No summary available.
መ/ቁ. 2992A ጥቅምት 26 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የባህርዳር ጨ/ጨ/A/ማኀበር - ነ/ፈጅ ኃ/የሱስ ደምሴ - ቀረበ።
ተጠሪ፡- Aቶ Aመሸ ሰይድ - Aልቀረቡም።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው በባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት ከነበርኩበት የሥራ ደረጃ ያለAግባብ ዝቅ የተደረግሁ ስለሆነ በደረጃዬ Eንድመደብ ይወሰንልኝ የሚል ክስ የAሁን ተጠሪ በAሁን Aመልካች ላይ Aቅርቦ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን Aከራክሮ በAመልካች በኩል የቀረበን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ ተጠሪ የኋላ ክፍያ ሣይጠይቅ በጠየቀው የሥራ መደብ ተመድቦ Eንዲሰራ በማለት ውሣኔ ሰጥቶ በዚህ ውሣኔ ላይ ግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች ቅሬታ Aድሮባቸው በየበኩላቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለምዓራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት Aቅርበው ፍ/ቤቱም በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ ሁለቱም የይግባኝ መዝገቦች ተጣምረው Eንዲታዩ ትEዛዝ ከሰጠ በኋላ ተጠሪ ያቀረበውን ይግባኝ በተመለከተ የወረዳውን ፍ/ቤት ውሣኔ Aሻሽሎ ይ/ባይ በደረጃ 9 ከተመደበበት ቀን ጀምሮ ያለውን ክፍያ መ/ሰጭ ላከፍለው ይገባል የሚል ውሣኔ በመስጠቱና Aመልካች በበኩሉ ያቀረበው የይግባኝ ቅሬታ ምንም ሣይባል በመታለፉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ቅሬታ በማቅረቡ ነው።
ይህ ሰበር ሰሚ ችሎትም የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ ተጠሪ ቀደም ሲል ክሱን ለወረዳ ፍ/ቤት Aቅርቦ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን ያለው የAሰሪና ሰራተኛ ወሣኝ ቦርድ ነው በማለቱ ክሱን ለAሰሪና ሰራተኛ ወሣኝ ቦርድ Aቅርቦ ጉዳዩ Eስከ ፍድራል ሰበር ሰሚ ችሎት ደርሶ ቦርዱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለውም ተብሎ ከተወሰነ በኋላ ተጠሪ በድጋሚ ክሱን ለወረዳ ፍ/ቤት ሲያቀርብ Aመልካች ያነሣው የይርጋ ክርክር ተቀባይነት ሣያገኝ መቅረቱ ተጠሪ ባለበት ተጣርቶ ላወሰን Eንደሚገባ በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ምላሽ ማግኘት የሚገባው ጭብጥ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል ወይንስ Aልሆነም? የሚለው በመሆኑ ይህንኑ ጭብጥ ይዘን ከሕጉ Aኳያ Eንደሚከተለው መርምረናል።
ተጠሪ ከላይ የተመለከተውን ክስ ለባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት ሲያቀርብ Aመልካች ለክሱ ምክንያት የሆነው ነገር የተፈፀመው በ1994 ዓ.ም ሲሆን ክሱ ግን የቀረበው በ1998 ዓ.ም ከ4 ዓመት በኋላ ስለሆነ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት የመጀመያ ደረጃ መቃወሚያ Aቅርቧል። የወረዳው ፍ/ቤትም ጉደዩ ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ክርክሩ የግል የሥራ ክርክር Eንጂ የወል የሥራ ክርክር ስላልሆነ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን Aይቶ ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን Aለው በማለት ውሣኔ የሰጠ ስለሆነ መቃወሚያው በAግባቡ Aልቀረበም በማለት ሣይቀበለው ቀርቷል።
ከሣሽ የሆነ ወገን ክሱን ለፍ/ቤት ከማቅረቡ በፊት የትኛው ፍ/ቤት ክሱን ለማየት የግዛትና የሥረ ነገር ሥልጣን Eንዳለው Aጣርቶ ማቅረብ Eንዳለበት ይታመናል። በዚሁ መሰረትም ተጠሪ ክሱን በቅድሚያ ለባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት Aቅርቦ ነበር። ሆኖም ፍ/ቤቱ ጉደዩን ለማየት የሥረ ነገር ሥልጣን የለኝም ሲል ከሣሹ/ተጠሪ/ የመረጠው ይግባኝ ማለትን ሣይሆን ክሱን ለAሰሪና ሰራተኛ ወሣኝ ቦርድ ማቅረብን በመሆኑ በዚሁ መሰረት ክሱን ለቦርዱ Aቅረቦ ክርክሩ ቀጥሎ መጨረሻ ጉዳዩ ለፍድራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ችሎቱም የዚህ ዓይነት ክርክር በወል የሥ^ ክርክር ላሸፈን ስለማይችል ቦርዱ ይህን ጉዳይ ተመልክቶ ውሣኔ የሰጠው ሥልጣን ሣይኖረው ነው በማለት የበኩሉን ውሣኔ ሰጥቷል።
257 258 ከዚህ በኋላ ተጠሪ ክሱን Kባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት ሲያቀርብ ክሱ በይርጋ ቀሪ መሆኑን በመግለጽ Aመልካች የይርጋ መቃወሚያ Aቅርቧል።
ከሥራ ክርክር ጋር በተያያዘ የሚቀርብ ክስ የይርጋ ጊዜ ከፍተኛው 1 ዓመት Eንደሆነ በAሰሪና ሰራተኛ A/ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 162 ላይ የተመለከተ ሲሆን ይህ የይርጋ ጊዜ ከማለፉ በፊት ተጠሪ በቅድሚያ ክሱን ለወረዳ ፍ/ቤት Aቅርቦ ነበር። ሆኖም ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለኝም በማለት ክሱን ሣይቀበል ሲቀር ክርክሩ የግል የሥራ ክርክር ከመሆኑ Aኳያ በይግባኝ ሥነ ሥርዓት በመጠቀም ይህንኑ ውሣኔ ተጠሪ ማስለወጥ ሲገባው ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን ለልለው ለAሰሪና ሰራተኛ Ñ<ÇÃ ወdኝ ቦርድ ክሱን ማቅረብ Aልነበረበትም።
የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በመ/ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ ከAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንፃር ይህንን ጉዳይ ለማየት የሥረ - ነገር ሥልጣን የለውም በማለት ውሣኔ ከመስጠቱ በስተቀር Aስቀድሞ ክርክሩ በተጀመረበት በባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት ክርክሩ ይቀጥል በማለት ውሣኔ Aልሰጠም።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
ስለሆነም ለባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት ድጋሚ ክስ ሲቀርብ በሕጉ ላይ የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ካለፈ ከ4 ዓመት በኋላ ቀርቦ ባለበት ሁኔታ ፍ/ቤቱ የይርጋ መቃወሚያውን ላቀበለው ሲገባ ውድቅ ማድረጉ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
Aመልካች በዚሁ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮበት የይግባኝ ቅሬታው” ለምEራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት Aቅርቦ ፍ/ቤቱ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች ያቀረቡት ይግባኝ ተጣምሮ Eንደሚታይ ትEዛዝ የሰጠ ቢሆንም በተጠሪ በኩል የቀረበውን ይግባኝ መርምሮ ከመወሰኑ በስተቀር የAመልካችን የይግባኝ ቅሬታ ሣይመለከተው Aልፎታል።
ዳኝነት የተጠየቀበት ነገር ተቀባይነት ሣያገኝ የታለፈ Eንደሆነ Eንደተከለከለ Eንደሚቆጠር በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 5(3) ላይ የተመለከተ ስለሆነ በዚህም ጉዳይ ይርጋን Aስመልክቶ Aመልካች ለምEራብ ጎጀም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበው ቅሬታ ስለታለፈ Eንደተከለከለ የሚቆጠር ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት ይህን ጉዳይ Aስመልክቶ ሐምል 17 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ Eንደዚሁም የምEራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም በዚሁ ጉዳይ መጋቢት 24 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ በAመልካች ላይ ክc< ያቀረበው በሕጉ ላይ የተቀመጠው ጊዜ ካለፈ በኋላ ስለሆነ ክc< በይርጋ ቀሪ ሆኗል ተብሎ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።