No summary available.
ታህሣሥ 8 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታፈሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ወ/ሮ Eማዋይሽ Aበራ ተጠሪ፡- ወ/ሪት Eልፍነሽ ሸዋዬ - ጠበቃ ዳኜ ረዳ ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው Aቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ በውርስ ሃብት ክፍፍል ላይ ተመስርቶ የቀረበን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት በትግራይ ብ/ክ/መ/በምስራቃዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ከሳሽ የነበረችው የAሁንዋ ተጠሪ ስትሆን፣ ከAባትዋ በውርስ Aገኘሁ ያለችውን ንብረት Eንዲያካፍሉዋት በAሁንዋ Aመልካችና በልሎች ሁለት ሰዎች /Eህቶችዋ/ ላይ ክስ መስርታ ክርክሩ ተሰምቶAል። በመጨረሻም ተጠሪ ለክሱ ምክንያት ከሆነው ንብረት ላይ ድርሻዋን ትውሰድ ተብሎ ተወስኖAል። በልላ በኩል ደግሞ Aመልካች በተሰጠው ውሣኔ ላይ ባለመስማማት ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ Aቅርባ ክርክሩ በድጋሚ ከተሰማ በኋላ በከፍተኛው ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ፀንቶAል። ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aለበት ተብሎ Eንዲሻር በሚል ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት የቀረበው Aቤቱታም ተቀባይነት Aላገኘም። Aቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
ይህ የሰበር ችሎት Aመልካች ሐምል 12 ቀን 1999 ዓ.ም. በፃፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን Aስቀርቦ ክርክሩን ሰምቶAል። Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲታይ የተወሰነው Aመልካች ይርጋን መሰረት በማድረግ ያቀረበችውን መቃወሚያ ውድቅ የመሆኑን Aግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ በግራ ቀኝ ወገኖች ከቀረበው ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
ቀደም ሲል Eንደተገለፀው ክርክሩ የውርስ ንብረት ክፍፍል የሚመለከት ሆኖ ተጠሪ ያቀረበችው የድርሻዬን ይሰጠኝ ክስ የይርጋ መቃወሚያ ቀርቦበታል። የስር ፍ/ቤቶች በሰጡAቸው ውሣኔዎች ላይ Eንደተመለከተው የተጠሪ Aባት ማለትም የንብረቱ የቀድሞ ባለሃብት የሞቱት በ1976 ዓ.ም. ሲሆን፣ ተጠሪ የውርስ ንብረት ይገባኛል ክስ የመሰረተችው ደግሞ በ1996 ዓ.ም. ነው። ፍ/ቤቶቹ በAመልካች በኩል የቀረበውን የይርጋ ክርክር ውድቅ ያደረጉት ከሣሽ ክሱን ያቀረበችው በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1AAA/2/ የተመለከተው የ15 ዓመት የጊዜ ገድብ ከማለፉ በፊት ነው የሚል ምክንያት በመስጠት Eንደሆነም ተገንዝበናል።
Eንደምናየው የተጠሪ Aውራሽ በሞቱበት Eና ክሱ በቀረበበት ጊዜ መካከል ያሉት ዓመታት ሲቆጠሩ ከ2A ዓመት በላይ AልፎAል። ወራሽ የሆነው ሰው በልላ ሰው የተያዘበትን የውርስ ሃብት ለማስመለስ ክስ መመስረት Eንደሚችል በሕጉ የተመለከተ ቢሆንም፤ /የፍ/ብ/ሕግ ቁ. 999/ ክሱን የሚያቀርብበት ጊዜ ግን በሕግ ተወስኖAል። ከሣሹ መብቱንና የውርሱ ንብረቶች በተከሣሹ መያዛቸውን ካወቀ ሦስት ዓመት ካለፈ በኋላ ስለወራሽነት ጥያቄ የሚያቀርበው ክስ ተቀባይነት Eንደልለው በፍ/ብ/ብ/ሕግ ቁ. 1AAA/1/ ተመልክቶAል። በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ ይመለስልኝ የምትለው የውርስ ሃብት Aመልካች Eንድትመልስላት ክስ የመሰረተችው በAመልካች መያዙን ካወቀች የሦስት ዓመት ጊዜ ከማለፉ በፊት ነው የሚል በፍሬ ነገር ረገድ የቀረበ ክርክር የለም። ይልቁንም ተጠሪ ክሱን የመሰረተችው የሦስት ዓመት ጊዜ ካለፈ በኋላ Eንደሆነ ነው በሥር ፍ/ቤቶች ጭምር ግንዛቤ የተወሰደው። በዚህ ዓይነት ሁኔታ በሕጉ የተመለከተው የሦስት ዓመት የጊዜ ገደብ ካለፈ ደግሞ ወደ 15 ዓመት የሚኬድበት ምክንያት የለም። በፍ/ብ/ሕግ/ቁ. 1AAA/2/ የተመለከተው የ15 ዓመት የጊዜ ገደብ Aስፈላጊ የሚሆነው በንUስ ቁ. /1/ በተቀመጠው 275 276 ድንጋጌ መሰረት ለጉዳዩ Eልባት መስጠት የማይቻል ሆኖ በተገኘ ጊዜ ነው።
ሲጠቃለል ተጠሪ በAመልካች ላይ ያቀረበችው ክስ በሕጉ በተመለከተው የሦስት ዓመት የይርጋ ጊዜ ቀሪ ሆኖAል። በመሆኑም ክሱ በይርጋ ቀሪ Aልሆነም በሚል በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
Aቤቱታ የቀረበበት በትግራይ ብ/ክ/መ/ በምስራቃዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. A1155 በሕዳር 5 ቀን 1999 ዓ.ም.፣ በክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 18A17 መጋቢት 11 ቀን 1999 ዓ.ም. Eና በክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ/ቁ. 19639 ግንቦት 2 ቀን 1999 ዓ.ም. የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት }i[ªM::
No topics extracted.
ተጠሪ ያቀረበችው የውርስ ንብረት ይሰጠኝ ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኖAል ብለናል።
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ።
መዝገቡ ይመለስ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ
መጋቢት 18 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ታፈሰ ይርጋ መድኀን ኪሮስ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- የIትዮጵያ Eህል ንግድ ድርጅት ነ/ፈ ቀረበ።
ተጠሪ፡- Aቶ ግርማ ተገኝ ጠበቃ ቀርበዋል።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የጉዳዩ Aመጣጥ መጀመሪያ የAሁኑ ተጠሪ ከየካቲት ወር 1994 ዓ.ም.
ጀምሮ ለሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ስለተደረገላቸው ለEኔም ላደረግልኝ ይገባል በማለት ግንቦት 23 ቀን 1999 ዓ.ም. በተፃፈው ማመልከቻ ለፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ክስ ያቀርባሉ።
የAሁኑ Aመልካችም ከሥራ የተሰናበትከው በ1994 ዓ.ም. በመሆኑ የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄህ በይርጋ ይቋረጣል በማለት መቃወሚያ ያቀርባል።
ፍ/ቤቱም ይህን መቃወሚያ በመቀበል ክሱ በAዋጅ ቁጥር 337/96 Aንቀጽ 162/2/ መሰረት በይርጋ የሚቋረጥ ነው ሲል ክሱን በመሰረዝ መዝገቡን ዘግቶታል።
በመቀጠልም የAሁኑ ተጠሪ ለፍ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኝ ስላቀረቡ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በAዋጅ ቁጥር 337/96 Aንቀጽ 164/3/ መሰረት በይርጋው ተጠያቂ የሆነው ሰው ወይም ወገን የልላውን መብት በጽሑፍ ሲያውቅለት ተብሎ በተደነገገውን መሰረት ሲታይ በሕብረት ስምምነቱና በደመወዝ ስኬል Aፈፃፀም መመሪያው ሰራተኛው ከተጠያቂነት ነፃ መሆኑ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ የኋላ ቀሪ ክፍያ የሚያጠቃልል የደመወዝ ጭማሪ ላያገኝ ይችላል ተብሎ ስለተደነገገ ይህ ድንጋጌ የይርጋውን ጊዜ ያቋርጠዋል።
277 278 በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤት ክሱን በመቀበል ግራ ቀኙን Aከራክሮ የመሰለውን Eንዲወስን በማለት ይወስናል።
የሰበር Aቤቱታውም ላቀርብ የቻለው በዚሁ የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ነው። የሰበር Aመልካች ያቀረበው ቅሬታ ተጠሪው ያቀረቡት የተጨማሪ ደመወዝና የጥቅማጥቅም ጥያቄ በAዋጅ ቁጥር 337/96 Aንቀጽ 162 መሰረት በይርጋ ቀሪ የሚሆን በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ብንከራከርም የከፍተኛው ፍ/ቤት ይህን የመቃወሚያ ክርክራችንን ውድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤቱን ትEዛዝ በመሻር ክሱ በAዋጅ ቁጥር 337/96 Aንቀጽ 164/3/ መሰረት በይርጋ ቀሪ Aይሆንም በማለት መወሰኑ Aግባብ Aይደለም። ድርጅቱ ለተጠሪው ይርጋውን ለማቋረጥ የሚችል በጽሑፍ ያወቀለት መብት የለም። በሕብረት ስምምነቱና በደመወዝ ስኬል Aፈፃፀም መምርያውም ይህን የሚያረጋግጥ ድንጋጌ የለም። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቱ ውሣኔ ተሽሮ ክሱ በይርጋ ቀሪ የሚሆን ነው ተብሎ Eንዲወስንልን የሚል ነው።
ይህ የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም የሰበር Aቤቱታውን በመመርመር የስር ፍ/ቤት ክሱ በይርጋ Aይታገድም በማለት የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር Eንዲቻል Aቤቱታ¨< ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልሳቸውን Eንዲያቀርቡ Aዟል።
ተጠሪም ጥር 19 ቀን 2AAA ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት መልስ በሕብረት ስምምነታችን Aንቀጽ 32 Eና 34 መሰረት Eንዲሁም በድርጅቱ የደመወዝ ስኬል Aፈፃፀም መመሪያ ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ በሚሰራበትና በ1996 ዓ.ም.
በሥራ Aመራር ቦርዱ በተሻሻለው መመሪያ ቁጥር 6 Eና በቁጥር 3.3.10 መሰረት Aንድ ሰራተኛ በጥፋት ምክንያት በክርክር ላይ Eያለ የደመወዝ ጭማሪ መጠየቅ Eንደማይችል ነገር ግን ተጣርቶ ከጥፋቱ ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆኑ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ የደመወዝ ጭማሪውን ያለፈ ውዝፍ ክፍያም ጭምር ማግኘት Eንደሚችል ተደንግጓል። Eኔም የተሰናበትኩት በAግባቡ ያለመሆኑን ተረጋግጦ ስንብቱ ሕገወጥ ነው ተብሎ ስለተወሰነልኝ ውሣኔ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ስድስት ወር ሳይሞላ ነው ክሱን ያቀረብኩት በመሆኑም ክሱ በይርጋ Aይቋረጥም ተብሎ በፍ/ከ/ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ የሚነቀፍበት የሕግ ምክንያት ባለመኖሩ ውሣኔው Ãê“M˜ በማለት ተከራክረዋል።
Aመልካች ድርጅትም የመልስ መልሱን በማቅረብ ክርክሩን ለማጠናከር ሞክሯል።
በበኩላችን ደግሞ ክሱ በይርጋ ቀሪ ላሆን ይችላል ወይስ Aይችልም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን Eንደመረመርነውም ሐምል 199A ዓ.ም. በወጣው የሕብረት ስምምነት በAንቀጽ 34.2.7.4 የደመወዝ ጭማሪ በሚሰጥበት ወቅት በጥፋት ምክንያት በጊዜያዊ Eገዳ ላይ የሚገኝ ሰራተኛ በዚህ የሕብረት ስምምነት መሰረት የደመወዝ ጭማሪ ለማግኘት የAስተዳደር ውሣኔ የማያግደው ከሆነ ጭማሪውን ከተፈቀደበት ጊዜ ጀምሮ ያገኛል ተብሎ የተደነገገው የAስተዳደር ውሣኔው ላያግደው ይችላል ወይስ Aይችልም የሚለውን ቅድመ ሁኔታ ከተመለከቱ በኋላ የሚታይ Eንጂ በቀጥታ የደመወዝ ጭማሪን ለማግኘት በሚፈቅደው መንገድ Aይደለም።
በልላ በኩል ደግሞ ምንም Eንኳን በድርጅቱ የደመወዝ ስኬል የAፈፃፀም መመሪያ በAንቀጽ 3.3.1A በዲስፕላን ጉድለት ወይም በልላ ጥፋት ምክንያት በሕብረት ስምምነት ወይም በሥራ Aመራር Aባላት የAስተዳደር ደንብ መሰረት በቅጣት የሪከርድ የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞች የሪከርድ የጊዜ ገደቡ Eስኪያበቃ ድረስ የደመወዝ ጭማሪ Eንዳይሰጣቸው ተከልክለው የቆዩት ሰራተኞቹ ፈፀሙት የተባለው ድርጊት ተጣርቶ ከተጠያቂነት ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆናቸው ከተረጋገጠ ወይም የደመወዝ ጭማሪ Eንዳይሰጣቸው በAስተዳደር ውሣኔ ካልተወሰነ ከተጠያቂነት ነፃ መሆናቸው ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ ብቻ የኋላ ቀሪ ክፍያ” የማያጠቃልል የደመወዝ ጭማሪ ላያገኙ ይችላሉ ተብሎ ቢደነግግም ይህ ድንጋጌ የሚመለከተው ከድርጊታቸው ከተጠያቂነት ነፃ ከወጡ በኋላ በዚያው ድርጅት መሥራት የሚቀጥሉ Eንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ ሰኔ 9 ቀን 1991 ዓ.ም. ተሻሽሎ 279 280 በወጣው የደመወዝ Eስኬል Aፈፃፀም መመሪያ Aንቀጽ 2/ለ/ ስለተደነገገና ተጠሪው ደግሞ ይህን የደመወዝ ጭማሪ ክስ ከማቅረባቸው በፊት ጥር 28 ቀን 1996 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በሥራ ክር/መ/ቁ/4544 የተሰጠው ውሣኔ ተጠሪው ካሣ ተከፈሎAቸው ከድርጅቱ Eንዲሰናበቱ የተወሰነ በመሆኑ ተጨማሪ ደመወዙን የሚጠይቁበት የሕግ ምክንያት የለም።
በመሆኑም Eነዚህ ተጠሪው በሰበር መልሳቸው የጠቀሱዋቸውና የሥር ፍ/ቤትም ለውሣኔው መሰረት ያደረÒቸው የሕብረት ስምምነቱና የደመዝ ስኬል Aፈፃፃም መመሪያ Aንቀፆች ለተጠሪው መብት የሚሰጡ ባለመሆናቸው የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜውን ለማቋረጥ ምክንያት የሚሆኑበት መንገድ የለም። የሥር ፍ/ቤትም በሰጠው ውሣኔ ድርጅቱ ለከሣሹ /የAሁን ተጠሪ/ መብታቸው በጽሑፍ ያወቀላቸው በመሆኑ ክሱ በAዋጅ ቁጥር 337/96 Aንቀጽ 164/3/ መሰረት በይርጋ ቀሪ የሚሆንበት ምክንያት የለም በማለት የፍ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠውን ትEዛዝ uመሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀሙ ተረጋግጧል።
ው ሣ ኔ
ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 57A49 ሐምል 23 ቀን 1999 ዓ.ም. የተሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 24175 ግንቦት 23 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ ፀንቷል። ይፃፍ።
ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በAዋጅ ቁጥር 337/96 Aንቀጽ 162 መሰረት በይርጋ ቀሪ ሆኗል፤ ይፃፍ።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ።