No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 12 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ መድሕን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- የIትዮጵያ መድን ድርጅት ነ/ፈጅ ቀረቡ ተጠሪ፡- የIትዮጵያ ንግድ ባንክ ነ/ፈጅ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል
ይህ ጉዳይ በመድን ውል ላይ የተመሰረተን ይርጋ የሚመለከት ሲሆን የAሁን ተጠሪ በAዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በAሁን Aመልካችና በሥር 1ኛ Eና 2ኛ ተከሣሾች ላይ ባቀረበው ክስ 1ኛ ተከሣሽ በሚያዝያ 13 ቀን 1989 ዓ.ም በተፈረመ ውል ከከሣሽ ብር 3000 ሺህ ሲበደር በ2ኛ ተከሣሽ ስም የተመዘገበች መኪና በዋስትና Aስይዟል። በብድሩ ውል መሰረት 1ኛ ተከሣሽ Eዳውን Aጠናቆ ሳይከፍል በዋስትና የተያዘችው መኪና ጉዳት የደረሰባት ስለሆነና ከሣሽ በመድን ውሉ መሰረት 3ኛ ተከሣሽ ለ1ኛ ተከሣሽ ላከፍለው የሚገባው ገንዘብ ቅድሚያ መብት ስላለው 3ኛ ተከሣሽም ለመክፈል ፈቃደኛ ሆኖ ነገር ግን ዛሬ ነገ በማለት ክፍያውን ሳይፈጽም ስለቀረ ሦስቱም ተከሣሾች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ Eንዲከፍሉ ይወስንልን በማለት ጠይቋል።
የሥር 3ኛ ተከሣሽ የAሁን Aመልካችም ቀርቦ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባነሣው ክርክር በዋስትና ተይዛለች የተባለችው መኪና በAደጋ ጉዳት የደረሰባት በነሐሴ 2 ቀን 1988 ዓ.ም ሲሆን ክሱ የቀረበው መስከረም 24 ቀን 1997 ዓ.ም ነው። 3ኛ ተከሣሽ Eዳውን Aምኗል የተባለው ደግሞ የካቲት 11 ቀን 1989 ነው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ክሱ Eስከቀረበበት ድረስ ያለው ሲታሰብ 7 ዓመት ከ7 ወር ከ10 ቀን ነው። ይህም በንግድ ሕግ ቁጥር 674 ላይ Eንደተመለከተው ጉዳቱ በደረሰ በ2 ዓመት ጊዜ ወስጥ ክሱ መቅረብ ሲገባው Eንደዚሁ ተቋርጧል ቢባል ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት Aመት መቅረብ ሲኖርበት በዚህ ጊዜ ውስጥ ክሱ ያልቀረበ ስለሆነ በይርጋ ቀሪ ስለሚሆን ፍ/ቤቱ ክሱን ውድቅ ላያደርግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በዚህ ረገድ የቀረበውን ክርክር መርምሮ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1852/2/ መሰረት ይርጋ ከተቋረጠ በኋላ ድጋሚ የሚኖረው የይርጋ ጊዜ 10 ዓመት Eንደሆነ መገንዘብ የሚቻል በመሆኑና ይህ የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜም ከመጠናቀቁ በፊት ክሱ ስለቀረበ 3ኛ ተከሣሽ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ያቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተቀባይነት የለውም ካለ በኋላ ግራ ቀኙ በፍሬ ጉዳይ ረገድ ያቀረቡትን ክርክር ውሣኔ ሰጥቷል።
3ኛ ተከሣሽ የAሁን Aመልካች በዚህ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለOሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት Aቅርቦ ፍ/ቤቱም በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ ይርጋ ከተቋረጠ በኋላ ድጋሚ የይርጋ ጊዜ የሚታሰበው Aስቀድሞ በነበረው የይርጋ ጊዜ ልክ Eንደሆነ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 1852 ድንጋጌ መረዳት የሚቻል Eንደመሆኑ መጠን በዚህም ጉዳይ ይግባኝ ባይ Eዳውን Aምኗል ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ የ2 ዓመት የይርጋ ጊዜ ከሚታሰብ በስተቀር 10 Aመት ላሆን ስለማይችል ይርጋው ከተቋረጠም በኋላ በዚህ የሁለት Aመት ጊዜ መልስ ሰጪ ክሱን ያላቀረበ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት ክሱ በይርጋ ቀሪ Aልሆነም በማለት መቃወሚያውን ውድቅ ማድረጉ በAግባቡ Aይደለም ብሎ ይህንኑ የከፍተኛውን ፍ/ቤት ውሣኔ ሽሮ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የAሁን ተጠሪም በዚህ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት Aቅርቦ ጠቅላይ ፍ/ቤቱም በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር በይርጋ Aልተቋረጠም ሲል ዋናው ክርክር በOሮሚያ 261 262 ጠቅላይ ፍ/ቤት Eንዲታይ ብሎ ጉዳዩን ወደ Oሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት መልሷል።
የሰበር Aቤቱታው የቀረበው ይህንኑ ውሣኔ ለማስለወጥ ሲሆን ይህ ችሎትም Aቤቱታውን መርምሮ ጉዳዩ በንግድ ሕግ ቁጥር 674/1/ ላይ የተመለከተው የ2 ዓመት ጊዜ ተቋርጧል ከተባለ Aዲሱ የይርጋ ጊዜ የሚታሰበው በንግድ ሕግ መሰረት ወይንስ በፍትሐበሕር ሕግ የሚለው ተጣርቶ ላወሰን Eንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን የሰበር Aቤቱታው ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ Aኳያ Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
በIንሹራንስ ውል ላይ ተመስርቶ የሚቀርብ ማንኛውም ክስ ጉዳቱ በደረሰ በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ Eንዳለበት የIንሹራንስን ጉዳይ በተለይ በሚገዛው በንግድ ሕጉ በቁጥር 674/1/ ላይ ተመልክቷል። በልላ በኩልም በሕጉ ላይ የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ሲቋረጥ Eንደ Aዲስ ስለሚቆጠረው የይርጋ ጊዜ በንግድ ሕጉ ላይ Aልተመለከተም። ይህ ነጥብ በልዩ ሕጉ ማለትም በንግድ ሕጉ ካልተሸፈነ ወደ ጠቅላላ ሕግ መሄድ ከሕግ Aተረጓጐም መርህ Aኳያ ተቀባይነት ያለው ስለሆነ በዚሁ መሰረት ጠቅላላ ሕጉን መመልከት Aግባብነት ይኖረዋል። ለጉዳዩ Aግባብነት የሚኖረውም ድንጋጌ የፍ/ብ/ሕ/ቁ/1852 ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረትም ይርጋ በተቋረጠ ጊዜ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ Eንደገና Aዲስ የይርጋ ዘመን መቁጠር Eንደሚጀምር በዚሁ ድንጋጌ በንUስ ቁጥር /1/ ሥር ተመልክቷል።
No topics extracted.
ከዚህ ድንጋጌ በግልጽ መረዳት የሚቻለው ይርጋው በተቋረጠ ጊዜ ቀድሞ የነበረው የይርጋ ጊዜ Eንደ Aዲስ መቁጠር የሚጀምር መሆኑን ነው።
በEርግጥ በዚሁ ድንጋጌ በንUስ ቁጥር /2/ ሥር ይርጋው ተቋርጦ በሚገኝበት ጊዜ የይርጋ ዘመኑ Aቆጣጠር ሁልጊዜ 10 ዓመት Eንደሆነ ተመልክቷል። ይሁንና ይህ ድንጋጌ የሚገኘው ጠቅላላ የውሎች ሕግ በሚለው ክፍል ከመሆኑም በላይ ውልን Aስመልክቶ የሚቀርብ ክስ በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ Eንደሚሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 ላይ ስለተመለከተ ከዚሁ ከጠቅላላ ውል ጋር በተያያዘ ›”É የይርጋ ጊዜ ሲቋረጥ ልላ Aዲስ ¾10 Aመት የይርጋ ጊዜ ላኖር Eንደሚችል ከሚያስገነዝብ በስተቀር በልዩ ሕግ የይርጋ ጊዜው ከ10 ዓመት ዝቅ ብሎ የሚኘው ሁሉ ተቋርጦ በሚገኝበት ወቅት Aዲሱ የይርጋ ጊዜ 10 ዓመት ነው ማለት ሕግ Aውጪው ለተለያዩ ክሶች የተለያየ የይርጋ ጊዜ የሰጠውን Eንደመለወጥ የሚቆጠር ነው።
ስለሆነም የፍድራል ጠ/ፍ/ቤት ክሱ በይርጋ Aልተቋረጠም በማለት የሰጠው ውሣኔ ለድንጋጌው ተገቢውን ትርጉም ባለመስጠት ስለሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ