No summary available.
ሐምል 10 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ Aሰግድ ጋሻው ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የIት/ንግድ ባንክ - የቀረበ የለም።
መልስ ሰጪ፡- Aቶ ኃይል ገ/ሥላሴ - ቀረበ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
Aቤቱታው የቀረበው የፍ/መጀ/ደረጃ ፍ/ቤት ሥራ ክርክር ችሎት በመ/ቁ. 16341 ግንቦት 19 ቀን 1997 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔና በይግባኝም የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 40290 ሕዳር 6 ቀን 1998 ዓ.ም የሥር ፍ/ቤቱን ውሣኔ በማጽናት ይግባኙ Aያስቀርብም በማለቱ ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስላለበት ላታረም ይገባዋል በማለት የቀረበ Aቤቱታ ነው።
የAሁኑ መ/ሰጪ በሥር በAሁን Aመልካች ላይ ያቀረበው ክስ፡- ህዳር 14 ቀን 1991 ዓ.ም ጀምሮ በተከሣሽ መ/ቤት በጥበቃ ሰራተኛነት በወር ብር 230 ደመወዝ Eየተከፈለኝ ስሰራ ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውልን በማቋረጡ የሥራ ስንብት ክፍያ፣ የካሣ ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ Eና የዓመት Eረፍት ፈቃድ ክፍያ Eንዲሁም ክፍያው ለዘገየበትም ክፍያ የሥራ ምስክር ወረቀት ጨምሮ ከወጪና ኪሣራ ጋር Eንዲከፈል Eንዲወሰንበት የሚል ነው።
የAሁን Aመልካችም ለቀረበለት ክስ የሰጠው መልስ፡- ከሣሽ ተቀጥሮ ሲሰራ የነበረው ድርጅቱ በመያዣነት የያዛቸውን የተለያዩ ተበዳሪ ሰዎች ገንዘብ ባለመክፈላቸው ንብረቱ Eስኪሸጥ ድረስ በጥበቃ ሰራተኛነት በተለያየ ጊዜ ውል Eየታደሰለት ሲሰራ የቆየና የመጨረሻ ጊዜ ውል የታደሰለትም ግንቦት 6 ቀን 1996 ዓ.ም Eስከ ነሐሴ 5 ቀን 1996 ዓ.ም ሲሆን፣ ከሣሽ ከሥራ ላሰናበት የቻለው ድርጅቱ የፅዳት Eና የጥበቃ ሥራን ለልላ ድርጅት በኮንትራት ለማሰራት በመስጠቱ ነው በማለት ስንብቱ ህገወጥ ነው ላባል ስለማይችል ከሣሽ የጠየቀው የክፍያ ጥያቄ Aይገባውም ሲል ተከራክሯል። Aመልካች ሥራውን ለልላ ድርጅት በኮንትራት መስጠቱን የሚያሳይም ሰነድ Aቅርቧል።
ክሱ የቀረበለት የፍድ/መጀ/ደረጃ ፍ/ቤትም የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ በመጨረሻም፡- የከሣሽ የሥራ ውል የሚቋረጠው ነሐሴ 5 ቀን 1996 ዓ.ም ሆኖ ተከሣሽ ግን ከሣሽን ከሥራ ያሰናበተው ሰኔ 28 ቀን 1996 ዓ.ም የውሉ ጊዜ ሳያበቃ በመሆኑ ስንብቱ ህገወጥ ነው። የሥራ ውሉ የተቋረጠው ከህግ ውጪ ሲሆን ደግሞ የስንብት ክፍያ ላከፈል ስለሚገባ የከሣሽ ጥያቄ ተቀባይነት Aለው።
የካሣ ክፍያን በተመለከተ የሥራ ውሉ ለተወሰነ ጊዜ በመሆኑ የውሉ ጊዜ ላቆይ Eስከሚችለው ጊዜ ድረስ ያለው ከሰኔ 28 ቀን 1996 ዓ.ም Eስከ ነሐሴ 5 ቀን 1996 ዓ.ም ያለው ደመወዙ ላከፈለው ይገባል።
የዓመት Eረፍትን በተመለከተም በAዋጁ ቁጥር 377/96 A.79/5/ ከሁለት ዓመት በላይ ላጠየቅ ስለማይችል የሥራ ውሉ ከመቋረጡ ሁለት ዓመት በፊት ያለው ይከፈል። የሥራ ምስክር ወረቀት ተከሣሽ ለከሣሽ Eንዲሰጥ በማለት መወሰኑን ከመዝገቡ መረዳት ይቻላል።
የAሁን Aመልካች በተሰጠው ውሣኔ ላይ ይግባኝ ለፍድ/ከፍተኛ ፍ/ቤት Aቅርቦም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 ይግባኙ ተሰርዞበታል።
ለሰበር የቀረበው Aቤቱታም በዚሁ ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስላለበት Eንዲታረም ¾T>ÖÃp ሲሆን፣ Aቤቱታው ተመርምሮ የሥር ፍ/ቤት የመ/ሰጪ የሥራ ውል የተቋረጠው በህገወጥ መንገድ ነው በማለት ለመ/ሰጪ የተለያዩ ክፍያዎች Eንዲከፈል የተሰጠው ውሣኔ በህጉ Aግባብ 305 306 መሆን Aለመሆኑን ለማጣራት መዝገቡ ለሰበር ችሎት Eንዲቀርብ ትEዛዝ ተሰጥቶበታል።
በዚህም መሰረት ግራቀኙ Eንዲቀርቡ ተደርጐ የቃል ክርክራቸው ተሰምቷል።
Eኛም መዝገቡን መርምረናል። Eንደመረመርነውም በAመልካችና በመ/ሰጪ መካከል የሥራ ውሉ የሚቆየው Eስከ ነሐሴ 5 ቀን 1996 ዓ.ም ሆኖ ከወዲሁ ሰኔ 28 ቀን 1996 ዓ.ም የመልስ ሰጪ ውል ላቋረጥ የቻለው መልስ ሰጪ ይሰራበት የነበረው የጥበቃ ሥራና የፅዳት Aገልግሎትንም ጨምሮ ለልላ ድርጅት በኮንትራት ተሰጥቶ በማሰራት መሆኑን Aመልካች ማስረጃ Aቅርቦ ማስረዳቱ በሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ ተመዝግቧል።
በዚህ መሰረት Aመልካች የመልስ ሰጪን የሥራ ውል ላያቋርጥ የቻለው መልስ ሰጪ ይሰራበት የነበረው የሥራ መደብ ለልላ ድርጅት በመሰጠቱ ምክንያት መሆኑ የተረጋገጠና ያልተካደ መሆኑን ያሳያል። ይህ ደግሞ Aሰሪው በAዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም፣ የድርጅቱን ምርታማነት ለማሳደግ የAሰራር ዘድዎችን በመለወጡ ምክንያት ሰራተኛው የያዘው የሥራ መደብ ቢሰረዝ Aሰሪው ማስጠንቀቂያ በመስጠት በህጋዊ መ”ÑÉ የሰራተኛውን የሥራ ውል ማቋረጥ EንÇ=ችል የAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ Aዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 28 መብት ይሰጠዋል።
No topics extracted.
የሥር ፍ/ቤት የመልስ ሰጪ የሥራ ውል የተቋረጠው ከህግ ውጪ ነው ያለው የውል ዘመኑ ከማለቁ በፊት የሥራ ውሉ መቋረጡን ምክንያት በማድረግ ብቻ ነው። ይሁን Eንጂ የሥራ ውሉ ለተወሰነ ጊዜም ሆነ ላልተወሰነ ጊዜ ቢሆን Aሰሪው የሥራ ውሉን ለማቋረጥ በቂና ህጋዊ የውል ማቋረጫ ምክንያት Eስካለው ድረስ የውል ዘመኑ ከማለቁ በፊት ወይም የውል ዘመኑ ላልተወሰነ ጊዜ ከሆነ በAዋጁ Aንቀጽ 35 መሰረት የማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት የሥራ ውሉን ለማቋረጥ Eንደሚችል ከህጉ ድንጋጌ መረዳት ይቻላል።
ማስጠንቀቂያ መስጠት የሚያስፈልገውም በተለይ በዚህ ጉዳይ የውሉ ዘመን ሳያልቅ በበቂ ምክንያት የሥራ ውሉ ከወዲሁ ላቋረጥ የሚችል ሆኖ ሲገኝ Eንጂ የውሉ ዘመኑ በማለቁ የሥራ ውሉ ለሚቋረጥ ሰራተኛ ማስጠንቀቂያ መስጠት Aስፈላጊ Aይሆንም። Aመልካች የውል ዘመኑ ከመድረሱ በፊት የመልስ ሰጪን የሥራ ውል ለማቋረጥ በቂ ምክንያት መኖሩን Eያስረዳ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የሥራ ውሉን ማቋረጡ ግን Aግባብ Eንዳልሆነ ግልጽ ነው :: ይህ ማለት ግን የሥራ ውሉ የተቋረጠው ከህግ ውጪ ነው ማለት ሳይሆን ውጤቱ ማስጠንቀቂያ ባለመስጠቱ በህጉ በተጠቀሰው በማስጠንቀቂያው ጊዜ ለሰራተኛው ላከፈለው ይገባ የነበረውን ደመወዝ Eንዲከፍለው የሚያስገድደው ብቻ ነው የሚሆነው።
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት Aመልካች የመልስ ሰጪን የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ በማቋረጡ የሥራ ውሉ የተቋረጠው ከህግ ውጪ ነው በሚል ይህን ተከትሎ የሚከፈል ክፍያ Eንዲፈፀም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስላለው ላታረም የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ