No summary available.
ግንቦት 28 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ተገኔ ጌታነህ ታፈሰ ይርጋ መድህን ኪሮስ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች ፡- የIትዮጵያ ንግድ ባንክ ነ/ፈጅ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- Eነ Aቶ Aለማየሁ ወልድ /10 ሰዎች/ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ክርክሩ የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን Aመጣጡን በተመለከተ ደግሞ የAሁን ተጠሪዎች መስከረም 9 ቀን 1998 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ በብራል የምግብ ዘይት ፋብሪካ በዘበኝነት ተቀጥረን ስናገለግል ቆይተናል። የፋብሪካው ባለቤት ከIትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር የወሰደውን ገንዘብ ላከፍል ባለመቻሉ ፋብሪካው ለባንኩ ተላልፏል። ድርጅቱ ሚያዝያ 12 ቀን 1997 ዓ.ም በሕገወጥ መንገድ ከሥራ Aሰናብቶናል። ስለሆነም የሥራ ስንብት፣ የማስጠንቀቂያ፣ ከሰኔ 1995 ዓ.ም Eስከ ሚያዝያ 12 ቀን 1997 ያለው ያልተከፈለ ደመወዛቸው፣ የካሣ ክፍያዎችና የመጓጓዣ Aበል Eንደዚሁም የዓመት Eረፍት ቀኖችን በገንዘብ ተለውጦ Eንዲከፈለን የምስክር ወረቀትም Eንዲሰጠን በማለት በፋብሪካውና በIትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ክስ መስርተዋል።
1ኛ ተከሳሽ የሆነው ፋብሪካ ባለቤት በሰጡት መልስ የድርጅቱ ንብረትነት ለIትዮጵያ ንግድ ባንክ ተላልፏል። የከሳሾችንና የልሎች ሰራተኞችን ክፍያ በተመለከተ ባንኩ ተጠይቆ Aያገባችሁም ብሎናል። ከሣሾቹ Eኔን የሚጠይቁበት ምክንያት ባለመኖሩ ከክሱ ልሰናበት ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የIትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ በሰጠው መልስ የፋብሪካው ባለቤት ፋብሪካውን መያዣ በማድረግ ገንዘብ ተበድረው Aልመለሱም። በብድር የተወሰደውን ገንዘብ ለማስመለስ ሲባል ፋብሪካውን በጨረታ ለማሸጥ ተሞክሮ የሚገዛው Aልተገኘም። ፋብሪካው ገዢ ስላጣም ባንኩ ተረክቦታል። የተረከበው ግን የፋብሪካ ሥራውን ለማስቀጠል ሳይሆን ሸጦ ገንዘቡን ገቢ ለማስደረግ ነው። ፋብሪካውን ሲረከብም ባንኩ ሰራተኞችን የሚመለከት ግድታ ጨምሮ Aይደለም። ከሰራተኞቹ ጋርም ባንኩ ያደረው የሥራ ውል የለም። በመሆኑም ክሱ ስለማይመለከተው ባንኩ ከክሱ በነፃ ላሰናበት ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ፋብሪካው የIትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረከበው በመሆኑ ራሱን የቻለ የህግ ሰውነት የለውም። የድርጅቱ ባለቤት የሆነው የIትዮጵያ ንግድ ባንክ 2ኛ ተከሳሽ የተደረገ በመሆኑ 1ኛ ተከሳሽ ተደርጐ ክስ የቀረበበት ፋብሪካ ከክሱ በነፃ Eንዲሰናበት በማለት ወስኗል።
በልላ በኩል ደግሞ 2ኛ ተከሳሽ የሆነው ባንክ 1ኛ ተከሳሽ ከሆነው የፋብሪካው ባለቤት የወሰደው ቁሳቁስ ሳይሆን ድርጅት ነው። ከሣሾች ከሥራ የተሰናበቱት ፋብሪካው ወደ የIትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተላለፈ በኋላ በመሆኑና የAሰሪና ሰራተኛ Aዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 16 የድርጅት ባለቤትነት መተላለፍ በሥራ ውሉ ላይ ለውጥ Eንደማይኖረው የሚደነግግ በመሆኑ 2ኛ ተከሳሽ የሆነው ባንክ ከሣሾችን በሚመለከት የAሰሪ ግድታዎች ሁሉ ይኖሩታል። በመሆኑም ባንኩ ተከሳሽ የተደረገው በAግባቡ ነው። የከሳሾችን ክፍያ ጥያቄዎች በሚመለከት ጥያቄዎቹን ያቀረቡት ሚያዝያ 12 ቀን 1997 ዓ.ም በሕገ ወጥ መንገድ ከሥራ ተሰናብተናል የተለያዩ ክፍያዎችንም Aልተከፈለንም በሚል ነው። 2ኛ ተከሳሽ የሆነው ባንኩ የሥራ ውሉን መቋረጥ ያመነ ቢሆንም የሥራ ውሉ የተቋረጠው በሕጋዊ መንገድ ስለመሆኑ ያቀረበው ክርክርም ይሁን ማስረጃ የለም በመሆኑም ስንብቱ ሕገ ወጥ በመሆኑ ባንኩ ለከሣሾች በክሱ የተጠቀሰው ደመወዛቸውን፣ የሥራ ስንብትና የካሣ ክፍያ 355 356 Eንደዚሁ የዓመት Eረፍት ሁለት ዓመት ያላለፈውን ብቻ በገንዘብ በመለወጥ Eንዲከፍል የምስክር ወረቀትም Eንዲሰጣቸው በማለት ወስኗል።
የፍ/ከ/ፍ/ቤት የቀረበለትን ይግባኝ መሰረት በማድረግ ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ በሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት Aላገኘሁበትም በማለት ውሣኔውን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት Aጽንቶታል።
የIትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰበር Aቤቱታውን ያቀረበውም የሥር ፍ/ቤቶች በሰጡዋቸው ውሣኔዎች ቅር በመሰኘት ሲሆን ቅሬታዎችም የሥር ፍ/ቤቶች 1ኛ ተከሳሽ የሆነውን ድርጅት ከክሱ በነፃ ያሰናበተው በAግባቡ Aይደለም። ድርጅቱ በንግድ ሕግ ቁጥር 969 መሰረት መክሰሩ Aልተረጋገጠም። ድርጅቱ ወደ ባንኩ በተላለፈበት በሚያዝያ 12 ቀን1997 ዓ.ም ሰራተኞቹ በሥራ ላይ Aልነበሩም። ድርጅቱ ባንኩን የተረከበው ለEዳ መክፈያነት Eንጂ ሥራውን ለማካሄድ ባለመሆኑ በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 16 ሥር ያለውን ግድታ የምረከብበት ምክንያት የለም። ድርጅቱን በAዋጅ ቁጥር 97/90 Eና 98/90 የተረከብኩት Eንደማንኛውም የዋስትና የተያዘ ንብረት በመሸጥ ገንዘቤን ገቢ ለማስደረግ ነው። ከተጠሪዎች ጋር ያደረግኩት የሥራ ውል ባለመኖሩና ፋብሪካውንም የተረከብኩት ሥራውን ለማስቀጠል ባለመሆኑ የፋብሪካው ባለቤት የነበረውን ግድታ የምሸከምበት በክሱ የተጠቀሰውን ክፍያ Eንድከፍል የምገደድበት ምክንያት የለም። የሥር ፍ/ቤቶች ድርጅቱን የተረከብከው የሰራተኞችንም የተለያዩ ክፍያዎች ለመክፈል ጭምር ነው በማለት በክሱ የተጠቀሱትን ክፍያዎች Eንድከፍል በመወሰናቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽመዋል። በመሆኑም ውሣኔው ላሻርልኝ ይገባል የሚል ነው።
ተጠሪዎቹ ደግሞ በሰጡት መልስ የተሰናበትነው Aመልካች ድርጅቱን ከተረከበ በኋላ ነው። Aዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 16 የAንድ ድርጅት የባለቤትነት መብት በየትኛውም መልኩ ሲተላለፍ የሥራውን ውል የመለወጥ ወይም የማሻሻል ይዘት Eንደማይኖረው ይደነግጋል። የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ Aንዳችም የሕግ ስህተት የልለበት በመሆኑ Aመልካች ያቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም። በመሆኑም ውሣኔው ላፀናልን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
Aመልካች ያቀረበው የመልስ መልስ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል።
በመቀጠልም ግራ ቀኙ የቃል ክርክር Aድርገው ክርክራቸውን Aስመዝግበዋል።
በበኩላችን ደግሞ Aመልካች በብድር የተወሰደው ገንዘብ ባለመከፈሉ ምክንያት ለብድሩ በዋስትና ተይዞ የነበረውን ድርጅት በጨረታ የሚገዛው ካጣ በኋላ በመነሻ ዋጋው ስላስቀረው ሰራተኞችን የሚመለከት ግድታም ከድርጅቱ ጋር ይተላለፍለታል ወይስ Aይተላለፍለትም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን Eንደመረመርነውም Aመልካች ባንክ የምግብ ዘይት ፋብሪካውን በጨረታ መነሻ ዋጋው የተረከበው ጨረታ ወጥቶ የሚገዛው በማጣቱ ምክንያት Eንጂ ፋብሪካው የማምረት ሥራውን ለማስቀጠል Eንዳልሆነ ይታወቃል። ፋብሪካው ባንኩ ከተረከበው ጊዜ ጀምሮ Eስካሁን Eየሰራ Aይደለም። የባንኩ ሥራ ገንዘብንና ገንዘብ ነክ ነገሮችን ማስቀመጥ፣ ማዘዋወር፣ ማበደርና መሰብሰብ Eንጂ ልላ የንግድ ሥራ ማከናወን ባለመሆኑም ባንኩ ለወደፊቱም ቢሆን ፋብሪካውን ይሰራበታል ተብሎ Aይገመትም ። ያለው Eድል በAነስተኛ ዋጋም ቢሆን ፋብሪካውን Eንዳለ uመሸጥ ወይም ማሽኖቹንና ህንፃውን ነቃቅሎና ከፋፍሎ በመሸጥ ገንዘቡን ገቢ የሚያደርግበትን Aማራጭ መውሰድ Eንጂ ፋብሪካውን Eንደ Aንድ የሥራ ዘርፍ በመውሰድ ዘይት ማምረት Aይሆንም።
የIትዮጵያ ንግድ ባንክ የዘይት ፋብሪካውን የተረከበው በAዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት በዋስትና የተያዘውን ንብረት ተረክቦ በመሸጥ ገንዘቡን ገቢ ለማድረግ Eንጂ በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 16 መሰረት ፋብሪካው የሕግ ሰውነት ኖሮት የባለቤትነት መብቱን ወደራሱ በማስተላለፍ ዘይት የማምረት ሥራውን ለማስቀጠልና በዚሁ ሥራ ትርፍ ለማግኝት Aይደለም። ይህ ፋብሪካ ባንኩ ከተረከበው ጊዜ ጀምሮ በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 2/2/ በትርጉም Eንደተቀመጠው የድርጅቱን ተግባር ለማከናወን Aላማ ይዞ በAንድ Aመራር 357 358 የሚመራ ተቋም ሆኖ የተቋቋመ Aይደለም። በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 16 ሥር የAንድ ድርጅት የባለቤትነት መብት ወደልላ Sተላለፍ የሥራ ውሉን የማሻሻል ውጤት Aይኖ[¨< ተብሎ የተደነገገው የባለቤትነት መብቱን ወደራሱ ያዛወረው Aካል ድርጅቱን የወሰደው ሥራውን Eንዳለ ለማስቀጠል ነው ተብሎ ስለሚገመት ነው። ባንኩ ግን ፋብሪካውን የተረከበው Eንዳለ ላሰራበት ሳይሆን በማናቸውም ሁኔታ ሸጦ ገንዘቡን ገቢ ለማድረግ ነው። ይህ በመሆኑም ነው ባንኩ ድርጅቱን ከመረከቡ በፊት Aብዛኛው የፋብሪካው ሰራተኛ Aስቀድሞ በፋብሪካው ባለቤት የተሰናበተው ። ተጠሪዎች ልላው ሰራተኛ ከተሰናበተ በኋላ በጥበቃ ሥራ ላይ የቆዩትም የፋብሪካው ባለቤት ፋብሪካውን ለባንኩ Eስኪያስረክቡ ብቻ Eንጂ ፋብሪካው ሥራውን ”Ç=kØM“ ተጠሪዎችም በተቀጠሩበት ሥራ Eንዲቀጥሉ ለማድረግ Aልነበረም።
በመሆኑም ተጠሪዎቹ የድርጅቱ የጥበቃ ሰራተኞች ሆነው የተቀጠሩት ባንኩ ፋብሪካውን ከመረከቡ በፊት በፋብሪካው ባለቤት በመሆኑና በጥበቃ ሥራም የቀጠሉት ባንኩ ድርጅቱን Eስከሚረከብ ከፋብሪካው ባለቤት ጋር በመስማማት Eንጂ ከባንኩ ጋር ባደረጉት ውል ባለመሆኑ፣ Eንደዚሁም ባንኩ ድርጅቱን የተረከበው ከላይ በዝርዝር Eንደተገለፀው ሸጦ ገንዘቡን ገቢ ለማድረግ Eንጂ የዘይት ማምረት ሥራውን ለማስቀጠል ስላልሆነ ተጠሪዎች በክሱ ¾ÖkdD†¨<“ ድርጅቱ ለባንኩ ከመተላለፉ በፊት መከፈል የነበረባቸው ክፍያዎች የፋብሪካውን ባለቤት የሚመለከቱ Eንጂ Aመልካችን የሚመለከቱ ግድታዎች ባለመሆናቸው የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሥራ ክርክር ችሎት 1ኛ ተከሳሽ የሆነው” የፋብሪካውን ባለቤት ከክሱ በማስወጣት የIትዮጵያ ንግድ ባንክ በክሱ የተጠቀሱትን ክፍያዎች Eንዲከፍል በማለት መወሰኑ በAግባቡ ያለመሆኑን ተገንዝበናል።
ስለዚህ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሥራ ክርክር ችሎት Eና የፍ/ከ/ፍ/ቤት የሥራ ክርክር ችሎት የሰጡት ውሣኔ የAዋጅ ቁጥር 97/90 Eና 377/96 ልዩነቶችን ያላገናዘበ በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትና መታረም የሚገባው ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
ይፃፍ።
የIትዮጵያ ንግድ ባንክ የምግብ ዘይት ፋብሪካውን በጨረታው መነሻ ዋጋ የወሰደው ፋብሪካውን በመሸጥ ገንዘቡን ገቢ ለማድረግ Eንጂ የፋብሪካውን ሥራ ለማስቀጠል ባለመሆኑ በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 16 መሰረት ቀደም ብሎ ፋብሪካው ከተጠሪዎች ጋር ያደረገውን የሥራ ውል የሚያስቀጥልበትና ሰራተኞችን የሚመለከት ግድታ የሚሸከምበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት ወስነናል። ይፃፍ።
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለን መዝገቡን ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል።
የሆነው የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት መዝገብ ወደመጣበት ከሸኚ ደብዳቤ ጋር ይመለስ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ዙ/ዘ 359 360
No topics extracted.