስኖAል። የሰበር Aቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
ይህ የሰበር ችሎትም Aመልካች ጥር 2A ቀን 2AAA ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን Aስቀርቦ ክርክሩን ሰምቶAል። Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲታይ የተወሰነው የጠ/ፍ/ቤቱ የቦርዱን ውሣኔ የሻረበትን Aግባብ ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
Eንደምንመለከተው በዚህ ጉዳይ Aከራካሪ ሆኖ የቀረበው ተጠሪን ከስራ ውጪ ያደረገው የሰራተኛ ቅነሳ ሕጉን ተከትሎ የተደረገ ነው ወይስ Aይደለም? የሚለው ነው። በAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ከተደረገው ክርክር Eና ቦርዱ ከሰጠው ውሣኔ Eንዳየነው Aመልካች ድርጅት ከ75% በላይ ኪሣራ የደረሰበት መሆኑ ተረጋግጦAል። ድርጅቱ በመክሰሩም የነበረው Aማራጭ መፍረስ ቢሆንም፣ Aፍርሶ ከመሄድ ይልቅ ልላ Aማራጭ ፈልጎ ሕልውናውን ማቆየት ይሻላል በሚል ሰፊ ጥረትና ጥናት ከተካሄደ በኋላ Aዲስ የስራ መዋቅር በማዘጋጀት ሰራተኞቹ ባላቸው የትምህርት ዝግጅት Eና የስራ ልምድ መሰረት ምደባ መደረጉንም ቦርዱ AረጋግጦAል። በመጨረሻም የድርጅቱ የሰራተኛ ማኀበር በተሳተፈበት የሰራተኛ ቅነሳ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ በAዲሱ የሥራ መዋቅር ለመመደብ የትምህርት ዝግጅቱ የሚፈቅድለት ሆኖ ባለመገኘቱ Eንዲቀ’ስ መደረጉን በቦርዱ ውሣኔ LÃ ቁልጭ ብሎ መቀመጡን በበኩላችንም ለመገንዘብ ችለናል። ይህ Eንግዲህ በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠውን ሁኔታ በግልጽ የሚያሳይ ሲሆን ለጉዳዩ ቀጥተኛ Aግባብነት ካለው የAዋጁ Aንቀጽ 29/3/ ጋርም የሚስማማ ነው። ይህ ድንጋጌ በግልጽ የሚያመለክተው በAዋጁ Aንቀጽ 28/1/ መሰረት የሰራተኞች ቅነሳ በሚደረግበት ጊዜ Aሰሪው ከሰራተኞች ማኀበር ወይም ተወካይ ጋር በመመካከር የስራ ችሎታ ያላቸውንና ከፍተኛ የምርት ውጤት Ád¿ ሰራተኞችን በሥራቸው ላይ Eንዲቆዩ ቅድሚያ መስጠት Eንደሚገባ¨< ነው።
367 368 በያዝነው ጉዳይ Eንደምናየው የሰራተኞች ቅነሳ የተደረገው በድንጋጌው የተመለከተውን ስርዓት ተከትሎ ነው። የጠ/ፍ/ቤቱ ከዚህ በተቃራኒ ስለመፈጸሙ በራሱ በኩል ያረጋገጠው የለም። Aመልካች ተጠሪን በሚመጥነው የሥራ መደብ ላመድበው ይገባል ወደሚለው ድምዳሜ የደረሰውም ምንም የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር ምክንያት ሳይኖረው ነው። ከዚህ የተነሣም Aቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
Aቤቱታ የቀረበበት የAማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 13933 ጥር 1 ቀን 2AAA ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮAል።
Aመልካች ተጠሪን የቀነሰው በሕጉ መሰረት ነው ብለናል። ሰለዚህም ወደስራው ይመለስ የሚባልበት የሕግ ምክንያት የለም ብለን ወስነናል።
No topics extracted.
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ። መዝገቡ ይመለስ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ
ጥር 27 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ Aብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ዎተር Aክሽን - ጠበቃ ተስፋዬ ብርሃኔ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ይልማ Aሰፋ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው ተጠሪ ከAመልካች ጋር የነበረውን የሥራ ውል ያቋረጠው ከሕግ ውጭ ስለሆነ ወደ ሥራው ላመለስ ይገባል በማለት የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት Aመልካች ቅሬታ በማቅረቡ ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ ተጠሪ በAመልካች ላይ በAላባ ቁላቶ መ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ በድርጅቱ ውስጥ ሕገወጥ ድርጊቶችን በመቃወሜ ከጥር 15 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ ተከሣሽ ከሥራና ከደመወዝ ያገደኝ ስለሆነ ወደ ሥራ Eንድመለስና ከታገድኩበት ጊዜ Aንስቶ ያለው ደመወዜ Eንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቋል።
የከሣሽ ክስና ማስረጃ ለተከሣሽ ደርሶ በሰጠው መልስ ከሥራና ከደመወዝ ከሣሽን ማገዱን Aምኖ ይህም ላሆን የቻለው ከሣሽ Aስቀድሞ ሲሰራበት ከነበረው þሮጀክት ወደ ልላ þሮጀክት ተዛውሮ Eንዲሰራ ተወስኖ ወደተዛወረበት þሮጀክት በመሄድ ሥራ ለመጀመር ፈቃደኛ ባለመሆኑ Eገዳው ትክክል ስለሆነ ወደ ሥራ ለመመለስም ሆነ ውዝፍ ደመወዝ ይከፈለኝ በማለት ያቀረበው ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
369 370 የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክሩን መርምሮ የተከሣሽ ድርጅት Aንድን ሰራተኛ Aስፈላጊ በሆነ ጊዜ ከAንድ የሥራ ቦታ ወደ ልላ የሥራ ቦታ Aዛውሮ ማሰራት Eንደሚችል በድርጅቱ የAስተዳደር ማኑዋል ላይ በግልጽ የተመለከተ ስለሆነ በዚሁ መሰረት ከሣሽ ወደተዛወረበት ቦታ በመሄድ ሥራ መጀመር ሲገባው Aለመሄዱ Aግባብነት የለውም ካለ በኋላ ከሣሽ ከተዛወረበት ጊዜ Aንስቶ ለAምስት የሥራ ቀናት በሥራ ላይ ባይገኝ ያለማስጠንቀቂያ በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 27(1)(ለ) መሰረት ተከሣሽ የሥራ ውሉን ማቋረጥ ቢችልም የሥራ ውሉ መቋረጡን በመግለጽ ለከሣሽ ያስታወቀው በሕጉ ላይ የተቀመጠው የ5 ቀን ጊዜ ሣይደርስ ስለሆነ የሥራ ውሉ የተቋረጠው ከሕግ ውጭ ነው ብሎ ከሣሽ ወደሥራው ተመልሶ Aዲስ በተመደበበት ቦታ ሄዶ Eንዲሰራ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የAላባ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የቀረበው Aቤቱታ ከሥራ ማገድን የሚመለከት ሆኖ ሣለ የወረዳው ፍ/ቤት በዚሁ ነጥብ ላይ ተመስርቶ ውሣኔ መስጠት ሲገባው የሥራ ውል መቋረጥን Aስመልክቶ ክርክር ሣይደረግበት ውሣኔ መስጠቱ በAግባቡ Aይደለም በማለት የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሯል።
በመቀጠልም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በበኩሉ Aከራክሮ Aመልካች Aዲስ ወደተመደበበት ቦታ በመሄድ ከጥር 8 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ Eንዲገኝ ከተገለፀለት በኋላ ከሥራ መሰናበቱን የሚገልጽ ደብዳቤ የደረሰው ደግሞ ከጥር 5 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ ስለሆነ ከጥር 8 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ በተመደበበት ሥራ ላይ ስላለመገኘቱ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ Aስቀድሞ የተደረገው የሥራ ስንብት ሕገወጥ ነው በማለት የከፍተኛውን ፍ/ቤት ውሣኔ በመሻር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትን ውሣኔ Aጽንቷል።
ይህ ሰበር ችሎትም Aመልካች ያቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ ተጠሪ ባለበት ተጣርቶ ላወሰን Eንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባቸው የጉዳዩ ጭብጦች Aመልካች ተጠሪን ከሥራ Aግዷል ወይንስ Aሰናብቷል? Aሰናብቷል የሚባል ቢሆን ስንብቱ ሕጋዊ ነው ወይንስ Aይደለም የሚሉት በመሆ“†¨< Eነዚህን ጭብጦች በመያዝ Aቤቱታው Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተም ተጠሪ በAመልካች ላይ ክስ የመሰረተው ያለAግባብ ከሥራና ከደመወዝ ያገደኝ ስለሆነ ወደሥራዬ Eንድመለስና ውዝፍ ደመወዝም Eንዲከፈለኝ èc”M˜ በማለት ነው።
Aመልካችም ተጠሪን ከሥራና ከደመወዝ ማገዱን ሣይክድ ተጠሪ ከሥራ ተሰናብቷል ባልተባለበት ሁኔታ ወደ ሥራ የመመለc<ም ሆነ የክፍያ ጥያቄው ያለAግባብ ስለሆነ ተቀባይነት ላኖረው Aይገባም በማለት ተከራክሯል።
ይሁንና Aመልካች ለተጠሪ በፃፈው ደብዳቤ ከሥራና ከደመወዝ መታገዱን Eስካስታወቀ ድረስ የሥራ ውሉ መቋረጡንና የሥራ ስንብት መደረጉን የሚያስገነዝብ ከመሆኑም በላይ በA/ቁ/377/96 Aንቀጽ 27/4/ ላይ የሰራተኛው የሥራ ውል Eንዲቋረጥ ከመደረጉ በፊት ሰራተኛውን ከሥራ Aግዶ ለማቆየት ስለሚቻልበት ሁኔታ በኀብረት ስምምነት ላወስን Eንደሚችል የተመለከተ ስለሆነ በዚህ መልኩም የተደረገ የኀብረት ስምምነት ስለመኖሩ ያልተረጋገጠ በመሆኑ Aመልካች በተጠሪ ላይ የፈፀመው የሥራ Eገዳ ሣይሆን የሥራ ስንብት መሆኑ ይህ ችሎት ተገንዝቧል።
ተጠሪ ከሥራ መሰናበቱ ከተረጋገጠ ስንብቱ ሕጋዊ ነው? ወይንስ Aይደለም? የሚለው 2ኛው ጭብጥ ሲታይ Aመልካች ለተጠሪ በፃፈው ደብዳቤ ከጥር 8 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ Aዲስ ወደተዛወረበት ቦታ በመሄድ ሥራ መጀመር Eንደሚገባው Aስታውቆት ወደዚሁ ቦታ ሄዶ ሥራውን ያልጀመረ ከመሆኑም በላይ ከጥር 8 ቀን 1998 ዓ.ም በፊትም ቀድሞ ሲሰራበት በነበረው መ/ቤት ከጥር 5 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ Eንዳልተገኘና በAጠቃላይም ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ያለበቂ ምክንያት በሥራ ገበታው Aለመገኘቱ የተረጋገጠ ስለሆነ ይህ ሁኔታ በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 27(2)(ለ) መሰረት በAሰሪው Aነሣሽነት የሥራ ውልን ለማቋረጥ የሚያበቃ 371 372 Eንደመሆኑ መጠን በዚሁ መሰረትም Aመልካች የሥራ ውሉን ባቋረጠበት ሁኔታ የበታች ፍ/ቤቶች ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት ተጠሪው ወደሥራ Eንዲመለስ በማለት የሰጡት ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የAላባ ቁላቱ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. A1A73 በመጋቢት 29 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ Eንደዚሁም የደቡብ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ.ቁ. 15679 በየካቲት 27 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
Aመልካች ተጠሪን ከሥራ ያሰናበተው ከሕግ ውጭ ስላልሆነ ተጠሪ ወደ ሥራ ለመመለስ ያቀረበው Aቤቱታ ተቀባይነት የለውም።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።