No summary available.
ሚያዝያ 30 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- Aብዱልቃድር መሐመድ Aሰግድ ጋሻው ደስታ ገብሩ ሒሩት መለሰ መስፍን Eቁበዮናስ Aመልካች፡- የIትዮጵያ Aገር Aቋራጭ ከፍተኛ Aውቶብስ የግል ባለንብረቶች ማኀ/ Aልቀረበም።
ተጠሪ፡- Aቶ Aያልው ይርጉ - ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን ክርክሩ ሲጀምር የAሁኑ ተጠሪ ከሣሽ Aመልካቹ ደግሞ ተከሣሽ ነበሩ። የAሁን ተጠሪ ጥቅምት 2 ቀን 1999 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት ክስ፣ በAመልካቹ መ/ቤት በገንዘብ ያዥነት ተቀጥሬ ስሰራ ገንዘብ በማጉደል መ/ቤቱ የስራ መደቤን ቀይሮ የቀረብኝን 13,819.36 (Aሥራ ሦስት ሺህ ስምንት መቶ Aሥራ ዘጠኝ ከሰላሳ ስድስት) ብር Eየሰራሁ በመክፈል ተስማምቼ ሣለ ድርጅቱ Eድሜዬ ከ6A ዓመት በላይ በመድረሱ ከስራ ተሰናብሀል በማለት በስምምነታችን መሰረት Eዳዬን ከፍዬ ሣልጨርስ ከስራዬ ያሰናበተኝ በመሆኑ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎኝ ወደ ስራዬ Eንድመለስ ይወሰንልኝ ሲሉ ዳኝነት በመጠየቃቸው ነው።
Aመልካቹ ቀርበው መልስ የሰጡ ሲሆን ይዘቱም፡- ከሣሹ /የAሁን ተጠሪ/ በጡረታ ሕጉ Eና በድርጅቱ የAስተዳደር መመሪያ ቁጥር 3.1.1.10.4 መሰረት በEድሜ ገደብ ጡረታ ከወጡ በኋላ ወደ ሥራዬ ልመለስ በማለት የሚጠይቁበት የሕግ ስርዓት ስለልለ ክሱ ውድቅ ይደረግ የሚል ነው።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ መጋቢት 14 ቀን 1999 ዓ.ም. በሰጠው ውሣኔ የከሣሽ ድርጅትን የAስተዳደር መመሪያ ትክክል 347 348 Eንዳልሆነ ወይም Eንደልለ ከሣሹ የሚያቀርቡት ክርክር ሣይኖር ከፍዬ ያልጨረስኩትን ገንዘብ ሣልከፍል መሰናበት የለብኝም የሚለው መከራከሪያ በድርጅቱ ውስጥ ለመቆየት ዋስትና ላሆን Aይችልም በሚል ክሱን ውድቅ Aድርጎታል።
በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ውሳኔ ቅር የተሰኙት ከሣሽ /የAሁን ተጠሪ/ ቅሬታቸውን በይግባኝ ለፍ/ከ/ፍ/ቤት Aቅርበዋል። የፍ/ከ/ፍ/ቤትም የAሁን Aመልካችን በማስቀረብ የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ግንቦት 28 ቀን 1999 ዓ.ም. በሰጠው ውሣኔ ተጠሪው በድርጅቱ ሲቀጠሩ በጡረታ የተገለሉ መሆኑ ታውቆ ስራቸውን ጀምረው ሲሰሩ Eንደገና 6A ዓመት የጡረታ Eድሜ ስለደረሰ በማለት ለሁለተኛ ጊዜ በጡረታ ማሰናበቱ ከሕጉ Aግባብ ውጪ በመሆኑ ስንብቱ Aላግባብ ነው። ስለዚህ ይግባኝ ባይ /የAሁን ተጠሪ/ የ6 ወር ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሐቸው ወደ ስራቸው Eንዲመለሱ በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሮታል።
ይህ የሰበር S´Ñw የቀረበው Aመልካች ሰኔ 18 ቀን 1999 ዓ.ም.
ጽፈው ባቀረቡት የሰበር ማመልከቻ የፍ/ከ/ፍ/ቤት ተጠሪ የ6 ወር ደመወዝ ተከፍሐቸው ወደ ሥራ ይመለሱ ሲል የሰጠው ውሣኔ ከA/ቁ. 377/96፣ ከድርጅቱ የAስተዳደር መመሪያና ከጡረታ ሕጋችን Aግባብ ውጪ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ለዚህ ችሎት Aቤት በማለታቸው ነው።
ይህ ችሎት የAመልካችን Aቤቱታ ተመልክቶ በዚህ ጉዳይ ተጠሪ በEድሜ ገደብ ጡረታ የወጣ መሆኑ ተረጋግጦ Eያለ ስንብቱ ሕገወጥ ነው ተብሎ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎት ወደ ሥራ ይመለስ መባሉ በAግባቡ መሆን Aለመሆኑን ለማጣራት ተጠሪን Aስቀርቦ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር Aካሂደዋል። Eኛም የግራ ቀኙን ክርክር Aግባብ ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
በመሰረቱ u›ªÏ l. 377/96 በAንቀጽ 24/3/ ላይ የሥራ ውል ከሚቋረጥባቸው ምክንያቶች Aንዱ ¾ሰራተኛው Aግባብ ባለው ሕግ መሰረት በጡረታ ሲገለል መሆኑ ተደንግጓል። ይህ Eንደተጠበቀ ሆኖ የAመልካች መ/ቤት የAስተዳደር መመሪያ ቁጥር 3.1.1.1A.4 Eና የመንግሥት ሰራተኞችን የጡረታ ጉዳይ የተመለከተው A/ቁ. 345/95 Aንቀጽ 12/1/ሐ/ የመንግሥት ሰራተኞች የጡረታ መውጫ Eድሜ 6A ዓመት መሆኑን በግልጽ ደንግጓል።
ከዚህ Aንፃር ተጠሪው የጡረታ Eድሜያቸው መድረሱን ክደው ያልተከራከሩ ሲሆን በEነዚህ ሕጎች መሰረት ከስራቸው በጡረታ የማይገለሉበት ወይም የስራ ውላቸው የማይቋረጥበት ምክንያት Aልተገኘም። ተጠሪው የቀረብኝን Eዳ ሣልከፍል በጡረታ ልገለል Aይገባም ቢሉም በጡረታ ቢገለሉ Eንኳ Eዳቸውን ከመክፈል Eንደማይገደቡ ግልጽ ነው። የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በውሣኔው Eንዳተተው ሁሉ Eዳቸውን Aለመክፈላቸው በድርጅቱ ውስጥ ለመቆየት ዋስትና ላሆናቸው Aይችልም። Aመልካቹም ቢሆን የጡረታ Eድሜው ያለፈን ሰራተኛ ወደ ሥራ መልስ ተብሎ የሚገደድበት የሕግ Aግባብ የለም። በመሆኑም የፍ/ከ/ፍ/ቤት ያለ Aንዳች የሕግ ድጋፍ ተጠሪው የ6 ወር ደመወዝ ተከፍሐቸው ወደ ሥራ ይመለሱ ሲል የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
Aመልካች በጡረታ የተገለለ ሰራተኛን /ተጠሪን/ ወደ ሥራ የሚመልስበትም ሆነ ውዝፍ የ6 ወር ደመወዝ የሚከፍልበት የሕግ Aግባብ የለም ብለን ወስነናል።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 1A819 መጋቢት 14 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።