No summary available.
ግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ መድህን ኪሮስ Aመልካች፡- ቻይና ዋንቦ Iንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን - Aልቀረበም።
ተጠሪ፡- ወርቅነህ ምህረቴ - Aልቀረበም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ የሥራ ውል የሚመሰረትበትን ሁኔታ የተመለከተ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የAሁን ተጠሪ ለAመልካች ድርጅት የጥብቅና Aገልግሎት ለመስጠት ተቀጥሬ ደመወዝ Eየተከፈለኝ በጥቅምት 2 ቀን 1996 ዓ.ም በተሰጠኝ የውክልና ሥልጣን ድርጅቱን በጥብቅና ሥራ በማገልገል ላይ ሳለሁ Aመልካች የስራ ውልን ያቋረጠው ስለሆነ በAመልካች ላከፈከኝ ይገባል ያሉትን ክፍያ በመዘርዘር በAማራ ክልል ደ/ማርቆስ ወረዳ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ ነው። የAሁን Aመልካች በሰጠው መልስ ድርጅቱ ተጠሪን በሰራተኛነት Aልቀጠረም፣ ደመወዝም Aልከፈለም፤ የድርጅቱ ጠበቃ የነበሩት Aቶ የስጋት ንጉሴ ሥራቸውን ሲለቁ Aዲስ Aበባ የሚገኙትንና የድርጅቱ የህግ Aማካሪ የነበሩትን Aቶ ጥበቡ ጋሹ የተባሉትን ግለሰብ መጥተው ደ/ማርቆስ Aካባቢ ያለውን የድርጅቱን ጉዳይ Eንዲከታተሉ ስንጠይቃቸው Aዲስ Aበባ ያለው ጉዳይ ብዙ ስለሆነ መምጣት Aልችልም - ነገር ግን Eኔ ደመወዝ Eየከፈልኩት የEኔን ቦታ ሸፍኖ የሚሰራ ሰው ስላገኘሁ ድርጅቱ ውክልና ብቻ ይስጠውና የጥብቅና Aገልግሎት ይስጥ በማለት በጠየቁን መሰረት ለAሁን ተጠሪ የውክልና ስልጣን ሰጥተናቸው ሲያገለግሉ ከመቆየታቸው በስተቀር ከEኛ ጋር የሥራ ውል የላቸውም፣ በመሆኑም 335 336 በመካከላችን የቅጥር ውል ሳይኖር ተጠሪ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል። ፍ/ቤቱም የቀረበለትን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ በተጠሪ የቀረበው የሰነድ ማስረጃ የሚያስረዳው ተጠሪ በAመልካች መወከላቸውን ነው በተጠሪ የተቆጠሩት ምስክሮች የመሰከሩትም ተጠሪ በድርጅቱ ውስጥ ተቀጥረው መስራታቸውን Eንደማያውቁ ነው፣ በAመልካች በኩል የተቆጠሩት ምስክሮች ደግሞ Aመልካች የሰጠውን መልስ በሚደግፍ መልኩ መስክረዋል፣ በግራ ቀኙ የጋራ ምስክር ሆነው የተቆጠሩት Aቶ ጥበቡ ጋሹ ቀርበው Eኔ በስሬ ልሎች ባለሙየዎችን Eየቀጠርኩ በተመሳሳይ ሁኔታ በልሎች ክልሎችም የሙያ ስራ ስለምሰራ ተጠሪንም በዚሁ መልክ ቀጥሬAቸው ደመወዝ Eየከፈልኳቸው Aመልካች በሚሰጣቸው የውክልና ሥልጣን በጥብቅና Eንዲያገለግሉ ተደርጎ Eኔ ከAመልካች ድርጅት ጋር ያለኝ ውል ሲቋረጥ ተጠሪ ሥራቸውን Aቁመው በEጃቸው የሚገኙትን መዝገቦች Eንዲያስረክቡ በነገርኳቸው መሰረት Aስረክበዋል በማለት የመሰከሩ ስለሆነ Aመልካች ባቀረቧቸው ማስረጃዎች ስላላስረዱ በግራ ቀኙ መካከል የሥራ ውል የለም፣ መካከላቸው የሥራ ውል ከልለ ደግሞ ተጠሪ የሥራ ውልን መሰረት Aድርገው ክስ ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ መብት ስለልላቸው ያቀረቡት ክስ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 33(2) መሰረት ውድቅ ተደርጓል በማለት ወስኗል። የAሁን ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለምስ/ጎጃ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት Aቅርበው ፍ/ቤቱ በAዋጅ ቁ. 377/96 Aንቀጽ 6 Eና 7 መሰረት የሥራ ውል በጽሁፍም ሆነ ያለጽሁፍ ላመሰረት ስለሚችል ተጠሪ ያቀረቡት የውክልና ሥልጣን ማስረጃ በግራ ቀኙ መካከል ውል መኖሩን የሚያስረዳ ሆኖ ሳለ የስር ፍ/ቤት ለህጉ የተሳሳተ ትርጓሜ በመስጠት ተጠሪ የጠየቋቸው ክፍያዎች Aይገቧቸውም በማለት የሰጠው ውሳኔ ሚዛናዊነት የጎደለው ነው በሚል ተጠሪ የጠየቋቸው ክፍያዎች ይከፈሐቸው ሲል ወስኗል።
የሰበር Aቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ ለማስለወጥ ሲሆን ይህ ችሎት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔዎች Aግባብ ካለው ህግ ጋር Aገናዝቦ በመመርመር በAመልካችና በተጠሪ መካከል የሥራ ውል Aለ የተባለው በAግባቡ መሆን Aለመሆኑ ተጣርቶ መወሰን ያለበት ነጥብ ሆኖ ስላገኘው ጉዳዩ ለሰበር Eንዲቀርብ Aድርጓል።
መዝገቡን Eንደመረመርነው የምስ/ጎጃ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት በግራ ቀኙ መካከል የሥራ ውል Aለ ለማለት የቻለው በተጠሪ የቀረበው የውክልና ሥልጣን ማስረጃ በግራ ቀኙ መካከል በቅጥር ላይ የተመሰረተ የውል ግንኙነት Eንደነበረ ያረጋግጣል በሚል መሆኑን ተገንዝበናል። በመሰረቱ በሁለት ወገኖች መካከል በቅጥር ላይ የተመሰረተ የሥራ ውል በጽሁፍ ቢደረግም ባይደረግም ውጤቱ ተመሳሳይ መሆኑ የማያከራክር ነው። ይህ የሚሆነው ግን ግንኙነቱ በውል ላይ የተመሰረተ ሲሆንና ይህም በማስረጃ ሲረጋገጥ ነው።
በዚህ ጉዳይ ተጠሪ በAመልካች ድርጅት ተቀጥረው ደመወዝ Eየተከፈላቸው የጥብቅና Aገልግሎት ሲሰጡ መቆየታቸውን ለማረጋገጥ ያቀረቡት በAመልካች ተሰጥቷቸው የነበረውን የውክልና ሥልጣን ማስረጃ ሲሆን ይህ ማስረጃ የሚያረጋግጠው Aመልካች በተጠሪ ተወክለው Eንደነበረ Eንጂ ተቀጥረው ሲያገለግሉ Eንደነበረ Aይደለም። በልላ በኩል በግራ ቀኙ የጋራ ምስክር ሆነው የተቆጠሩት ግለሰብ ለAመልካች ድርጅት የጥብቅናና የህግ ማማከር Aገልግሎት ሲሰጡ በነበረበት ወቅት ተጠሪን በመቅጠር ደመወዝ Eየከፈሐቸው ከAመልካች በሚያገኙት የውክልና ሥልጣን ለድርጅቱ የጥብቅና Aገልግሎት Eንዲሰጡ ያሰማሯቸው መሆኑንና ድርጅቱ ከEሳቸው ጋር የነበረው ግንኙነት ሲቋረጥም ተጠሪ ከድርጅቱ ጋር የነበራቸው ግንኙነትም Aብሮ የተቋረጠ መሆኑን መስክረዋል። ከዚህ መረዳት ሚቻለው ተጠሪ የተቀጠሩት Aመልካች ድርጅት በቀጠራቸው ግለሰብ Eንጂ በAመልካች Aለመሆኑ ራሳቸው ተጠሪ ባቀረቧቸው ምስክር የተመሰከረ መሆኑን ነው። በመሆኑም በግራ ቀኙ መካከል የውል ግንኙነት Eንዳልነበረ ተገንዝበናል። በተጠሪና በAመልካች መካከል የውል ግንኙነት ካልነበረ ደግሞ ተጠሪ በAመልካች ላይ ከውል የመነጨ የመብት ጥያቄ ማቅረብ Aይችሉም። በዚህም ምክንያት ተጠሪ Aገልግሎቱን ሲሰጡ የነበረው ከAመልካች ጋር በነበራቸው የውል ግንኙነት መሆኑን ባላስረዱበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤት የውክልና ሥልጣን ማስረጃው በግራ 337 338 ቀኙ መካከል የውል ግንኙነት Eንደነበረ ስለሚያስረዳ በተጠሪ የተጠየቁትን ክፍያዎች Aመልካች መክፈል Aለበት በማለት መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የAማራ ክልል ደ/ማርቆስ ወረዳ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 01741 ታህሣስ 13 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል። የክልሉ የምስ/ጎጃ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ.12681 ጥር 9 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሸሯል።
ተጠሪ የAመልካች ተቀጣሪ ስላልነበሩ Aመልካች በተጠሪ የተጠየቀውን ክፍያ ለመክፈል Aይገደድም በማለት ተወስኗል። ይጻፍ።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሳራቸውን ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።