No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 2A416 ታህሣሥ A8 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- Aቶ ቢኒያም ገረመው - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የቻይና መንገድና ድልድይ ሥራ ድርጅት
ለሰበር Aቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ የጀመረው በደቡብ ጎንደር መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የፎገራ ወረዳ ፍ/ቤት ነው።
Aመልካች ተሻሽሎ በቀረበ የክስ ማመልከቻ ተጠሪ ከሥራ ያላግባብ ያሰናበታቸው ስለሆነ Aዋጁ የሚፈቅድላቸውን ክፍያዎች Eንዲከፍላቸው ጠይቀዋል።
ፍ/ቤቱም ተጠሪ Aመልካችን ከሥራ ያሰናበተው ከሕግ ውጭ በመሆኑ የስንብት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ክፍያ፣ የAመት ፈቃድ በገንዘብ ተቀይሮ፣ Eንዲሁም የካሣ ክፍያ Eንዲከፈላቸው ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ በደቡብ ጎንደር መ/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኙን ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም Aመልካች ከስራ የተሰናበቱት በሕገ ወጥ መንገድ መሆኑን በመቀበል የሥር ፍ/ቤት ግን ክሱ Eንዲሻሻል ሲያዝ በቂ ምክንያት ያልነበረው በመሆኑና የተጠየቀውን ገንዘብ ከፍ ለማድረግ ብቻ ክስ ላሻሻል Eንደሚችል በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 91 ስላልተመለከተ Aመልካች ክርክሩን ላቀጥል የሚገባው መጀመሪያ ባቀረበው የገንዘብ መጠን ነው በማለት Aመልካች በመጀመሪያ ደረጃ ክስ የጠየቁትን የAገልግሎት ክፍያና የ2 ወር ደመወዝ ብቻ Eንዲከፍላቸው ወስኗል።
የAሁኑ የሰበር Aቤቱታ የቀረበው ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ነው።
ይህ ችሎትም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የተሻሻለውን ክስ ውድቅ በማድረግ በመጀመሪያ በቀረበው ክስ መሰረት ውሣኔ መስጠቱ ተገቢ መሆን Aለመሆኑን ለመመርመር Aቤቱተው ለሰበ` ችሎት ቀርቦ Eንዲታይ በማድረግ ተጠሪ ለAቤቱታው መልስ Eንዲሰጡ መጥሪያ ልኳል። ነገር ግን ተጠሪው መጥሪያ ደርሶት ባለመቅረቡ ችሎቱ መዝገቡን Eንደሚከተለው መርምሯል።
ከላይ Eንደተገለፀው ጉዳዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍ/ቤት ውሣኔ የሰጠው የAመልካችን የተሻሻለ ክስ መሰረት በማድረግ ነው። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ግን Aመልካች በመጀመሪያ ክሣቸው ላይ የጠየቁትን የገንዘብ መጠን ከፍ ለማድረግ ብቻ ክሱ Eንዲሻሻል መደረጉ ተገቢ Aይደለም በማለት የAመልካችን የመጀመሪያ ክስ መሰረት Aድርጎ ውሣኔ ሰጥቷል። ይህ ችሎትም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የተሻሻለውን ክስ ውድቅ ለማድረግ የሕግ መሰረት ነበረው ወይ? የሚለውን ነጥብ ተመልክቷል።
የመጀመሪያው ፍ/ቤት ክሱ Eንዲሻሻል የፈቀደበት ምክንያት በመጀመሪያው ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ ያልተመለከተ ቢሆንም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ክሱ Eንዲሻሻል የተፈቀደው Aመልካች የሚጠይቋቸውን መብቶች በተብራራ ሁኔታ Aሻሽለው Eንዲያቀርቡ መሆኑን በውሣኔው ላይ Aስፍሯል። በዚህም መሰረት Aመልካቹ በቀድሞ ክሣቸው ከጠየቁት ዳኝነት በተጨማሪ በሕገ-ወጥ ስራ ስንብት ምክንያት ላከፈሐቸው የሚገባቸውን ልሎች መብቶች Aካተው ጠይቀዋል። ይህም ቀድሞ Eንዲከፈላቸው የጠየቁትን የገንዘብ መጠን ከፍ Eንዲል Aድርጎታል።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም የተሻሻለውን ክስ ውድቅ ያደረገው በክስ Tሻሻል ሰበብ በመጀመሪያ ዳኝነት የተጠየቀበትን የገንዘብ መጠን ከፍ ማድረግ Aይገባም በማለት ነው። በመሆኑም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 91 መሰረት ክስ ሲሻሻል ዳኝነት የተጠየቀበትን የገንዘብ መጠን ከፍ ማድረግ ይቻል ወይም Aይቻል Eንደሆነ ተመልክተናል።
በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 91 መሰረት ፍርድ ከመስጠቱ በፊት በማናቸውም ጊዜ ወይም ፍ/ቤቱ ተገቢ ሆኖ ካገኘው የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ነገሩን ይበልጥ የሚያብራራው ወይም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዳ ከሆነ ክሱ 293 294 Eንዲሻሻልና ክርክሩ Eንዲለወጥ ላፈቀድ ይችላል። Eንግዲህ Aንድ ተከራካሪ ክሱን ለማሻሻል ወይም ክርክሩን ለመለወጥ ፍ/ቤትን ለመጠየቅ መብት ያለው ሲሆን ፍ/ቤቱ ግን ጥያቄውን የሚቀበለው የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ክስ የቀረበበትን ጉዳይ በይበልጥ ግልጽ የሚያደርገው ወይም ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት Aስፈላጊ መሆኑን ሲያምን ነው።
በተያዘው ጉዳይ Aመልካች በመጀመሪያው ክሣቸው የጠየቁት የስንብት ክፍያና የ2 ወር ደሞዝ ብቻ ነበር። ነገር ግን Aንድ ሰራተኛ በሕገወጥ መንገድ ከሥራ ሲሰናበት በAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ Aዋጅ መሰረት የተለያዩ ክፍያዎች የማግኘት መብት Aለው። Aመልካችም በሕገወጥ መንገድ ከሥራ ከተሰናበቱ ላከፈላቸው የሚገባውን ክፍያዎች ሁሉ የማግኘት መብት ስላላቸው በመጀመሪያ ሣይጠይቁ የቀሩትን ክፍያዎች ጨምረው ክሱን ማሻሻላቸው ለትክክለኛ ፍትህ Aሰጣጥ የሚረዳ በመሆኑ ክሱ መሻሻሉ ስህተት ነው ለማለት Aይቻልም። በሆኑም ክስ የሚሻሻለው ጉዳዩን ለማብራራት ብቻ ሣይሆን ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት Aስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በመሆኑና Aመልካችም በሕገወጥ መንገድ ከተሰናበቱ ላከፈላቸው የሚገባውን ክፍያ ሁሉ መጨመራቸውና ይህም ዳኝነት የጠየቁበትን የገንዘብ መጠን ከፍ ያደረገው ቢሆንም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዳ በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የተሻሻለውን ክስ ተቀባይነት ማሣጣቱ ስህተት ሆኖ Aግኝተነዋል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የደ/ጎንደር መ/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. A6764 በግንቦት 11 ቀን 1997 ዓ.ም. Aመልካች ላከፈላቸው የሚገባው በቀድሞ ክስ የጠየቁት ብቻ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ ክፍል ተሽሯል።
Aመልካች ላከፈላቸው የሚገባውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ የፎገራ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ. A1511/96 በጥቅምት 17 ቀን 1999 ዓ.ም.
የሰጠው ውሣኔ ጸንቷል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ የመ/ቁ. 2A67A ጥቅምት 14 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች መንበረፀሐይ ታደሰ ጌታቸው ምህረቱ Aሰግድ ጋሻው ሂሩት መለሰ Aብዱረሂም Aህመድ Aመልካች፡- የIትዮጵያ ቴልኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን - ነገረፈጅ ግርማ ማርቆስ ተጠሪ፡- Aቶ ሰለሞን በርሄ - Aልቀረቡም።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ የጀመረው በፍ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁኑ ተጠሪ በስር ከሣሽ ነበሩ። በክሣቸውም ተጠሪ Aመልካች መ/ቤት ተቀጥረው ሲያገለግሉ መ/ቤቱ ያላግባብ ስላሰናበታቸው የተለያዩ ክፍያዎች Eና ውዝፍ ደሞዝ ተከፍሎAቸው ወደሥራቸው Eንዲመለሱ ጠይቀዋል። Aመልካች ቀርቦ ተጠሪ በጡረታ ተገለው የነበሩና ለ3 ዓመት ጥበቃን ለማጠናከር በጊዜያዊነት የተቀጠሩ በመሆናቸው የተቀጠሩበት ጊዜ ሲያበቃ መሰናበታቸው Aግባብ መሆኑን ተከራክሯል። ጉዳዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍ/ቤትም የቅጥር ውሉ ለተወሰነ ጊዜ በመሆኑ ጊዜው ሲያበቃ መሰናበታቸው Aግባብ ነው። የ3 ዓመት ቦነስ የ3 ዓመት ትርፍ ሰዓት Eና በዚህ 3 ዓመት ውስጥ ለ21 የበዓል ቀናት የሰሩበት ክፍያ ግን ይከፈላቸው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለተው የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ደግሞ የቦነስ ጥያቄው ባልሰሩበት ጊዜ የተጠየቀ ነው በሚል ይህን የውሣኔ ክፍል ብቻ ሽሮታል።
የAሁኑ የሰበር Aቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ሲሆን የቅሬታው ነጥብ የክፍያ ጥያቄዎቹ በይርጋ የሚታገዱ ሆነው Eንዲከፈል መወሰኑ Eና የትርፍ ሰዓት ለመሥራታቸውም ያስረዱት ነገር ሣይኖር Aመልካች Aልካደም በሚል ብቻ Eንዲከፈላቸው መወሰኑ ስህተት ነው የሚል ነው።
295 296 ይህ የሰበር ችሎትም የይርጋው መቃወሚያ ታልፎ መወሰኑ Aግባብ መሆን Aለመሆኑን ለመመርመር Aቤቱታው ለሰበር ችሎት Eንዲቀርብ Aድርጓል። ተጠሪ ቀርበው መልሣቸውን በጽሁፍ Eንዲያቀርቡ የታዘዘ ቢሆንም በትEዛዙ መሰረት ያቀረቡት መልስ ባለመኖሩ ችሎቱ መዝገቡን Eንደሚከተለው መርምሯል።
ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ከጠየቁት ዳኝነት ውሣኔ የተወሰነላቸው የትርፍ ሰዓት Eና የበAል ቀናት የሰሩበት ክፍያ ብቻ ሲሆን Aመልካች ግን ይህም ክፍያ ቢሆን በይርጋ ቀሪ የሚሆን ነው ሲል ተከራክሯል። ከስር ክሱ መረዳት Eንደቻለነው ተጠሪ የጠየቁት የ3 ዓመት የትርፍ ሰዓት Eና በዚሁ 3 ዓመታት ውስጥ ለ21 የበዓል ቀናት የሰሩበት ክፍያን ነው። በAሰሪና ሰራተኛ Aዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 162(3) መሰረት ሰራተኛው የሚጠይቃቸው የደሞዝ' የትርፍ ሰዓት Eና ልሎች የክፍያ ጥያቄዎች ሰራተኛው ክፍያዎቹ መጠየቅ ካለባቸው ጊዜ Aንስቶ Eስከ 6 ወር ካልጠየቁ መብቱ በይርጋ የሚታገድ መሆኑ ተመልክቷል። ከፍ ሲል Eንደተመለከተው ደግሞ ተጠሪ የጠየቁት ክፍያ ስራ ከጀመሩበት ከህዳር 5 ቀን 1993 ዓ.ም. ጀምሮ Eስከ ተሰናበቱበት ህዳር 1 ቀን 1996 ዓ.ም. ድረስ ያለውን ክፍያ ነው የትርፍ ሰዓትU ሆነ የበAላት ቀን ክፍያ ደግሞ ከደሞዝ ጋር Aብሮ የሚከፈል በመሆኑ (የAዋጁን Aንቀጽ (68(2)ይመለከ…ል) ተጠሪ Eነዚህን ክፍያዎች መጠየቅ ያለባቸው የትርፍ ሰዓት ወይም የበAል ቀናት ¾ሰሩበት ወር ደሞዝ ከሚከፈልበት ቀን Aንስቶ Eስከ 6 ወር ድረስ ብቻ ነው።
በመሆኑም ተጠሪ በክሣቸው ካቀረቡት የክፍያ ጥያቄ ውስጥ በይርጋ ላታገድ የማይችለው ክስ ካቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ ወደኋላ ያለው የስድስት ወር ክፍያ ብቻ ነው።
በEርግጥ Aመልካች የይርጋውን ክርክር ስለ ማንሣቱ በፍ/መ/ደረጃ ፍርድ ቤት ውሣኔ ግልባጭ ላይ የሚታይ ባይሆንም በፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ ሃተታ ላይ ግን ክርክሩ መነሣቱ ይታያል። ይሁን Eንጂ ፍርድ ቤቱ ክርክሩን በዝምታ Aልፎታል። ተጠሪም ቢሆኑ በዚህ ችሎት ቀርበው ክርክሩ በስር ፍርድ ቤት Aለመነሣቱን ያስተባበሉት ነገር የለም። በልላ በኩል ግን Aመልካች ተጠሪ ትርፍ ሰዓት Eና የበAል ቀናት ያለመስራታቸውን ባለማስተባበሉ የስር ፍርድ ቤቶች Aቤቱታውን Eንዳመነበት መቁጠራቸው የሕግ ስህተት ፈጽመዋል Aያስብላቸውም። ምክንያቱም ተከሣሽ ክሱ ላይ የቀረበው” ነገር በዝርዝርና በግልጽ ያልካደው ከሆነ Eንደታመነ የሚቆጠር መሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 235 ስር በግልጽ ተመልክቷል።
በAጠቃላይ በይርጋ ላታገድ የማይችለው ክስ ከቀረuበት ጊዜ Aንስቶ ወደ ኋላ ባለው የ6 ወር ጊዜ ውስጥ ተጠሪ የሰሩበት የትርፍ ሰዓት Eና የበዓል ቀናት ክፍያ ብቻ በመሆኑ Aመልካች ላከፍል የሚገደደውም ይኸንኑ ክፍያ ብቻ ነው። የስር ፍ/ቤቶችም የAመልካችን የይርጋ ክርክር በማለፍ የ3 ዓመት የትርፍ Eና በAል ቀናት ክፍያ Eንዲከፈል መወሰናቸው የሕግ ስህተት ነው።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ውሣኔ ተሻሽሐል።
ክስ ከቀረበበት ጊዜ Aንስቶ ወደ ኋላ ሲቆጠር 6 ወር ያለፈው የክፍያ ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ይሆናል።
ክስ ከቀረበበት ጊዜ Aንስቶ ወደ ኋላ በAለው የ6 ወር ጊዜ ውስጥ ተጠሪ የሰሩት የትርፍ ሰዓት Eና የበዓል ቀናት ክፍያ ካለ ይኸው ታስቦ ይከፈላቸው።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ።