No summary available.
ሚያዚያ 07 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ መልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- ወ/ሮ መገርቱ ነጋሣ- Aልቀረቡም ተጠሪ፣ Eነ ወ/ሮ ፀሃይ ልጋ Aልቀረቡም
ለሰበር Aቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዳይ የጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ነው።
የAሁኑ ተጠሪዎች ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት ክስ የ1ኛ ተጠሪ ባለቤት የቀሪዎቹ ተጠሪዎች Aባት በህይወት በነበሩበት ጊዜ ክስ የቀረበበትን ቤት ለAቶ ደረጀ መንግስቱ Aከራይተው የነበረ ሲሆን ተከራዩ Aመልካችን ቤቱ ውስጥ Aስገብተው Aካባቢውን ለቀው ጠፍተዋል። Aመልካችንም የግል ቤታችንን ለቀው Eንዲወጡ ጠይቀን ፍቃደኛ Aልሆኑም።ለሚመለከተዉ ቀበልም Aመልክተን Aመልካችም ቤት ሲያገኙ ለቀው የሚወጡ መሆኑን በEማኞች ፊት Aረጋጠው የፈረሙ ቢሆንም ቤቱን ስላለቀቁ ቤቱን Eንዲያስረክቡን፣ ያለምንም ክፍያ ከመጋቢት 26 ቀን 1991 ዓ.ም ክስ Eስከቀረበበት ድረስ ስለኖሩ በወር ብር 150(Aንድ መቶ ሃምሳ) ታስቦ በድምሩ ብር 11,250 (Aስራ Aንድ ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ) Eንዲከፈሉ ይወሰንልን ብለው ጠይቀዋል።
Aመልካችም ለቀረበባቸው ክስ በሰጡት መልስ ክስ የቀረበበት ቤት ተጠሪዎች በሚኖሩበት ቤት ይዞታ ስር የሚጠቃለል ለመሆኑ ማስረጃ Aላቀረቡም፣ ቤቱ ለAቶ ደረጀ መንግስቱ የተከራየበት ማስረጃ Aልቀረበም፣ ቤቱን በወረራ ይዛለች ካሉ ይህን ካወቁ 10 ዓመት በላይ ስለሆነ በይርጋ ይታገዳል፣ የደረሰባቸው የጥቅም ጉዳት ከውል ውጪ Eንደመሆኑ መጠን የኪራይ ማስከፈል ጥያቄAቸው ሁለት Aመት ካለፈው በይርጋ ይታገዳል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ካቀረቡ በኋላ ለፍሬ ጉዳዩ በሰጡት መልስ ቤቱን የተጠሪዎች Aውራሽ Aልሰሩትም ለAቶ ደረጄም Aላከራዩም፣ ቤቱ የAቶ ደረጀ ሲሆን ለAመልካች Aከራይተውኛል፣ ቤቱን ለማስረከብ ቃል ገብታለች የተባለው ተገድጄ የፈረምኩት ስለሆነ Aልገደድበትም በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ የAመልካችን መቃወሚያዎች ውድቅ ካደረገ በኋላ Aመልካች ይዘውት የሚገኘው ቤት የ1ኛ ተጠሪ ባለቤትና የቀሪዎቹ Aባት ይዞታ ስር የሚካተት መሆኑ ተረጋግጧል በማለት Aመልካች ቤቱን ለተጠሪዎች Eንዲያስረክቡና Aመልካች ቤቱን Eለቃለሁ ብለው ከፈረሙበት ጊዜ ጀምሮ በወር ብር 150.00 (መቶ ሃምሣ) Eየታሰበ ክሱ Eስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ብር 11,250 ( Aስራ Aንድ ሺህ ሁለት መቶ ሃምሣ) ይክፈሉ በማለት ወስኗል። ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፍ/ከ/ፍ/ቤትም ውሣኔውን Aጽንቷል።
የAሁኑ የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም ውሣኔው የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት ነው። ይህ ችሎትም Aመልካች ከመጋቢት 26 ቀን 1991 ዓ.ም Eስከ ሐምል 19 ቀን 1997 ዓ.ም ድረስ ያለውን የተጠሪዎችን ቤት ያላግባብ የያዙበትን ብር 11,250(Aስራ Aንድ ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ) Eንዲከፍሉ የተሰጠውን ውሣኔ Aግባብነት ለመመርመር Aቤቱታው ለሰበር ችሎት ቀርቦ Eንዲታይ Aድርጐ ተጠሪዎች ክርክራቸውን በጽሁፍ Aቅርበዋል።
ፍ/ቤቱም መዝገቡን መርምሯል።
ተጠሪዎች Aመልካች ቤታቸውን ያለAግባብ ስለያዙ Eንዲያስረክቧቸውና በቤቱ ያለAግባብ ለተገለገሉበት ካሣ Eንዲከፍሉ ጠይቀዋል። Aመልካች በበኩላቸው ቤቱ የተጠሪዎች Aለመሆኑንና ቤት Eንዲለቁም ሆነ ካሣ Eንዲከፍሉ የቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ የሚሆን ነው ሲሉ ተከራክረዋል።
225 226 ከክርክሩ ክስ የቀረበበት ቤት የተጠሪዎች መሆኑ በማስረጃ መረጋገጡን የተገነዘብን በመሆኑ Aመልካች የቤቱን ባለቤትነት በተመለከተ ማስረጃ ላይ ተንተርሰው ያቀረቡትን ክርክር ይህ ችሎት Aልተቀበለውም። ልላው Aመልካች ያነሱት ክርክር ቤት Eንዲያስረክቡ የቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ነው የሚል ነው። Aመልካችዋ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ያሉት ክሱ ሁከት ይወገድልኝ በማለት የቀረበ ስለሆነ ነው በማለት ነው። ነገር ግን ተጠሪዎች ይዞታችን በሃይል ተወስዷል ወይም በይዞታችን ላይ ሁከት ተፈጥሯል በማለት ያቀረቡት ክስ የለም። ክሣቸው በኪራይ ለAቶ ደረጀ ያስረከቡትን ቤት Aመልካች መብት ሣይኖራቸው ገብተው Aልወጣም ብለዋልና ያስረክቡን የሚል ነው። ስለሆነም Aመልካች AለAግባብ የያዙትን ንብረት Eንዲለቁ የቀረበ ክስ ስለሆነ የAመልካች ተቃውሞ ተቀባይነት የለውም።
በመጨረሻ Aመልካች ያቀረቡት ክርክር የቀረበው የካሣ ጥያቄም ቢሆን በይርጋ ቀሪ ይሆናል የሚል ነው። ክስ የቀረበበት ቤት የተጠሪዎች በመሆኑ ቤቱ” ያላግባብ ይዘው ለተጠቀሙበትና ያላግባብ ለበለፀጉበት ካሣ Eንዲከፍሉ ክስ ቀርቧል:: በልላ ሰው የስራ ድካም ወይም በልላ ሰው ሃብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው ጥቅም ባገኘበት መጠን ለባለሃብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ኪሣራ መክፈል Eንዳለበት በፍ/ህ/ቁ.
No topics extracted.
2162 ሥር ተመልክቷል። በመሆኑም Aመልካች በቤቱ Aላግባብ በበለፀጉበት መጠን ኪሣራ Eንዲከፍሉ መጠየቃቸው ህጉን መሰረት ያደረገ ነው። በልላ በኩል ግን ይህ የካሣ ጥያቄ ላቀርብ የሚገባበት” የጊዜ ገደብ በተመለከተ ክርክር ቀርቧል። ያለAግባብ ስለመበልፀግ የሚናገረው ምEራፍ የካሣ ጥያቄ የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ Aይናገርም። ነገር ግን Aላግባብ ስለመበልፀግና ከውል ውጪ ስለሚደርስ ሃላፊነት የሚናገሩት ድንጋጌዎች በAንድ Aንቀጽ ውስጥ ተካትተው መገኘታቸው Eንዲሁም ያለAግባብ መበልፀግም ከውል ውጪ የሚደርስ ሃላፊነት በመሆኑ ከውል ውጭ uሚደርስ ሃላፊነት ሥር የተመለከተው የይርጋ ዘመን በተመሣሣይ Aላግባብ መበልፀግ” በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት ላኖረው ይገባል። በዚህ መሰረት ከውል ውጭ ሃላፊነትን በተመለከተ ተበዳዩ ክስ ማቅረብ የሚችለው ካሣ የሚጠይቅበት ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ Aስከ 2 Aመት ድረስ መሆኑ በፍ/ህ/ቁ 2143/1/ ሥር ተመልክቷል።
በተያዘው ጉዳይ Aመልካች ቤቱን ያለማቋረጥ ለረዥም ጊዜ ይዘው Eየተገለገሉበት በመሆኑ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ኋላ ላሉት ሁለት Aመታት Aላግባብ በቤቱ በተገለገሉበት መጠን Eንዲከፈሉ የተጠየቁት ካሣ በይጋ የሚታገድ Aይሆንም:: ከዛ በፊት ያሉት ግዜያት ግን በይርጋ ቀሪ የሚሆኑ ናቸው። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች የ6 Aመት ካሣ Eንዲከፍሉ የሰጡት ውሣኔ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ’¨< wK“M።
ው ሣ ኔ
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 13468 በሐምል 27 ቀን 1999 የሰጠው ውሣኔ፣ የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 58602 በኀዳር 30 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጡት ውሣኔዎች ተሻሽለዋል።
Aመልካች ክስ የቀረበበትን ቤት ያስረክቡ። ከሐምል 20 ቀን 1995 ዓ.ም Eስከ ሐምል 19 ቀን 1997 ዓ.ም ላለው ጊዜ ብቻ በቤቱ Aላግባብ ለተጠቀሙበት በወር ብር 150.00(Aንድ መቶ ሃምሣ) ታስቦ በድምሩ ብር 3,600(ሦስት ሺህ ስድስት መቶ) ለተጠሪ ይክፈሉ።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ ።