No summary available.
ጥቅምት 28 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድ መሐመድ ሐጐስ ወልዱ መስፍን Eቁበዮናስ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ Aመነው Aመልካች፣ ወ/ሮ ስንልሽ ማዘንጊያ - ጠበቃ ቀረበ ተጠሪ፣ Eነ Aቶ ተስፋ ማዘንጊያ - ቀርበዋል መዝገቡን መርምረን የሚተለውን ፍርድ ሰጥተናል፣
በዚህ ጉዳይ የAሁኖቹ ተጠሪዎች በAመልካች ላይ ኅዳር 20 ቀን 1998 ዓ.ም ባቀረቡት ክስ፣የAሁኗ Aመልካች ግምቱ ብር 190,850 (የAንድ መቶ ዘጠና ሺ ስምንት መቶ ሃምሳ) የሆነና ከAውራሻችን ከወ/ሮ የንጉሤ ማዘንጊያ የሚደርሰንን የውርስ ንብረት የያዘች ስለሆነ የውርስ ንብረት ታካፍለን የሚል ነው። የAሁን Aመልካች ለክሱ ከሰጠችው መልሶች መካከል፣Aሁን የተጠየቀውን የውርስ ንብረት ወራሽ መሆኔ በፍ/ቤት ተረጋግጦ ላለፉት 10 ዓመታት በEጄ የቆየ ስለሆነ ተጠሪዎች በይርጋ ቀሪ የሆነን ጉዳይ Aንስተው ላጠይቁኝ Aይገባም የሚል ይገኝበታል። Aቤቱታ የቀረበለት የሰሜን ጎንደር መስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የAሁኗን Aመልካች የይርጋ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የውርስ ንብረቱን ከሳሽና ተከሳሾች Eኩል ይካፈሉ ብሐል። ጉዳዩን በይግባኝ የቀረበለት የA/ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኙን በፍ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.
337 ውድቅ በማድረግ መዝገቡን ዘግቶታል።
የሰበር Aቤቱታው በዚህ ላይ የቀረበ ሲሆን ፣ይህ ችሎት የካቲት 13 ቀን 1999 በዋለው ችሎት የሥር ፍ/ቤት የይርጋ ጥያቄውን ያለፈው በAግባቡ መሆን Aለመሆኑን ለመመርመር ሲባል መዝገቡ ለሰበር Eንዲቀርብ ትEዛዝ ሰጥቶ የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ሰኔ 26 ቀን 1999 ሰምቷል።
በዚህ ጉዳይ የሥር ፍ/ቤት የይርጋው” ጥያቄ ውድቅ ያደረገበት ዋ’ኛ ምክንያት የAሁኗ Aመልካች ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን የውርስ ንብረቶች የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1000 /2/ በሚደነግገው መሰረት ከ15 ዓመት በላይ በይዞታዋ ስር ስላላደረገች ክሱ በይርጋ ቀሪ Aይሆንም በሚል ነው።
በመሰረቱ Aውራሽ የተባሉት ወ/ሮ ¾ንጉሤ ማዘንጊያ መጋቢት 7 ቀን 1988 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ መሆኑ ታውቋል። የAሁኗ Aመልካች ግንቦት 15 ቀን 1989 ዓ.ም የሟች ሕጋዊ ወራሽ መሆኗ ተረጋግጦ ንብረቱን ይዛ ስትገለገልበት ስለመቆየቷም ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ መረዳት ተችሐል።
የAሁኖቹ ተጠሪዎች ደግሞ በዚሁ ከተማ Eየኖሩ ላለፉት 10 ዓመታት በተከሳሽ የተያዙትን የውርስ ንብረቶች ሳይጠይቁ መቆየታቸው ታውቋል።
በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1000 /1/ መሰረት ከሳሽ መብቱንና የውርስ ንብረቶች በተከሳሹ መያዛቸውን ካወቀ ሦስት ዓመት በኋላ ስለወራሽነት ጥያቄ የሚቀርበው ክስ ተቀባይነት ለማግኘት Aይችልም በሚል ተደንግጓል። የሥር ፍ/ቤት ይህን መሰረታዊ የይርጋ ሕግ ወደ ጐን በመተው ግራ ቀኙ Eየተከራከሩበት ያለው የውርስ ንብረት ከዘር የወረደ ርስት Eንደሆነ በመቁጠር ለጉዳዩ Aግባብ ያልሆ’ ሕግ ጠቅሶ የይርጋ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ መሰታዊ የሕግ ስህተት ነው ብለናል።
ው ሣ ኔ
የተጠሪዎች የውርስ ንብረት ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ሆኗል ብለናል፣
የA/ብ/ክ/መ የሰሜን ጎንደር መ/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሰኔ 15 ቀን 1998 በሆነ መዝገብ የሰጠው ውሳኔ Eና የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 09867 በሐም 17 1998 ዓ.ም የሰ×D†¨< ትEዛሁች ተሽረዋል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ፣
መዝገቡ ያለቀለት ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፣ የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ቤ/ኃ249 250
ኅዳር 24 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡ መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጐስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ- ነ/ፈጅ Aቶ ዓለሙ Iብሳ ተጠሪ፡- Aቶ ግዛው መንጀታ - ጠበቃ Aቶ ማርቆስ ወ/ሰንበት መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
No topics extracted.
በዚህ ጉዳይ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው Aመልካች በፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ በወረዳ 5 ቀበል 07 ክልል ቁጥር 1354 የሆነውን ቤት ጥቅምት 1 ቀን 1977 ዓ.ም በተፈረመ ውል ለመኖሪያ Aገልግሎት ተከራይቶ የነበረ ሲሆን ያለ Aከራዩ ፈቃድ ወደ ምግብ ቤት በመለወጥ የንግድ ሥራ Eየሰራበት ስለሚገኝ የኪራይ ውል ተሰርዞ ቤቱን Eንዲያስረክብ በማለት ጠይቆ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን Aከራክሮ ተከሳሽ ለመኖሪያነት የተከራዮትን ቤት ወደ ንግድ ቤት መቀየራቸውን ከሳሽ ያወቀው በ1979 ዓ.ም ሲሆን ክሱን በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ ማቅረብ ሲገባው ጊዜው ካለፈ በኋላ ያቀረበ ስለሆነ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ውሳኔ በመስጠቱና ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/337 መሰረት ይግባኙን በመሰረዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት Aመልካች ቅሬታ በማቅረቡ ነው።
ይህ ሰበር ችሎቱም በAመልካች በኩል የቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተጠሪ ባለበት ተጣርቶ ላወሰን Eንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል; የሚለው በመሆኑ ከሕጉ ጋር ተገናዝቦ ተመርምሯል።
ውል ባለመፈጸሙ ምክንያት Eንዲፈጸም በመጠየቅ ወይም በውል Aለመፈጸም ምክንያት የጉዳት ኪሣራ በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ ወይንም Eንዲሰረዝ በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ በ10 ዓመት የጊዜ ግደብ ካልቀረበ በይርጋ ቀሪ Eንደሚሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 1845 ላይ የመለከተ ሲሆን የይርጋው ጊዜ መቆጠር የሚጀምረውም ግድታውን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነው ወይም ውሉ የሚሰጠው መብት ከተሰራበት ቀን ጀምሮ Eንደሆነ በቁጥር 1846 ላይ ተመልክቷል።
በተያዘው ጉዳይ Aመልካች በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተው ለመኖሪያ ቤት የተከራየውን ቤት ወደ ንግድ ቤትነት የቀየረ ስለሆነና ይህም ውሉን መጣስ ስለሆነ ውሉ በፍርድ ተሰርዞ ቤቱን Aንድረከብ ይወሰንልኝ በማለት Eንደመሆኑ መጠን የውል መጣስ ተግባሩ በዚህ ቀን ተጀምሮ በዚህ ቀን ቆሟል ለማለት ከውሉ ባህሪይ Aኳያ የማይቻል ከመሆኑም በላይ Aሁንም Eየቀጠለ ያለ ተግባር በመሆኑ በEንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1846 መሰረት በማናቸውም ጊዜ ግድታውን ለመጠየቅ ተገቢ ስለሚሆን ተጠሪ የመኖሪያ ቤቱን ወደ ንግድ ቤት ከቀየሩበት ጊዜ ጀምሮ 10 ዓመት በመቁጠር የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ሳይቀበለው መቅረቱና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህንኑ ማጽናቱ ከውሉ ባህርይም ሆነ ከሕጉ ጋር ያልተገናዘበ ሆኖ ተገኝቷል።
ስለሆነም ቀጥሎ የተመለከተው ተወስኗል።
251 252
የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ. መጋቢት 1 ቀን 1998 ዓ.ም Eንዲሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ኅዳር 29 ቀን 1999ዓ.ም Aመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ¾c×D†¨< ¨<d’@−‹ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመv†¨< ስለሆ’< በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 348 (1) መሰረት ተሽረዋል።
Aመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ያልሆነ ስለሆነ የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ግራ ቀኙ በፍሬ ጉዳይ ረገድ ያቀረቡትን ክርክር መርምሮ የበኩሉን ውሳኔ Eንዲሰጥ በፍ.ብ.ሕ.ሥ.ሥ.ቁ 341 መሰት ተመልሶለታል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተገዝቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ የሰ/መ/l. 28997 ታህሳስ 1 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጐስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ስለAሶሳ ዞን ግብርና Eና ትምህርት መምሪያዎች የቤኒሻንጉል ጐምዝ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ፣ ተጠሪ፡-
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ፍ ር ድ፡ጉዳዩ ይዞታዬ በተከሣሾች በመወሰዱ በላዩ ላይ (በመሬቱ ላይ) የነበሩትን ልዩ ልዩ ተክሎች ግምት በካሣ መልክ ይክፈለኝ በሚል ተጠሪ በመሰረተው ክስ መነሻነት የተጀመረውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በቤኒሻንጉል ብ/ክ/መ በAሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን ፍ/ቤቱ ከሣሽና ተከሣሾች ያቀረቡትን ክርክር ከሰማ በኋላ ተከሣሾች ብር 148,600 (መቶ Aርባ ስምንት ሺ ስድስት መቶ) ለከሣሽ ይክፈሉ ሲል ወስኗል። በልላ በኩል ደግሞ የሥር ተከሣሾች ውሣኔውን በመቃወም ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ በማለታቸው ክርክሩ በድጋሚ ተሰምቶAል። በመጨረሻም ፍ/ቤቱ የኃላፊነቱን መጠን ብቻ በማሻሻል ብር 75,000 (ሰባ Aምስት ሺህ) Eንዲከፈል በAብላጫ ድምጽ ወስኗል። Aቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
Eኛም Aመልካች የሥር ተከሣሾችን በመወከል የካቲት 9 ቀን 99 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪውን Aስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲታይ የተወሰነው የሥር ተከሣሾች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረቡት የይርጋ ክርክር የመታለñን Aግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምናል።
ከመዝገቡ መገንዘብ Eንደቻልነው ተጠሪ ላቀረበው የካሣ ጥያቄ መነሻ የሆነው መሬት ተወሰደ የተባለው በ1984 ዓ.ም ሆኖ ተጠሪ የካሣ ይከፈለኝ ክሱን ለፍ/ቤት ያቀረበው ደግሞ በ1998 ዓ.ም ነው። Aመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበውም ከውል ውጭ የደረሰን ኃላፊነት መሰረት በማድረግ የቀረበው የካሣ ክፍያ ጥያቄ በፍ/ብ/ ሕግ ቁ 2143 መሰረት በሁለት ዓመት ይርጋ ቀሪ ሆኖAል በማለት ነው። የሥር ፍ/ቤቶችም ጉዳቱ ደረሰ የተባለበትን ጊዜ Eና ክሱ የቀረበበትን ጊዜ በማስመልከት የቀረበው የፍሬ ነገር ክርክር ትክክል መሆኑን ግንዛቤ ወስደዋል። የAመልካችን የይርጋ ክርክር ውድቅ ያደረጉትም ክርክሩን በማስረጃ Aላስደገñም በማለት ሳይሆን፣ ተጠሪ ክሱን ከመመስረቱ በፊት ለከተማው ማዘጋጃ ቤት ጥያቄ Aቅርቦ ስለነበር የይርጋው Aቆጣጠር በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1851 በተደነገገው መሰረት ተቋርጦOል የሚል ምክንያት በመስጠት ነው።
Eንደምንመለከተው ተጠሪ ከ1998 ዓ.ም ዓ.ም በፊት በየትኛውም ፍ/ቤት ክስ Aልመሰረተም። ይህም ማለት በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1851(ለ) Eንደተመለከተው መብቱ Eንዲታወቅለት በፍ/ቤት ክስ Aቅርቦ ካሣ ላከõK<ኝ ይገባል ለሚላቸው ሰዎች (Aካላት) Aስታውቆ Aልተገኘም። ተከሣሾችም ቢሆኑ Eዳውን Aምነው ተገኝተዋል Aልተባለም። Eነዚህ በሕጉ የተመለከቱት ሁኔታዎች ተሟልተው ባልተገኙበት ጊዜ በሕጉ የተቀመጠው የይርጋ Aቆጣጠር ተቋርጦAል ለማለት የሚቻል Aይደለም። ተጠሪ መሬቱን ወስዷል ወይም Aስወስዷል ላለው የከተማው ማዘጋጃ ቤት ጥያቄ Aቅርቦ ላሆን ይችላል። ይህ ግን የይርጋ ማቋረጫ ሁኔታ ተደርጎ በሕጉ የተቀመጠ ባለመሆኑ ተጠሪ መከራከሪያ ላያደርገው Aይችልም። የሥር ፍ/ቤቶችም ይህንኑ መከራከሪያ በመቀበል መወሰናቸው ትክክል Aይደለም። በመሆኑም Aቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
Aቤቱታ የቀረበባቸው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ብ/ክ/መ/የAሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ 1359 ሐምል 21 ቀን 98 ዓ.ም የሰጠውና የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.916 ጥር 21 ቀን 99 ዓ.ም በAብላጫ ድምጽ የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ሕግ ቁ. 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪ ያቀረበው ¾"X ØÁo በይርጋ ቀሪ ሆኖAል ብለናል።
ወጭና ኪሣራ ግራቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ። መዝገቡ ይመለስ።
የማይነበብ የAምስት የዳኞች ፊርማ Aለበት ነ/ዓ 255 256 የሰበር መ/ቁ. 2992A ጥቅምት 26 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የባህርዳር ጨ/ጨ/A/ማኀበር - ነ/ፈጅ ኃ/የሱስ ደምሴ - ቀረበ።
ተጠሪ፡- Aቶ Aመሸ ሰይድ - Aልቀረቡም።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው በባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት ከነበርኩበት የሥራ ደረጃ ያለAግባብ ዝቅ የተደረግሁ ስለሆነ በደረጃዬ Eንድመደብ ይወሰንልኝ የሚል ክስ የAሁን ተጠሪ በAሁን Aመልካች ላይ Aቅርቦ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን Aከራክሮ በAመልካች በኩል የቀረበን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ ተጠሪ የኋላ ክፍያ ሣይጠይቅ በጠየቀው የሥራ መደብ ተመድቦ Eንዲሰራ በማለት ውሣኔ ሰጥቶ በዚህ ውሣኔ ላይ ግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች ቅሬታ Aድሮባቸው በየበኩላቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለምዓራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት Aቅርበው ፍ/ቤቱም በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ ሁለቱም የይግባኝ መዝገቦች ተጣምረው Eንዲታዩ ትEዛዝ ከሰጠ በኋላ ተጠሪ ያቀረበውን ይግባኝ በተመለከተ የወረዳውን ፍ/ቤት ውሣኔ Aሻሽሎ ይ/ባይ በደረጃ 9 ከተመደበበት ቀን ጀምሮ ያለውን ክፍያ መ/ሰጭ ላከፍለው ይገባል የሚል ውሣኔ በመስጠቱና Aመልካች በበኩሉ ያቀረበው የይግባኝ ቅሬታ ምንም ሣይባል በመታለፉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ቅሬታ በማቅረቡ ነው።
ይህ ሰበር ሰሚ ችሎትም የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ ተጠሪ ቀደም ሲል ክሱን ለወረዳ ፍ/ቤት Aቅርቦ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን ያለው የAሰሪና ሰራተኛ ወሣኝ ቦርድ ነው በማለቱ ክሱን ለAሰሪና ሰራተኛ ወሣኝ ቦርድ Aቅርቦ ጉዳዩ Eስከ ፍድራል ሰበር ሰሚ ችሎት ደርሶ ቦርዱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለውም ተብሎ ከተወሰነ በኋላ ተጠሪ በድጋሚ ክሱን ለወረዳ ፍ/ቤት ሲያቀርብ Aመልካች ያነሣው የይርጋ ክርክር ተቀባይነት ሣያገኝ መቅረቱ ተጠሪ ባለበት ተጣርቶ ላወሰን Eንደሚገባ በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ምላሽ ማግኘት የሚገባው ጭብጥ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል ወይንስ Aልሆነም? የሚለው በመሆኑ ይህንኑ ጭብጥ ይዘን ከሕጉ Aኳያ Eንደሚከተለው መርምረናል።
ተጠሪ ከላይ የተመለከተውን ክስ ለባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት ሲያቀርብ Aመልካች ለክሱ ምክንያት የሆነው ነገር የተፈፀመው በ1994 ዓ.ም ሲሆን ክሱ ግን የቀረበው በ1998 ዓ.ም ከ4 ዓመት በኋላ ስለሆነ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት የመጀመያ ደረጃ መቃወሚያ Aቅርቧል። የወረዳው ፍ/ቤትም ጉደዩ ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ክርክሩ የግል የሥራ ክርክር Eንጂ የወል የሥራ ክርክር ስላልሆነ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን Aይቶ ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን Aለው በማለት ውሣኔ የሰጠ ስለሆነ መቃወሚያው በAግባቡ Aልቀረበም በማለት ሣይቀበለው ቀርቷል።
ከሣሽ የሆነ ወገን ክሱን ለፍ/ቤት ከማቅረቡ በፊት የትኛው ፍ/ቤት ክሱን ለማየት የግዛትና የሥረ ነገር ሥልጣን Eንዳለው Aጣርቶ ማቅረብ Eንዳለበት ይታመናል። በዚሁ መሰረትም ተጠሪ ክሱን በቅድሚያ ለባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት Aቅርቦ ነበር። ሆኖም ፍ/ቤቱ ጉደዩን ለማየት የሥረ ነገር ሥልጣን የለኝም ሲል ከሣሹ/ተጠሪ/ የመረጠው ይግባኝ ማለትን ሣይሆን ክሱን ለAሰሪና ሰራተኛ ወሣኝ ቦርድ ማቅረብን በመሆኑ በዚሁ መሰረት ክሱን ለቦርዱ Aቅረቦ ክርክሩ ቀጥሎ መጨረሻ ጉዳዩ ለፍድራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ችሎቱም የዚህ ዓይነት ክርክር በወል የሥ^ ክርክር ላሸፈን ስለማይችል ቦርዱ ይህን ጉዳይ ተመልክቶ ውሣኔ የሰጠው ሥልጣን ሣይኖረው ነው በማለት የበኩሉን ውሣኔ ሰጥቷል።
257 258 ከዚህ በኋላ ተጠሪ ክሱን Kባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት ሲያቀርብ ክሱ በይርጋ ቀሪ መሆኑን በመግለጽ Aመልካች የይርጋ መቃወሚያ Aቅርቧል።
ከሥራ ክርክር ጋር በተያያዘ የሚቀርብ ክስ የይርጋ ጊዜ ከፍተኛው 1 ዓመት Eንደሆነ በAሰሪና ሰራተኛ A/ቁጥር 377/96 Aንቀጽ 162 ላይ የተመለከተ ሲሆን ይህ የይርጋ ጊዜ ከማለፉ በፊት ተጠሪ በቅድሚያ ክሱን ለወረዳ ፍ/ቤት Aቅርቦ ነበር። ሆኖም ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለኝም በማለት ክሱን ሣይቀበል ሲቀር ክርክሩ የግል የሥራ ክርክር ከመሆኑ Aኳያ በይግባኝ ሥነ ሥርዓት በመጠቀም ይህንኑ ውሣኔ ተጠሪ ማስለወጥ ሲገባው ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን ለልለው ለAሰሪና ሰራተኛ Ñ<ÇÃ ወdኝ ቦርድ ክሱን ማቅረብ Aልነበረበትም።
የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በመ/ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ ከAዋጅ ቁጥር 377/96 Aንፃር ይህንን ጉዳይ ለማየት የሥረ - ነገር ሥልጣን የለውም በማለት ውሣኔ ከመስጠቱ በስተቀር Aስቀድሞ ክርክሩ በተጀመረበት በባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት ክርክሩ ይቀጥል በማለት ውሣኔ Aልሰጠም።
ስለሆነም ለባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት ድጋሚ ክስ ሲቀርብ በሕጉ ላይ የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ካለፈ ከ4 ዓመት በኋላ ቀርቦ ባለበት ሁኔታ ፍ/ቤቱ የይርጋ መቃወሚያውን ላቀበለው ሲገባ ውድቅ ማድረጉ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
Aመልካች በዚሁ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮበት የይግባኝ ቅሬታው” ለምEራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት Aቅርቦ ፍ/ቤቱ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች ያቀረቡት ይግባኝ ተጣምሮ Eንደሚታይ ትEዛዝ የሰጠ ቢሆንም በተጠሪ በኩል የቀረበውን ይግባኝ መርምሮ ከመወሰኑ በስተቀር የAመልካችን የይግባኝ ቅሬታ ሣይመለከተው Aልፎታል።
ዳኝነት የተጠየቀበት ነገር ተቀባይነት ሣያገኝ የታለፈ Eንደሆነ Eንደተከለከለ Eንደሚቆጠር በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 5(3) ላይ የተመለከተ ስለሆነ በዚህም ጉዳይ ይርጋን Aስመልክቶ Aመልካች ለምEራብ ጎጀም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበው ቅሬታ ስለታለፈ Eንደተከለከለ የሚቆጠር ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የባህርዳር ወረዳ ፍ/ቤት ይህን ጉዳይ Aስመልክቶ ሐምል 17 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ Eንደዚሁም የምEራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም በዚሁ ጉዳይ መጋቢት 24 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ በAመልካች ላይ ክc< ያቀረበው በሕጉ ላይ የተቀመጠው ጊዜ ካለፈ በኋላ ስለሆነ ክc< በይርጋ ቀሪ ሆኗል ተብሎ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።