No summary available.
ግንቦት 14 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ መድህን ኪሮስ ዓላ መሐመድ Aልማው ወል Aመልካች፡- Aቶ ግርማ ሽፈራው ጠበቃ ባዩ ደስታ ቀረቡ ተጠሪ፡- የክርስቲያን በጎ Aድራጎት ልማት ድርጅት ጠበቃ Aድማሱ መዓዛ ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቄራ ምድብ የሥራ ክርክር ችሎት በመዝገብ ሚያዚያ 29 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፍድራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 1A ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት Aመልካች የሰበር Aቤቱታ በማቅረቡ ነው። የክርክሩ ፍሬ ጉዳይ Aመልካች ተጠሪው .7A /Aስራ ዘጠኝ ሺ Aንድ መቶ ሰባ ሶስት ብር ከሰባ ሣንቲም/ þሮቬደንት ፈንድ Eንዲከፍላቸው ያቀረቡት ክስ ተጠሪው በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 162 መሰረት በይርጋ ይታገዳል በማለት ያቀረበውን ክርክር በመቀበል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክርክሩ በይርጋ ቀሪ ይሆናል ብሎ ውሣኔ በመስጠቱና የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ይህንኑ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሣኔ በማጽደቁ ነው።
Aመልካች þሮቪደንት ፈንድ ከሰራተኛው ደመወዝ በየወሩ በፐርሰንት Eየተቀነሰ በAሰሪው የሚቀመጥና የሚጠራቀም ሰራተኛው ከሥራ ሲሰናበት የሚጠቀምበት በጡረታ መልክ የሚከማች የሰራተኛው ገንዘብ ነው። ይህ ገንዘብ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 28AA Eና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 28A2 የተቀመጠ በመሆኑ በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 1756 ንUስ Aንቀጽ 3 መሰረት ባለመብቱ ሲጠይቅ በተጠየቀ ጊዜ የሚከፈል eKJ’ በይርጋ ይቋረጣል መባሉ ተገቢ Aይደለም በማለት Aመልክቷል። ተጠሪው በበኩሉ፤ þሮቪደንት ፈንድ በመዝገበ ቃላት ውስጥ ያለውን ትርጓሜ በመጥቀስና þሮቪደንት ፈንድ የሰራተኛ ጥቅማጥቅም በሚባሉት ውስጥ፤ የሚመደብ Eንደሆነ በመግለጽ Eንደዚሁም þሮቪደንት ፈንድ ሰራተኛው 5% Aሰሪው ደግሞ 15% በማዋጣት በባንክ በተከፈተ ሒሣብ Eንደሚቀመጥ በመግለጽ፣በይርጋ ይታገዳል መባሉ ተገቢ ነው በማለት ተከራክሯል። የክርክሩ ፍሬ ጉዳይና በሰበር በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን Eኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን Eንደመረመርነው ከሥራ ቅጥር ውል የሚመነጩ የደመወዝ “ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ጥያቄዎች በAንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ያለባቸው መሆኑን በAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ AዋÏ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 162 ተደንግጓል። Eነዚህ ክፍያዎች በመሰረታዊነት ሰራተኛው ስራ ላይ Eያለ የይገባኛል ጥያቄ ላያቀርብ Eና የመብት ጥያቄ ላነሣ የሚችልባቸው ናቸው።
ይህ ከሆነ የAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 162 የተደነገገው የይርጋ የጊዜ ገደብ፣ በባህሪው Ÿደመዝ ጭማሪ፣ ከትርፍ ሰዓት Eና በዓል ቀን ክፍያ የተለየ ነው። የገንዘቡም ምንጭ ቢሆን ሙሉ በሙሉ Aሰሪው Aይደለም።
ከተጠራቀመው ገንዘብ ውስጥ፣ከሰራተኛው በየወሩ Aምስት ፐርሰንት Eየተቆረጠ ተቀምጧል። ዓላማውም ሰራተኛው ከሥራ ሲሰናበቱ ወይም ሥራውን በራሣቸው ፈቃድ ሲለቁ፤ Eነሡና ቤተሰቦቻቸው ችግር ላይ Eንዳይወድቁ፣ ለመደጎምና የማህበራዊ ደህንነትና ዋስትና ክፍያ ተጠቃሚ Eንዲሆኑ ለማድረግ ነው። ከዚህ Aንፃር ስንመለከተው þሮቪደንት ፈንድ ይከፈለኝ የሚለው ጥያቄ በAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ Aዋጅ 377/1996 Aንቀጽ 162 መሰረት በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው።
351 352 በልላ በኩል Aመልካች ገንዘቡ የAደራ ገንዘብ በመሆኑ በተጠየቀ በማናቸውም ጊዜ ላከፈል ይገባዋል በማለት ያቀረበው ክርክር þሮቪደንት ፈንድ ባለባቸው መሥሪያ ቤቶች የሚተዳደሩ ሰራተኞች በሕይወት ባሉበት በማናቸውም ጊዜ ወይም የEነርሱ ወራሾች፤ መብቱ” ላጠÃቁ ከሚችሉበት ቀን Aንስቶ፣ ከሃያ ዓመት በኋላ፣ ከሃምሣ ዓመት በኋላ Eና ከዚያም በላይ Eየመጡ፣ ጥያቄ Eንዲያቀርቡ Eድል የሚሰጥ ነው። ይኸ ደግሞ የሚበረታታና የሕግ ጥበቃ የሚሰጠው Aይደለም። ስለሆነም þሮቪደንት ፈንድ፤ በስንት ዓመት ውስጥ መጠየቅ Eንደሚገባው የሚደነግግ ግልጽ የሕግ ድንጋጌ ባይኖርም በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1677 Aንቀጽ 1 Eና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1845 መሰረት መታየት ያለበት ነው። ከዚህ Aንፃር þሮቪደንት ፈንድ ባለመብቱ በAስር ዓመት ውስጥ ካልጠየቀ በይርጋ ቀሪ ይሆናል። Aመልካች ከተጠሪ ጋር ያለው የሥራ ውል የተቋረጠው ጥቅምት 29 ቀን 1992 ዓ.ም በመሆኑ፣ þሮቪደንት ፈንዱን ተጠሪ Eንዲከፍለው ያቀረበው ጥያቄ Aስር ዓመት Aልሞላውም። በመሆኑም የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት Eና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የAመልካች ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aለበት በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የAመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቄራ ምድብ ችሎት Aመልካችና ተጠሪ የሚያደርጉትን ልሎች የፍሬ ጉዳይና የሕግ ክርክር በመስማትና ማስረጃቸውን በማመዛዘን የመሰለውን ውሣኔ ይሰጥ ዘንድ ጉዳዩን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 341 መሰረት መልሰን ልከንለታል። ይፃፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ራሣቸው ይቻሉ።
ይህ ፍርድ በፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ግንቦት 14 ቀን 2AAA ዓ.ም በሙሉ ድምጽ ተሰጠ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት 353 354
No topics extracted.