No summary available.
ግንቦት 14 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ Aሰግድ ጋሻው መድሕን ኪሮስ ዓላ መሐመድ በላቸው Aንሺሶ Aመልካች፡- ቴልኮሚኒኬሽን ኮርፖሬሽን ቀረቡ ተጠሪ፡- Aቶ ጫላ ሐሰን ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ክርክሩ የተጀመረው በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ መጀመርያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁኑ ተጠሪ ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ድርጅቱ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ያደረገውን የደመወዝ ጭማሪ በድምሩ ብር 4736፣ ከሐምል ወር 1998 ዓ.ም ጀምሮ የተደረገውን የደመወዝ ጭማሪ በድምሩ ብር 1132፣ ከሚያዝያ 1998 - ሰኔ 1998 ያልተከፈለኝ የትራንስፖርት Aበል ብር 3AA በድምሩ ብር 8159 ከወለድ ጭምር Eንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ክስ Aቅርበዋል።
የAሁኑ Aመልካች ደግሞ በሰጠው መልስ ከሣሽ ያቀረቡት የክፍያ ጥያቄ 6 ወር ያለፈበት በመሆኑ በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀፅ 162/3/ መሰረት በይርጋ ይታገዳል። ቦነሱና ልላው ጥቅማጥቅምን በተመለከተም ከሣሽ ክፍያው Eንዲከፈላቸው የጠየቁት በሥራ ላልነበሩበት ጊዜ በመሆኑ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም። በመሆኑም ክሱ ውድቅ ላሆን የሚገባው ነው በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ Aንድ ሰራተኛ ለስድስት ወር የሥራ ከሆነ ለበጀት ዓመቱ የተፈቀደውን ጭማሪና ቦነስ Eንደሚያገኝ በሕብረት ስምምነቱ የተደነገገ በመሆኑ ድርጅቱ በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ ለከሣሽ ይክፈል በማለት ወስኗል። በድርጅቱ ስለቀረበው የይርጋ ጥያቄ ግን ምንም ሣይል Aልፎታል።
ይግባኝ የቀረበለት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ Aካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከተመለከተ በኋላ ከሣሽ በልሉበትና ለኮርፖሬሽኑ Eድገትና ብልጽግና ያደረጉት AስተዋፅO ሣይኖር ላከፈላቸው የሚገባ የደመወዝ ጭማሪም ሆነ የቦነስ ክፍያ የለም። በ1998 ዓ.ም በጀት ዓመት የተደረገው የደመወዝ ጭማሪም ሆነ የቦነስ ክፍያ ላከፈላቸው Aይገባም። በልላ በኩል ግን ከሣሽ ከደርጅቱ ከመሰናበታቸው በፊት በ1997 ዓ.ም ለAሥራ Aንድ ወራት ያክል በድርጅቱ የሰሩ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት ድርጅቱ በዚሁ ዓመት ለልሎች ሰራተኞች የከፈለውን የደመወዝ ጭማሪና ጥቅማጥቅም ለከሣሽም Eንዲከፍል በማለት የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ ነው። በመሆኑም ድርጅቱ የ1997 ዓ.ም የደመወዝ ጭማሪና ቦነስ ለከሣሽ Eንዲከፍል በማለት የመ/ደ/ፍ/ቤቱን ውሣኔ በማሻሻል ወስኗል። በAመልካች ስለቀረበው የይርጋ ክርክር ደግሞ ምንም ሣይል Aልፎታል።
Aመልካች ያቀረበው የሰበር Aቤቱታም ይህን በጉራጌ ዞን የወልቂጤ Aካባቢ ከ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ ለማስለወጥ ሲሆን ቅሬታውም ፍ/ቤቱ የይርጋ ክርክሬን ወደጎን በመተው የ1997 ዓ.ም የደመወዝ ጭማሪና ቦነስ ለAሁን ተጠሪ Eንድከፍል የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aለበት' የ1997 ዓ.ም ክፍያ ተከፍሎ የተጠናቀቀው በጥቅምት ወር 1998 ዓ.ም ሲሆን ክሱ ደግሞ የቀረበው ጥቅምት 21 ቀን 1999 ዓ.ም ልክ በዓመቱ ነው ክሱ የስድስት ወር ጊዜ ሣያልፍ መቅረብ ሲገባው የቀረበው በዓመቱ በመሆኑ ጥያቄው በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀፅ 162/3/ መሰረት በይርጋ ቀሪ መሆን Aለበት። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ላሻር ይገባዋል የሚል ነው።
ተጠሪው ደገሞ በሰጡት መልስ በጊዜው ክስ ላቀርብ ያልቻልኩት ያለAግባብ ተሰናብቻለሁ። ወደሥራ ልመለስ ይገባል የሚል ክስ Aቅርቤ ስለነበረ ነው። ወደሥራ ከተመለስኩኝ በኋላም ክፍያው Eንዲከፈለኝ በተደጋገሚ ጥያቄ 265 266 Eያቀረብኩኝ ስለነበር ክሱ በይርጋ Aይታገድም። የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም። በመሆኑም ውሣኔው ላፀናልኝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
በበኩላችን ደግሞ ክሱ በይርጋ ቀሪ መሆን የሚገባው ነው ወይስ Aይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን Eንደመረመርነውም የ1997 ዓ.ም የደመወዝ ጭማሪ የተከፈለው ጥቅምት 1998 ዓ.ም በመሆኑና ክሱ ደግሞ የቀረበው በጥቅምት ወር 1999 ዓ.ም በመሆኑ ጥያቄው በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 162/3/ መሰረት በይርጋ ቀሪ መሆን ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል። በወቅቱ ክስ ልመሰርት ያልቻልኩት ወደሥራ ልመለስ የሚል ክስ Aቅርቤ ስለነበረ ነው በማለት ተጠሪ ያቀረቡት” ክርክር በተመለከተም ወደ ሥራ ልመለስ የሚለው ክስ የይርጋ ጊዜውን ላያቋርጥ የሚችል ባለመሆኑ ክርክሩ ተቀባይነት የለውም። ወደ ሥራ ከተመለስኩም ከግንቦት 15 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ Eንዲከፈለኝ Eጠይቅ ነበር ያሉትም ቢሆን በድርጅቱ ጥያቄው ተቀባይነት ያላገኘ በመሆኑ የይርጋ ጊዜውን የሚያቋርጥ Aይደለም። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶቹ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ሆኖ Eያለ የ1997 ዓ.ም የደመወዝ ጭማሪና ቦነስ ለተጠሪው Eንዲከፈል በማለት የሱጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትና መታረም የሚገባው መሆኑን ተገንዝበናል። የ1998 ዓ.ም Eና የ1999 ዓ.ም ክፍያን በተመለከተ ደግሞ ተጠሪው መስቀለኛ የሰበር Aቤቱታ ያቀረቡበት ባለመሆኑ Eንዲሁ መታለፍ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ 1- የጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ Aካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ.
A2327 ግንቦት 15 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የወልቂጤ ከተማ መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. AA7AA የካቲት 1 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
ይፃፍ።
2- የሥር ፍ/ቤቶች ክሱ በይርጋ ቀሪ ላሆን የሚገባው ነው በማለት መወሰን ሲገባቸው በቀረበው የይርጋ ጥያቄ ምንም ሣይሉ ማለፋቸውና ክፍያው Eንዲፈፀም በማለት የሰጡት ውሣኔ በAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 162/3/ ሥር የተደነገገውን የይርጋ ሕግ የሚጋፋ በመሆኑ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ወስነናል።
ይፃፍ።
3- ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ Eንዲቻቻሉ ብለን መዝገቡን ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ተ.ወ 267 268