No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ 20295 ሐምል 5 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ Aሰግድ ጋሻው ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ Aመነው Aመልካች፡- Aቶ ደጀኔ ለገሰ - ቀረቡ ተጠሪ፡- Eነ Aቶ መላኩ ጌታቸው - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው Aመልካች የውርስ ሀብት ለመረከብ በተጠሪዎች ላይ ያቀረቡት ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል ተብሎ በፍድራል መጀመሪያ ደረጃና ከፍተኛ ፍ/ቤት ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ሲታይ Aመልካች በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ ከሳሽ በEናታቸው በወ/ሮ የልፍኝ Eጅጉ ተተክተው የወ/ሮ ያምሮት Eጅጉ ወራሽ መሆናቸውን ሰኔ 30 ቀን 1996 ዓ.ም በፍ/ቤት ውሳኔ Aረጋግጠዋል። የተከሳሾች Aያት ወ/ሮ ታደለች Aርጋው ከወ/ሮ ምንትዋብ ሙሴ ጋር በመሆን የAክስቴ የወ/ሮ ያምሮት Eጅጉ ወራሽ ናቸው ተብሎ የካቲት 29 ቀን 1981 ዓ.ም በፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ መቃወሚያ Aቅርቤ ሰኔ 30 ቀን 1991 ዓ.ም ተሰርዟል። ከዚያም ቤት ለማስለቀቅ ሚያዚያ 10 ቀን 1992 ዓ.ም በተከሳሾች Eናትና በወ/ሮ ምንትዋብ ሙሴ ላይ ክስ ብመሰርትም ተከሳሾች በሞት በመለየታቸው መጥሪያ ሳይደርሳቸው ክሱ ተቋርጧል።
በAጠቃላይ ተከሳሾች ከወ/ሮ ያምሮት Eጅጉ የሚደርሰኝን የውርስ ሀብት ያስረክቡኝ በማለት ጠይቀዋል።
ተጠሪዎችም በሰጡት መልስ ከሳሽ የወ/ሮ ያምሮት Eጅጉ ሕጋዊ ወራሾች መሆናቸውን ያረጋገጡት ሐምል 14 ቀን 1986 ዓ.ም ይዘውብኛል የሚሉትን ቤት ላለፋት ዘጠኝ ዓመታት ያልጠየቁ ስለሆነ ክሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1000 (1) መሰረት በ3 ዓመት ይርጋ ይታገዳል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና በፍሬ ጉዳዩም ሙሉ መልስ በመስጠት ተከራክረዋል።
ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፍድራሉ መ/ደ/ፍ/ቤት የከሳሽ ክስ በይርጋ ይታገዳል ወይስ Aይታገድም የሚለውን ጭብጥ መሥርቶ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክሩን መርም[ል።
በዚህም መሰረት ከሳሽ የወ/ሮ ያምሮት Eጅጉ ወራሽ መሆናቸውን ያረጋገጡት ሐምል 14 ቀን 1986 ዓ.ም ነው። ከዚህም በኋላም በተከሳሶሾች Eናት ላይም ሆነ በተከሳሾች ላይ የውርስ ሀብት ይልቀቁልኝ በማለት ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት Eንዳገኙ ይቆጠራል።
ይህ የይርጋ ጊዜ ላቋረጥ ከሚችልባቸው ምክንያቶች Aንዱ ክስ ቀርቦ በሆነ ጊዜ ሲሆን ከሳሽ በመ/ቁ 3311/81 የካቲት 29 ቀን 1981 ዓ.ም የተከሳሾች ወላጅ Eናትና ወ/ሮ ምንትዋብ ሙሴ ወራሾች ናቸው ተብሎ የተሰጠን ውሳኔ በመቃወም Aቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም ይህ የመቃወሚያ ክርክር የወራሽነት መብት ላይ ብቻ ያነጣጠረ በመሆኑና የውርስ ንብረት ይሰጠኝ በሚል የቀረበ ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1851(ለ) መሰረት ይርጋው ተቋርጧል ለማለት Aይችልም።
ስለሆነም ከሳሽ የወራሽነት መብታቸውን ካረጋገጡና የውርሱ ንብረቶች በተከሳሾች መያዛቸውን ካወቁ በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ በተከሳሾች ላይ ክሱን ያላቀረቡ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ ቁጥር 1000(1) መሰረት በ3 ዓመት ይርጋ ይታገዳል በማለት ክሱን ሳይቀበለው ቀርቷል።
ጉዳዩን በይግባኝ የመረመረው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን Aከራክሮ ተመሳሳይ ጭብጥ በመያዝ የፍ/ብ/ሕ ቁ.1AAA(1) ተፈፃሚነቱ Aንድ የወራሽነት ማስረጃ ያለውና ነገር ግን ይህ ማስረጃው በሕግ ዓይን ተቀባይነት የልለው ሆኖ ውርሱን ወይም የውርሱን Aንድ ክፍል የያዘ ከሆነ በሕጉ ዓይን ተቀባይነት ያለው ማስረጃ የያዘው ወራሽ ወራሽነቱ Eንዲታወቅለትና የተወሰዱበት የውርስ ንብረቶች Eንዲመለሱለት በሚጠየቅበት ጊዜ Eንደሆነ በውሳኔው ላይ Aስፍሮ በተያዘው ጉዳይ ግን መ/ሰጭዎች ተጠቃሹን ንብረት የያዙት ምንም ዓይነት የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖራቸው ስለሆነ ለጉዳዩ Aግባብነት ያለው ድንጋጌ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000 ሳይሆን ቁጥር 1845 ነው ካለ በኋላ ከዚሁ Aኳያ ሲታይም የይ/ባይ/የተጠሪ Aውራሽ በ1978 ዓ.ም መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ተጠሪም በመብታቸው መሥራት የሚችሉት ከዚህ ጊዜ በኋላ ስለሆነ ቤት ይለቀቅልኝ በማለት ክስ የመሰረቱት ምንም Eንኳን መጥሪያው ለመ/ሰጭዎች Aውራሽ ያልደረሰ ቢሆንም በ1992 ዓ.ም ከ14 ዓመት በኋላ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 ላይ በተቀመጠው የ1A ዓመት ጊዜ ክሱ ያልቀረበ ስለሆነ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ምክንያቱን ቀይሮ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ውሳኔን Aጽንቷል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወምና መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aለበት በማለት ሲሆን ይህ ሰበር ሰሚ ችሎትም የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ የመ/ሰጪዎች Aውራሽ የሟች ወ/ሮ ያምሮት Eጅጉ ልጅ ነኝ በማለት ያወጡትን የወራሽነት ማስረጃ Aመልካች ጥር 2A ቀን 1987 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መቃወሚያ በማቅረብ Eንዲሰረዝ ካደረገ፣ የወራሽነት ማስረጃ ያሰረዘበት ውሳኔ ከግምት ሳይገባ ንብረቱን ለመረከብ የጠየቀው Aውራሹ ከሞቱ ከ1A ዓመት በኋላ ነው ተብሎ ክሱ በይርጋ ቀሪ ¾መደረጉ” Aግባብነƒ ለማጣራት ሲሆን ተጠሪዎች ቀርበው ክሱ በይርጋ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ Aግባብነƒ በመዘርዘር Aቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
No topics extracted.
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን በሥር ፍ/ቤቶች በተጠሪ በኩል የቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ Aግባብነƒ ከሕጉ Aኳያ Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
Aመልካች በፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ያቀረቡት ክስ ባጭሩ ከAክስቴ ከወ/ሮ ያምሮት Eጅጉ በውርስ የተላለፈልኝን ቤት ይዘው የሚገኙ ስለሆነ ያስረክቡኝ በማለት ነው።
ተጠሪዎች የAመልካች Aክስት የሆኑት የወ/ሮ ያምሮት Eጅጉ” ንብረት በመውረስ ረገድ የቅድሚያ መብት Eንደልላቸው ቢረጋገጥም ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ይዘው የተገኙት ወራሽ ነን በማለት ነው። ተጠሪዎች ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት በመውረስ ረገድ ከAመልካች የቀደመ መብት ባይኖራቸውም ንብረቱን ይዘው የሚገኙት የመውረስ መብት ሳይኖራቸው ነው ለማለት ግን የሚÁeችል Aይሆንም።
ተጠሪዎች ቤቱን ይዘው የሚገኙት በወራሽነት መብት ነው ከተባለ ደግሞ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1AAA(1) በዚህ ጉዳይ ተፈፃሚነት Aለው ማለት ነው።
ስለሆነም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተጠቀሰው ድንጋጌ ለዚህ ጉዳይ ተፈፃሚነት የለውም በማለት የይርጋ ክርክሩን ከቁጥር 1845 ድንጋጌ ጋር Aያይዞ በዚሁ ድንጋጌ መሰረት ክሱ በይርጋ ተቋርጧል የሚል ውሳኔ ¾cÖ¨< ሕጉን በተገቢው ካለመተርጐም Eንደሆነ ታምኖበታል።በልላ በኩልም Aመልካች ተጠሪዎች የያዙትን የውርስ ንብረት ያስረክቡኝ በማለት በተጠሪዎች ላይ ክስ የመሰረቱት ሰኔ 3A ቀን 1996 ዓ.ም ሲሆን የAክስታቸው ወራሽነታቸውን ያረጋገጡት ደግሞ ሐምል 14 ቀን 1986 ዓ.ም ነው።
Aመልካች ወራሽነታቸውን ካረጋገጡ በኋላ በፍ.ብ.ሕ.ቁ. 1000(1) ላይ የተቀመጠው የ3 ዓመት የይርጋ ጊዜ ከማለፋ በፊት በተጠሪዎች ተይዞብኛል የሚሉት ንብረት Eንዲመለስላቸው መጠየቅ ይገባቸው Eንደነበር የሚታመን ከመሆኑም በላይ የተጠሪዎች Aውራሽ የAመልካች Aክስት ወራሽ ናቸው ተብሎ የተሰጠውን ውሳኔ Aመልካች ለማሰረዝ Aቤቱታ Aቅርበው ክሱን ማቅረብ የሚችሉት ውሳኔው ከተሰረዘ በኋላ ነው ቢባል Eንኳን ይሄው ውሳኔ በ1991 ዓ.ም ተሰርዞ ክሱን ግን ያቀረቡት የ3 ዓመቱ የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ በ1996 ዓ.ም ስለሆነ ከተጠቀሰው የፍ.ብ.ሕ.ቁ 1AAA(1) Aኳያ በይርጋ የማይታገድበት ምክንያƒ Aልተገኘም፡
(1) የሥር ፍ/ቤቶች የቀረበው ክስ በይርጋ ተቋርጧል በማለት የሰጡት ውሳኔ ከውጤት Aኳያ በAግባቡ ሆኖ ስለተገኘ በፍ.ብ.ሕ.ሥ.ሥ.ቁ.
348 (1) መሰረት ፀንቷል።
(2) የፍርዱ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይተላለፍ (3) ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ (4) መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።