No summary available.
ግንቦት 8 ቀን 1999 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ የሰ/መ/ቁ. 32A13 መጋቢት 25 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ መድኀን ኪሮስ Aመልካች፡- ደምስ ጥበበሥላሴ - ቀርቧል።
ተጠሪ፡- ቴዎድሮስ ጥበበሥላሴ - ወኪል ቀርባለች።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የውርስን ጥያቄ መነሻ ያደረገ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሣሽ የነበረው የAሁኑ ተጠሪ ነው። በAመልካች ላይ ክስ የመሰረተውም የሁለታችን Aባት የሆኑት Aባ ጥበበሥላሴ ካሣሁን ስለሞቱ ወራሽነቴ ተረጋግጧል። የውርስ ሀብቱ ግን ያልተከፋፈለ በመሆኑ የውርስ Aጣሪ ይሾምልን በማለት ነው። Aመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ ጥያቄው በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ተከራክፘል።
በመጨረሻም ፍ/ቤቱ ክርክሩን ከመረመረ በኋላ፣ ጥያቄው በይርጋ ቀሪ Aልሆነም በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሣኔው ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዟል።
የሰበር Aቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
Eኛም Aመልካች ሐምል 18 ቀን 1999 ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲታይ የተወሰነው Aመልካች ያነሳው የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ የተደረገው በሕግ Aግባብ ነው ወይ የሚለውን ነጥብ መመርመር ያለበት ሆኖ በመገኘቱ ነው። በዚህ መሰረትም ይህ ነጥብ፣ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
271 272 ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር መገንዘብ Eንደቻልነው Aመልካች የይርጋ መቃወሚያውን ያነሳው ተጠሪ ክሱን ያቀረበው Aባታችን ከሞቱ ከስምንት ዓመት በኋላ ነው። በልላ ሰው Eጅ ያለAግባብ ተይዞ የነበረውን የውርስ ሃብት ብቻዬን ተከራክሬ በማስለቀቅ ለስምንት ዓመት ሙሉ በይዞታዬ ሥር የያዝኩት በመሆኑ Aሁን Aካፍል ልባል Aይገባም በማለት ነው።
በEርግጥም ተጠሪ ክሱን ያቀረበው በAመልካች ክርክር የተነገረው ሁሉ ከተከናወነ በኋላ ስለመሆኑም Aልተካደም። የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተቃውሞውን ውድቅ ያደረገው የይርጋውን ድንጋጌ የያዘው የፍ/ብ/ሕግ ቁ.
1AAA ተገቢነት የሚኖረው የውርስ ሃብቱ የተያዘው ትክክለኛ ወራሽ ባልሆነ ሰው ሲሆን ነው። Aመልካች ግን /የስር ተከሣሽ/ ትክክለኛ ወራሽ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት Eንደሆነ ከውሣኔው ለመመልከት ችለናል።
Eንደምንመለከተው Aከራካሪው ጉዳይ ከውርስ ሃብት ክፍፍል ጋር የተያያዘ ነው። Aመልካች Eና ተጠሪ የAንድ Aባት ልጆች ናቸው። Eየተከራከሩ ያሉት Aባታቸው በተውት የውርስ ሃብት ላይ ነው። ስለ ውርስ ወይም Aወራረስን በተመለከተ ተገቢነት ያለው ሕግ በፍትሐብሕር ሕጉ በAንቀጽ Aምስት ሥር ያሉትን ድንጋጌዎች Aጠቃሎ የያዘው የሕጉ ክፍል ነው። በዚህ Aንቀጽ ሥር ያሉት ከቁጥር 826 Eስከ 1125 ድረስ ያሉት ድንጋጌዎች EንደየAግባቡ ከውርስ ጋር ተያይዘው ለሚነሱት ክርክሮች መፍቻ የሚውሉ ወይም Aግባብ’ƒ ያላቸው ናቸው። የፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1AAAም ከነዚሁ Aንዱ ነው። በመሆኑም Aግባብነቱ በወራሾች መካከል ለሚነሳው የይርጋ መቃወሚያ /ክርክር/ Eንደሆነ የሚያከራክር Aይደለም። Aግባብነት የማይኖረው የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ካለው በተቃራኒው፣ ማለትም Aንደኛው ተከራካሪ ወገን ወራሽ ባልሆነበት ጊዜ ነው። Eውነታው ይህ ከሆነ ደግሞ የስር ፍ/ቤቶች ለፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1AAA የሰጡት ትርጉም ትክክል Aይደለም ማለት ነው።
ልላው ለጉዳዩ Aወሳሰን Aግባብነት ያለው ድንጋጌ የፍ/ብ/ሕግ ቁ.
974/2/ ነው። ይህ ድንጋጌ ሟቹ ከሞቱ ከAምስት ዓመት በኋላ ስለውርስ ክፍያ Aመዳደብ ወይም ድልድል በማናቸውም Aስተያየት ቢሆን መቃወሚያ ማቅረብ Eንደማይቻል ያመለክታል። በያዝነው ጉዳይ Eንደምናየው Aመልካች በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 947 Eንደተደነገገው ያለ Aንዳች ፎርማላቲ የውርስ Aጣሪነት መብት Aለው። በዚህ መሰረትም የውርሱ ሃብት የሆነውን ንብረት ካለበት ፈልጎና ይዞት ከነበረው ሰው Aስለቅቆ በራሱ ይዞታ ስር Aድርጎታል። በዚህ Aይነት ሁኔታም ለስምንት ዓመት ያሕል ቆይቶAል። Aመልካች ንብረቱን የያዘው ለኔ የሚገባ የውርስ ሃብት ነው በሚል Eንደሆነ መገመት የሚያስቸግር Aይደለም። ተጠሪ ግን ይህ ንብረት ለኔም የሚገባ /የምወርሰው/ ሃብት ነው ወይም Aመልካች ብቻውን ላይዘው Aይገባም የሚል ጥያቄ ሳያነሳ ለ8 /ስምንት/ ዓመት ያክል ቆይቶAል። በመሆኑም የጊዜ ገደቡ ካለፈ በኋላ ያቀረበው የውርስ ሃብት ክፍፍል ጥያቄ በAምስት ዓመቱ ይርጋ ቀሪ ሆኖAል።
No topics extracted.
ሲጠቃለል የተጠሪ የውርስ ሃብት ክፍፍል ጥያቄ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1AAA/1/ በተመለከተው የሦስት ዓመትም ሆነ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 974/2/ uተቀመጠው የAምስት ዓመት የጊዜ ገደብ በይርጋ ቀሪ ሆኖAል። ስለዚህም Aቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
56847 ሰኔ 26 ቀን 1999 ዓ.ም. በሰጠው ትEዛዝ የፀናው ውሣኔ /ትEዛዝ/ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ ያቀረበው የውርስ ይጣራልኝ ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል ብለን ወስነናል።
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግን ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ። መዝገቡ ይመለስ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ