No summary available.
መጋቢት 18 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ታፈሰ ይርጋ መድኀን ኪሮስ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- የIትዮጵያ Eህል ንግድ ድርጅት ነ/ፈ ቀረበ።
ተጠሪ፡- Aቶ ግርማ ተገኝ ጠበቃ ቀርበዋል።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የጉዳዩ Aመጣጥ መጀመሪያ የAሁኑ ተጠሪ ከየካቲት ወር 1994 ዓ.ም.
ጀምሮ ለሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ስለተደረገላቸው ለEኔም ላደረግልኝ ይገባል በማለት ግንቦት 23 ቀን 1999 ዓ.ም. በተፃፈው ማመልከቻ ለፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ክስ ያቀርባሉ።
የAሁኑ Aመልካችም ከሥራ የተሰናበትከው በ1994 ዓ.ም. በመሆኑ የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄህ በይርጋ ይቋረጣል በማለት መቃወሚያ ያቀርባል።
ፍ/ቤቱም ይህን መቃወሚያ በመቀበል ክሱ በAዋጅ ቁጥር 337/96 Aንቀጽ 162/2/ መሰረት በይርጋ የሚቋረጥ ነው ሲል ክሱን በመሰረዝ መዝገቡን ዘግቶታል።
በመቀጠልም የAሁኑ ተጠሪ ለፍ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኝ ስላቀረቡ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በAዋጅ ቁጥር 337/96 Aንቀጽ 164/3/ መሰረት በይርጋው ተጠያቂ የሆነው ሰው ወይም ወገን የልላውን መብት በጽሑፍ ሲያውቅለት ተብሎ በተደነገገውን መሰረት ሲታይ በሕብረት ስምምነቱና በደመወዝ ስኬል Aፈፃፀም መመሪያው ሰራተኛው ከተጠያቂነት ነፃ መሆኑ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ የኋላ ቀሪ ክፍያ የሚያጠቃልል የደመወዝ ጭማሪ ላያገኝ ይችላል ተብሎ ስለተደነገገ ይህ ድንጋጌ የይርጋውን ጊዜ ያቋርጠዋል።
277 278 በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤት ክሱን በመቀበል ግራ ቀኙን Aከራክሮ የመሰለውን Eንዲወስን በማለት ይወስናል።
የሰበር Aቤቱታውም ላቀርብ የቻለው በዚሁ የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ነው። የሰበር Aመልካች ያቀረበው ቅሬታ ተጠሪው ያቀረቡት የተጨማሪ ደመወዝና የጥቅማጥቅም ጥያቄ በAዋጅ ቁጥር 337/96 Aንቀጽ 162 መሰረት በይርጋ ቀሪ የሚሆን በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ብንከራከርም የከፍተኛው ፍ/ቤት ይህን የመቃወሚያ ክርክራችንን ውድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤቱን ትEዛዝ በመሻር ክሱ በAዋጅ ቁጥር 337/96 Aንቀጽ 164/3/ መሰረት በይርጋ ቀሪ Aይሆንም በማለት መወሰኑ Aግባብ Aይደለም። ድርጅቱ ለተጠሪው ይርጋውን ለማቋረጥ የሚችል በጽሑፍ ያወቀለት መብት የለም። በሕብረት ስምምነቱና በደመወዝ ስኬል Aፈፃፀም መምርያውም ይህን የሚያረጋግጥ ድንጋጌ የለም። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቱ ውሣኔ ተሽሮ ክሱ በይርጋ ቀሪ የሚሆን ነው ተብሎ Eንዲወስንልን የሚል ነው።
ይህ የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም የሰበር Aቤቱታውን በመመርመር የስር ፍ/ቤት ክሱ በይርጋ Aይታገድም በማለት የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር Eንዲቻል Aቤቱታ¨< ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልሳቸውን Eንዲያቀርቡ Aዟል።
ተጠሪም ጥር 19 ቀን 2AAA ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት መልስ በሕብረት ስምምነታችን Aንቀጽ 32 Eና 34 መሰረት Eንዲሁም በድርጅቱ የደመወዝ ስኬል Aፈፃፀም መመሪያ ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ በሚሰራበትና በ1996 ዓ.ም.
በሥራ Aመራር ቦርዱ በተሻሻለው መመሪያ ቁጥር 6 Eና በቁጥር 3.3.10 መሰረት Aንድ ሰራተኛ በጥፋት ምክንያት በክርክር ላይ Eያለ የደመወዝ ጭማሪ መጠየቅ Eንደማይችል ነገር ግን ተጣርቶ ከጥፋቱ ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆኑ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ የደመወዝ ጭማሪውን ያለፈ ውዝፍ ክፍያም ጭምር ማግኘት Eንደሚችል ተደንግጓል። Eኔም የተሰናበትኩት በAግባቡ ያለመሆኑን ተረጋግጦ ስንብቱ ሕገወጥ ነው ተብሎ ስለተወሰነልኝ ውሣኔ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ስድስት ወር ሳይሞላ ነው ክሱን ያቀረብኩት በመሆኑም ክሱ በይርጋ Aይቋረጥም ተብሎ በፍ/ከ/ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ የሚነቀፍበት የሕግ ምክንያት ባለመኖሩ ውሣኔው Ãê“M˜ በማለት ተከራክረዋል።
Aመልካች ድርጅትም የመልስ መልሱን በማቅረብ ክርክሩን ለማጠናከር ሞክሯል።
በበኩላችን ደግሞ ክሱ በይርጋ ቀሪ ላሆን ይችላል ወይስ Aይችልም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን Eንደመረመርነውም ሐምል 199A ዓ.ም. በወጣው የሕብረት ስምምነት በAንቀጽ 34.2.7.4 የደመወዝ ጭማሪ በሚሰጥበት ወቅት በጥፋት ምክንያት በጊዜያዊ Eገዳ ላይ የሚገኝ ሰራተኛ በዚህ የሕብረት ስምምነት መሰረት የደመወዝ ጭማሪ ለማግኘት የAስተዳደር ውሣኔ የማያግደው ከሆነ ጭማሪውን ከተፈቀደበት ጊዜ ጀምሮ ያገኛል ተብሎ የተደነገገው የAስተዳደር ውሣኔው ላያግደው ይችላል ወይስ Aይችልም የሚለውን ቅድመ ሁኔታ ከተመለከቱ በኋላ የሚታይ Eንጂ በቀጥታ የደመወዝ ጭማሪን ለማግኘት በሚፈቅደው መንገድ Aይደለም።
No topics extracted.
በልላ በኩል ደግሞ ምንም Eንኳን በድርጅቱ የደመወዝ ስኬል የAፈፃፀም መመሪያ በAንቀጽ 3.3.1A በዲስፕላን ጉድለት ወይም በልላ ጥፋት ምክንያት በሕብረት ስምምነት ወይም በሥራ Aመራር Aባላት የAስተዳደር ደንብ መሰረት በቅጣት የሪከርድ የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞች የሪከርድ የጊዜ ገደቡ Eስኪያበቃ ድረስ የደመወዝ ጭማሪ Eንዳይሰጣቸው ተከልክለው የቆዩት ሰራተኞቹ ፈፀሙት የተባለው ድርጊት ተጣርቶ ከተጠያቂነት ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆናቸው ከተረጋገጠ ወይም የደመወዝ ጭማሪ Eንዳይሰጣቸው በAስተዳደር ውሣኔ ካልተወሰነ ከተጠያቂነት ነፃ መሆናቸው ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ ብቻ የኋላ ቀሪ ክፍያ” የማያጠቃልል የደመወዝ ጭማሪ ላያገኙ ይችላሉ ተብሎ ቢደነግግም ይህ ድንጋጌ የሚመለከተው ከድርጊታቸው ከተጠያቂነት ነፃ ከወጡ በኋላ በዚያው ድርጅት መሥራት የሚቀጥሉ Eንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ ሰኔ 9 ቀን 1991 ዓ.ም. ተሻሽሎ 279 280 በወጣው የደመወዝ Eስኬል Aፈፃፀም መመሪያ Aንቀጽ 2/ለ/ ስለተደነገገና ተጠሪው ደግሞ ይህን የደመወዝ ጭማሪ ክስ ከማቅረባቸው በፊት ጥር 28 ቀን 1996 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በሥራ ክር/መ/ቁ/4544 የተሰጠው ውሣኔ ተጠሪው ካሣ ተከፈሎAቸው ከድርጅቱ Eንዲሰናበቱ የተወሰነ በመሆኑ ተጨማሪ ደመወዙን የሚጠይቁበት የሕግ ምክንያት የለም።
በመሆኑም Eነዚህ ተጠሪው በሰበር መልሳቸው የጠቀሱዋቸውና የሥር ፍ/ቤትም ለውሣኔው መሰረት ያደረÒቸው የሕብረት ስምምነቱና የደመዝ ስኬል Aፈፃፃም መመሪያ Aንቀፆች ለተጠሪው መብት የሚሰጡ ባለመሆናቸው የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜውን ለማቋረጥ ምክንያት የሚሆኑበት መንገድ የለም። የሥር ፍ/ቤትም በሰጠው ውሣኔ ድርጅቱ ለከሣሹ /የAሁን ተጠሪ/ መብታቸው በጽሑፍ ያወቀላቸው በመሆኑ ክሱ በAዋጅ ቁጥር 337/96 Aንቀጽ 164/3/ መሰረት በይርጋ ቀሪ የሚሆንበት ምክንያት የለም በማለት የፍ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠውን ትEዛዝ uመሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀሙ ተረጋግጧል።
ው ሣ ኔ
ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 57A49 ሐምል 23 ቀን 1999 ዓ.ም. የተሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 24175 ግንቦት 23 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ ፀንቷል። ይፃፍ።
ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በAዋጅ ቁጥር 337/96 Aንቀጽ 162 መሰረት በይርጋ ቀሪ ሆኗል፤ ይፃፍ።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ።