No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 07 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ተገኔ ጌታነህ መድኅን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- Aቶ ተገኝ ይማም Aልቀረቡም ተጠሪዎች፡- Eነ Aቶ ካሣሁን ደሳለኝ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ክርክሩ የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን ተጠሪዎች ነሐሴ 7 ቀን 1996 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ Eህታችን ወ/ሮ ያልጋ ደሳለኝ Eና Aቶ ተገኝ ይማም ተጋብተው Eየኖሩ ሳሉ Eህታችን ጥቅምት 11 ቀን 1982 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለየች Aብረው የሰሩትን ቤትና Aብረው ያፈሩትን ልላ ንብረት ለEኛው ለሟች ወራሾች ግማሹን Eንዲሰጡን Eንዲወሰንልን በማለት ክስ Aቅርበዋል።
የAሁኑ Aመልካች ደግሞ በታህሳስ 23 ቀን 1996 ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡት መልስ ክሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1000(2) Eና 1845 መሰረት በይርጋ ቀሪ ላሆን የሚገባው ነው። ከሟች ጋር ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በስተቀር የጋብቻ ግንኙነት Aልነበረንም። ቤቱ የግል ንብረቴ ነው፤ የልሎቹን ንብረቶች ግምትም የተጋነነ ነው። በመሆኑም ክሱ ውድቅ ሆኖ ልሰናበት ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ክሱ በይርጋ ቀሪ Aይሆንም። ተከሣሾቹ የሟችን ግማሽ ንብረት ለከሣሾች Eንዲያስረክቡ በማለት ወስኗል። የፍ/ከ/ፍ/ቤትም የቀረበለትን ይግባኝ ከተመለከተ በኋላ የሥር ፍ/ቤቱን ውሣኔ Aጽንቶታል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ በመቃወም ሲሆን Aመልካች ያቀረቡት ቅሬታ ክሱ የቀረበው ሟች ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየች ከAሥራ ሦስት ዓመት በኋላ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1000(2) Eና 1845 መሰረት በይርጋ ቀሪ መሆን ያለበት ነው። የሥር ፍ/ቤቶች የይርጋ ክርክሬን ውድቅ በማድረግ በEኔ ላይ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔና ፍ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠው ትEዛዝ Eንዲሻሩልኝ የሚል ነው።
ይህ የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም Aቤቱታውን ከመረመረ በኋላ ክሱ በይርጋ Aይታገድም መባሉ በAግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር Eንዲቻል Aቤቱታው ያስቀርባል የሚል ትEዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪዎች ደግሞ ባቀረቡት መልስ Eህታችን ከሞተች Aሥራ Aምስት ዓመት ሳያልፍ ነው ክስ የመሰረትነው በመሆኑም ክሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1000(2) መሰረት በይርጋ ቀሪ የሚሆንበት የሕግ ምክንያት የለም። የፍ/ብ/ሕ/ቁ/1845 ደግሞ ተግባራዊ የሚሆነው ውልን መሰረት በማድረግ በሚቀርቡት ክርክሮች ላይ Eንጂ የውርስ ክርክርን uሚመለከት Aይደለም። በዚሁ ምክንያት ክሱ በይርጋ የሚታገድበት ምክንያት ላኖር Aይችልም። ክሱ” በጊዜው ለማቅረብ ያልቻልነውም ከተጠሪዎቹ Aንዱ የሆነው Aቶ ካሣሁን ደሳለኝ በሻEቢያ መንግሥት የተከፈተብንን ወረራ ለመመከት በመዝመቱ ምክንያት ሳይሰማ በመቅረቱ ምክንያት ነው። የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔም የሚነቀፍበት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የልለው በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ Eንዲፀና Eንዲወሰንልን በማለት ተከራክረዋል።
በበኩላችን ደግሞ ክሱ በይርጋ ቀሪ ላሆን ይገባል ወይስ Aይገባም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን Eንደመረመርነው በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1000(2) መሰረት የይርጋ ጥያቄ የሚነሳው ክርክሩ Eየተደረገ ያለው በወራሾች መካከል ሲሆን በመሆኑና በዚህ ጉዳይ ክስ የቀረበው በወራሽ ላይ ባለመሆኑ ክሱ በዚሁ የሕግ ቁጥር መሰረት በይርጋ ቀሪ ላሆን የሚችልበት ምክንያት የለም ብለናል።
239 240 በልላ በኩል ደግሞ ክርክሩ Eየተካሄደ ያለው በወራሾችና ወራሽ ባልሆኑ ሰዎች መካከል በመሆኑ ተጠሪዎች የEህታቸውን ንብረት የያዙትን Aመልካች ንብረቱን Eንዲያካፍላቸው ለመጠየቅ የሚከለክላቸው ወይም በጊዜ Eንዳይጠይቁ የሚያደርጋቸው ሕጋዊ ምክንያት በልለበት ሁኔታ ክስ ሳይመሰርቱ ከAሥር ዓመት በላይ የቆዩበትን ሁኔታ ስንመለከት ጥያቄው የይርጋ ክርክር ላያስነሣ የሚችል ሆኖ Aግኝተነዋል። በመሆኑም Aመልካች ያነሱትን የይርጋ መቃወሚያ Aግባብነት ከፍ/ብ/ሕ/ቁ/1677 Eና 1845 Aንፃር መታየት የሚገባው መሆኑን ተገንዝበናል። በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1677(1) Eንደተመለከተው ግድታው ከውሉ የተገኘ ባይሆንም በፍትሐብሕር ሕጉ Aራተኛ መፀሐፍ በAንቀጽ 12 ሥር የተመለከቱት ስለ ውሎች በጠቅላላው የተቀመጡት ድንጋጌዎች በግድታው ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ። በEርግጥ የAንዳንድ ግድታዎችን Aመጣጥ ወይም ዓይነት በመመልከት ከተጠቀሰው Aንቀጽ ሥር ከተመለከቱት ደንቦች የተለዩ ድንጋጌዎች በሕግ ተመልክቶ ከተገኘ Eነዚህ በተለይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች Aግባብነት Eንደሚኖራቸው በተጠቀሰው ቁ.1677(2) ተመልክቷል።
ወደያዝነው ጉዳይ ስንመለስ ተጠሪዎች የመሰረቱትን ክስ በተመለከተ በተለይ Aግባብ ያለው የይርጋ ደንብ የለም። የግድታውን Aመጣጥ ወይም Aይነት በሚመለከት Aግባብ ያለው የይርጋ ደንብ ከልለ ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁ1845 የተደነገገው የAሥር Aመት ገደብ/ይርጋ/ ላፈፀምበት Eንደሚገባ ግልጽ ነው። ክሱ የቀረበው ሟች ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩ ከAሥራ ሦስት ዓመት በኋላ በመሆኑም በዚሁ የይርጋ ደንብ ተቋርጧል ማለት ነው። Eውነታው ይህ ከሆነ ደግሞ የሥር ፍ/ቤቶች በይርጋ ረገድ የቀረበውን የAመልካች መቃወሚያ ውድቅ ያደረጉት ያለAግባብ ከሕጉ ውጪ ነው። ከዚህ የተነሣም Aቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ችለናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
Aቤቱታ የቀረበበት የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/31726 ህዳር 1 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠውና የፍ/ከ/ቤት በመ/ቁ/34855 ግንቦት 8 ቀን 1998 ዓ.ም ያፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/348(1) መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
ተጠሪዎች በAመልካች ላይ የመሰረቱት ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ወስነናል። ይፃፍ። ውሣኔው የተሰጠው በድምጽ ብልጫ ነው።
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙን ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ ብለን መዝገቡን ዘግተን ወደ መ/ቤት መልሰናል።
የማይነበብ የAራት ዳኞች ፊርማ Aለበት የልዩነት ውሣኔ Eኔ በAራተኛ ተራ ቁጥር የተሰየምኩት ዳኛ Aብላጫው ድምጽ ተጠሪዎች የሟች Eህታቸው ወ/ሮ ያልጋ ደሣለኝ ከተጠሪው ጋር በጋብቻ በነበረችበት ወቅት Aፍርታ የነበረውን ቤትና ልሎች የጋራ ንብረቶች ተጠሪው Eንዲያካፍላቸው ያቀረቡት ጥያቄ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1677 ንUስ Aንቀጽ 1 Eና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1845 መሰረት በይርጋ ስለሚታገድ ተቀባይነት የለውም የማለት በሰጠው ውሣኔ ያልተስማማሁ በመሆኑ በሀሳብ ተለይቻለሁ።
የክርክሩ ፍሬ ጉዳይ ከላይ በግልጽ Eንደተቀመጠው የተጠሪዎች Aውራሽ የሆነችው ወ/ሮ ያልጋ ደሣለኝ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ጥቅምት 11 ቀን 1982 ዓ.ም ነው። ተጠሪዎች Aመልካች የሟችን የውርስ ንብረት Eንዲያካፍላቸው ለፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡት ነሐሴ 7 ቀን 1995 ዓ.ም ነው። ተጠሪዎች የሟች ውርስ በAመልካች Eጅ መሆኑን ያወቁት በሐምል ወር 1993 ዓ.ም Eንደሆነ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መጋቢት 7 ቀን 1996 ዓ.ም በሰጠው ብይን በግልጽ ተመልክቷል። ይኸም ሲሰላ፤ ተጠሪዎች የወራሽነት ጥያቄያውን በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 999 መሰረት ያቀረቡት ሟች ከሞተች ከAሥራ 241 242 ሦስት ዓመት ከAሥር ወር ውስጥ የሟች ንብረት በAመልካች Eጅ መሆኑን ካወቁበት ሁለት ዓመት Eንደሆነ ያመለክታል።
ከላይ የተመለከቱት ፍሬ ጉዳዮች ሲመዘኑ ተጠሪዎች ክስ ያቀረቡት በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1000 ንUስ Aንቀጽ 1 የተመለከተው የሦስት ዓመት የይርጋ ገደብም ሆነ የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1000 ንUስ Aንቀጽ 2 የተደነገገው የAሥራ Aምስት ዓመት የይርጋ ገደብ ከማለፉ በፊት ቢሆንም Aብላጫው ድምጽ ŸLà ¾}ÑKì¨<” ¨<d’@ ¾cÖ¨< በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1000 ንUስ Aንቀጽ 2 የተደነገገው የይርጋ የጊዜ ገደብ የሚያገለግለው ክርክሩ በሟች ወራሾች መካከል በሚደረግበት ጊዜ Eንጂ የሟች ወራሾች ወራሽ ካልሆነ ሰው ጋር በሚከራከሩበት ጊዜ ተጠቃሽነትም ሆነ ተፈፃሚነት የለውም የሚል የሕግ ትርጓሜ በመስጠት ነው። ተጠሪዎች ያቀረበት ክስ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1677/1/ Eና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1845 መሰረት በይርጋ ይታገዳል የሚል ውሣኔ ሰጥቷል። በEኔ በኩል ይህ Aበላጫው ድምጽ በሰጠው የህግ ትርጓሜና ውሣኔ የማልስማማው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው።
የሟች ወራሾች ከላይ uተገለፁት የሕግ ድንጋጌ−‹ መሰረት የውርስ Aጣሪውን የውሣኔ ሀሣብ የሚቃወሙ ከሆነ ሀሣቡን የሚቃወሙበት የጊዜ ገደብና የAጣሪው ውሣኔ ፈራሽ Eንዲሆን ክስ የሚያቀርቡበት የይርጋ የጊዜ ገደብ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 973 Eና በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 974 ተደንግጓል። ሕግ Aውጪው በሟች የኑዛዜና ያለ ኑዛዜ ወራሾች መካከል ውርሱ Eየተጣራ ባለበት ሂደት በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 973 Eና የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 974 መሰረት ይፈታል በሚል Eምነት የይርጋ የጊዜ ገደቦችን Aስቀምጧል የሚል Eምነት Aለኝ። ሕግ Aውጪው በሟች ውርስ Aወራረስ ሥርዓት ውስጥ መሰረታዊና ቁልፍ የሥራ ሂደት Aድርጐ የሚመለከተው የውርስ ማጣራት ሒደትን ሲሆን የሟች” ውርስ በAግባቡ ለማጣራት ይቻል ዘንድ Aንድ መቶ ዘጠኝ የሚሆኑ ድንጋጌዎች” ማለትም በፍትሐብሕር ሕግ ቀጥር 942 Eስከ ፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1051 ደንግጓል። ሆኖም የሟች ውርስ በEነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት በAግባቡ የማይጣራ በመሆኑ uሟች ወራሾች መካከል በፍርድ ቤቶች የሚካሄዱ ክርክሮች ይታያሉ። ስለሆነም በሟች ወራሾች መካከል የሚደረገው ክርክር ባህሪ በመለየት uፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 973 Eና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 974 የተደነገጉት የይርጋ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ በሚሆኑበት Aግባብ ለሕጉ ትርጓሜ መስጠት ሲገባ በወራሾች መካከል ውርሱ በሚጣራበት ጊዜም ሆነ ከዚያ በኋላ Kሚነሱ ክርክሮች የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1000/2/ የይርጋ ገደብ ተፈፃሚነት ያለው መሆኑን የሚያሣይ ትርጓሜ መስጠቱ ተገቢነት ያለው Aይደለም።
የሟች Aንደኛው ወይም ከAንድ በላይ የሆኑ ህጋዊ ወራሾቹ በልሉበት ወይም ወኪላቸው ባልተኘበት ሁኔታ ይልቁንም ሟች ልላ ወራሽ Eንደልለው በመቁጠር የሟች ውርስ ሲከፈል የነበሩት የሟች ወራሾች የሟችን ንብረት ተከፋፍለው ቢወስዱ የሟች ውርስ ሲከፈል Áልነበረው ወራሽ ክፍያው ፈራሽ Eንዲሆንና Eሱ ባለበት Eንደገና የውርስ ንብረቱ ተከፍሎ ድርሻው Eንዲሰጠው መጠየቅ Eንደሚችል የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1080 ንUስ Aንቀጽ 2 ይደነግጋል። Eሱ በልለበት ልሎች የሟች ወራሾች የሟችን ንብረት ተከፋፍለው የደረሰ የሟች ወራሽ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1080 ንUስ Aንቀጽ 2 መሰረት የተደረገው የውርስ ንብረት ክፍያ Eንዲፈርስና የEሱ ድርሻ Eንዲሰጠው መጠየቅ የሚችልበት” የይርጋ የጊዜ ገደብ በተመለከተ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1080 ንUስ Aንቀጽ 3 ተደንግጓል። ይኸውም የውርስ ክፍያ ሲከናወን ያልነበረው ወራሽ ክፍያውን ካወቀበት በAንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ወይም በማናቸውም G<’@ u=J” ሟች ከሞተበት ቀን Aንስቶ በAሥር ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ ጥያቄው ውድቅ Eንደሚሆን በግልጽ ተደንግጓል።
ስለሆነም በሟች ወራሾች መካከል የሟች ውርስ ከተዘጋ በኋላ የሚኖረው ክርክር የውርስ ሀብቱን ያካፍለኝ የሚል መሆኑና Eንደዚህ Aይነት ጥያቄ ላቀርብ የሚችለው የሟች ውርስ ክፍያ መደረጉን ካወቀበት በAንድ ዓመት ውስጥ ወይም ሟች ከሞተበት ቀን Aንስቶ ደግሞ በAሥር ዓመት ውስጥ ካልቀረበ ተቀባይነት Eንደልለው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1080 ንUስ Aንቀጽ 3 በግልጽ በሚደነግግበት ሁኔታ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1000 የይርጋ ድንጋጌዎች በወራሾች መካከል Kሚደረግ ክርክር ተፈፃሚነት ያላቸው ናቸው በማለት Aብላጫው ድምጽ የሰጠው ትርጉም Aሣማኝ ሆኖ Aላገኘሁትም።
በEኔ በኩል ከላይ የተገለፁትን የይርጋ ድንጋጌዎች ህግ Aውጪው በወራሾች መካከል ¾T>’d¨<” ክርክር ለመዳኘት Aስቦ የደነገገ ሲሆን የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1000 የይርጋ ድንጋጌዎች ግን የሟች ሕጋዊ ወራሽ በሆነ ሰውና የሟች ወራሽ ባልሆነ ሰው መካከል የሟች” ውርስ ንብረት Aስመልክቶ የሚደ[ገውን ክርክር የጊዜ ገደብ ለመወሰን የደነገጋቸው ናቸው ብዬ Aምናለሁ። ሕግ Aውጪው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1000 ድንጋጌዎች የሟች ወራሾች ያልሆኑ ሰዎች በሚያደርጉት ክርክር ተፈፃሚነት Eንዲኖረው በማሰብ የደነገገ መሆኑን ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 999 Eስከ ፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1002 ያሉትን ድንጋጌዎች ያስቀመጠበትን Aግባብ በማየት ለመረዳት ይቻላል። የEነዚህን ድንጋጌዎች ርEስና Aቀማመጥ ስንመለከት
ስለሆነም የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1000 ድንጋጌዎች በራሳቸው ተነጥለው የሚቆሙና የሚተረጎሙ ሳይሆኑ ሕግ Aውጪው መሰረታዊ መርህ ነው በማለት በግልጽ ካስቀመጠው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 999 ጋር ተያያዥነት ያላቸውና በይዘትም ሆነ uትርጓሜያቸው ከዚሁ ጋር መታየት ያለባቸው የወራሽነት ጥያቄ መሰረታዊ መርህ Eንደሆ’< በግልጽ በርEሱ ላይ በማመልከት ሕግ Aውጪው የደነገገው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 999 Aንድ ሰው ዋጋ ያለው የወራሽነት ማስረጃ ሣይኖረው ውርስን ወይም ከውርሱ Aንዱን ክፍል ብቻ በEጁ ያደረገ Eንደሆነ Eውነተኛው ወራሽነቱ Eንዲታወቅለት Eና የተወሰዱት የውርስ ንብረቶች Eንዲመለስለት በዚህ ሰው ላይ የወራሽነት ጥያቄ ክስ ለማቅረብ Eንደሚችል የሚደነግግ ሲሆን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1000 ደግሞ Eውነተኛው ወራሽ፣ ወራሽ ካልሆነው ሰው ላይ የውርስ ንብረቱ Eንዲመለስለት ክስ የሚያቀርብበትን የይርጋ የጊዜ ገደብ የሚደነግግ ነው።
ስለሆነም በEኔ በኩል የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1000 ድንጋጌዎች የሟች Eውነተኛ ወራሽ የሆነ ሰው የሟች ወራሽ ካልሆነ ማናቸውም ሰው ላይ የውርሱን ንብረት ለማስመለስ የሚያቀርበው” ክስ የይርጋ የጊዜ ገደብ የሚይደነግጉ መሆናቸው Aከራካሪ Aይደለም። Aከራካሪው ጉዳይ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1000 ንUስ Aንቀጽ 1 Eና የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1000 ንUስ Aንቀጽ 2 የተፈፃሚነት ወሰንና Aተረጓጎም ነው። ስለሆነም የሟች ውርስ ንብረት ክፍያና ከሟች ውርስ ላደርሰኝ የሚገባው ድርሻ Aልደረሰኝም በማለት የሟች ወራሾች በልሎቹ ውርሱን በተካፈሉት ወራሾች ላይ የሚያቀርቡት ክስ የይርጋ የጊዜ ገደብ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1080 ንUስ Aንቀጽ 3 የተደነገገ በመሆኑና የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1000 ንUስ Aንቀጽ 2 የሟች ወራሽ የሟች ወራሽ ካልሆነ ሰው የውርሱን ንብረት ለማስመለስ የሚያቀርበውን የይርጋ የጊዜ ገደብ የሚደነግግ በመሆኑ ተጠሪዎች ያቀረቡት የወራኝነት ጥያቄ Aሥራ Aምስት ዓመት ያልሞላው በመሆኑ በይርጋ Aይቋረጥም የሚል የሀሣብ ልዩነት Aለኝ።
ምክንያቱም የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1845 ተፈፃሚነት የሚኖረው “ሕግ በልላ Aኳኋን ካልወሰነ በስተቀር; Eንደሆነ በግልጽ ይደነግጋል። በያዝነው ጉዳይ በሟች ወራሾች መካከል የሚደረገውን ክርክር የይርጋ የጊዜ ገደብ የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 973 የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 974 Eና በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1080 ንUስ Aንቀጽ 3 ተደንግጓል። የEነዚህ” ድንጋጌዎች መሰረታዊ ዓላማና የተፈፃሚነት ወሰን በመተርጎም በሟች ወራሾች መካከል የሚነሣውን ክርክር የይርጋ የጊዜ ገደብ መወሰን በሚቻልበት ሁኔታ ሕግ Aወጪው Aንድ ወራሽ ወራሽነቱ Eንዲታወቅለትና የውርስ ንብረት Eንዲመልስለት ወራሽ vልሆነ ሰው ላይ የሚያቀርበውን ክስ ለመዳኘት በማሰብ የደነገገውን የፍትሐብሕር ሕግ Aንቀጽ 1000፣ በወራሾች መካከል ባለ ክርክር ተፈፃሚነት ያለው ድንጋጌ ነው የሚል ትርጓሜ መስጠትና በወራሾችና ወራሽ ባልሆኑ ሰዎች መካከል የሚደረገው” ክርክር የይርጋ የጊዜ ገደብ የሚደነግግ የውርስ ሕግ ድንጋጌ ስለልለ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1845 ተፈፃሚነት ላኖረው ይገባል በማለት Aብላጫው ድምጽ የሰጠው መደምደሚያ ከላይ ባነሣኋቸው ምክንያቶች ተገቢ ናቸው ብዬ ስለማላስብ የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1000 ንUስ Aንቀጽ 1 Eና 2 ድንጋጌዎች በAመልካችና በተጠሪዎች ጉዳይ ተፈፃሚነት ያላቸው ናቸው። የተጠሪዎችም የወራሽነት ክስ በይርጋ የሚታገድ Aይደለም በማለት በልዩነት ወስኛለሁ።
የማይነበብ የAንድ ዳኛ ፊርማ Aለበት ቤ/ኃ 247 248