No summary available.
¾c/S/l. 33924 ሚያዝያ 16 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ መድሕን ኪሮስ Aመልካች፡- ወ/ሮ ገብርኤላ ሂኮላቶማስ - ጠ/Aስቴር AርAያ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ - ነ/ፈጅ ቤዛ Aስራት ቀረቡ
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ክስ የጀመረው በፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው።
የAሁን Aመልካች ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት ክስ ከAባቴ በውርስ የተላለፈልኝን ቤት ተጠሪው በAደራ ተረክቦ Eያስተዳደረ ቢቆይም ቤቱን Eንዲያስረክበኝ ብጠይቀው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ቤቱን Eንዲያስረክበኝና ከ1973 ዓ.ም ጀምሮ የሰበሰበውን የኪራይ ገንዘብ Eንዲመልስልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ተጠሪም ለክሱ በሰጠው መልስ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለውም፣ Aመልካች ክሱን ለማቅረብ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም፣ ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ Aቅርቧል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ Aመልካች ቤቱ የAባታቸው የግል ቤት ለመሆኑ የሚያስረዳ በህጉ መሰረት የተሰጠ የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ Aላቀረቡም ወይም ቤቱ ከAዋጅ ውጪ የተወረሰ ተብሎ ከሚመለከተው Aካል Eንዲመለስላቸው የተፈቀደ ማስረጃ Aላቀረቡም በመሆኑም ክስ በተመሰረተበት ንብረት ላይ ጥቅም ወይም መብት የላቸውም በማለት ክሱን ውድቅ Aድርጓል።
በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፍ/ጠቅላይ ፍ/ቤትም ይግባኙን ሣይቀበለው ቀርቷል።
የAሁኑ የሰበር Aቤቱታ ይህንን ውሣኔ ለማስለወጥ የቀረበ ነው ይህ ችሎትም Aመልካች የመክሰስ መብት የላቸውም መባሉ በAግባቡ መሆን Aለመሆኑን ለመመርመር Aቤቱታው ለሰበር ችሎት Eንዲቀርብ Aድርጓል።
በዚሁ መሰረት ተጠሪ ቀርቦ ክርክሩን በጽሁፍ Aቅርቧል። ችሎቱም መዝገቡን Eንደሚከተለው መርምሯል።
ከላይ Eንደተገለፀው Aመልካች ክስ የመሰረቱት ተጠሪ በAደራ ሲያስተዳድረው የቆየውን የAባታቸውን ቤት Eንዲያስረክባቸው ነው። Aንድ ከሣሽ ክስ Eንዲያቀርብ የሚፈቀድለት ለክሱ ምክንያት በሆነው ነገር ወይም ክሱ በተመሰረተበት ሃብት ላይ ጥቅም ወይም መብት ያለው መሆኑን ካረጋገጠ Eንደሆነ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 33/2/ ሥር ተመልክቷል። ስለሆነም Aመልካች ለመረከብ ክስ በመሰረቱት ቤት ላይ መብት ወይም ጥቅም ያላቸው መሆኑን ላያረጋግጡ ይገባል። የሥር ፍ/ቤቶች የAመልካችን ክስ ወድቅ ያደረጉት የቤቱ የባለቤትነት ማረጋገጫ ባለመቅረቡ Aመልካች በንብረቱ ላይ መብት ያላቸው መሆኑን Aላረጋገጡም በማለት ነው።
Eኛ Eንዳየነው ግን Aመልካች ክስ የቀረበበት ቤት የሟች Aባታቸው ቤት ለመሆኑ የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ባያቀርቡም በስራና ከተማ ልማት ሚ/ር የተፃፈ ደብዳቤና የቤቱን የቦታ ካርታ Aቅርበዋል በማስረጃነት የቀረበው ደብዳቤ ክርክር የተነሣበት ቤት የAመልካች Aባት የነበረና Eሳቸው ሲሞቱ ቤቱን ተረክቦ የነበረው የግሪክ ኤምባሲ ቤቱን ለስራና ከተማ ልማት ያስረከበ በመሆኑ ግሪክ Aገር Aሉ የተባሉት የሟች ልጆች ባለመብቶች መሆናቸው ከተረጋገጠ ቤቱን Eንዲረከቡ የሚያሣስብ መሆኑን ያመለክታል። የከተማ ቤቶችን ባለቤትነት ለመወሰን ስልጣን ያለው Aካል የፃፈው ይህ ደብዳቤ ቤቱ የAመልካች Aባት መሆኑን የሚጠቁም ሆኖ Aግኝተነዋል። Aመልካች ደግሞ የሟች Aባታቸው ወራሽ መሆናቸውን Aረጋግጠው የቀረቡ በመሆኑ በቤቱ ላይ ጥቅም ወይም መብት ያላቸው መሆኑን Aላረጋገጡም ለማለት የሚያስችል ሁኔታ Aላየንም። የፍ/ህ/ቁ. 1195/1/ም ቢሆን ለAንድ ሰው የተሰጠው የቤት ባሃብትነት ምስክር ወረቀት ይህ ሰው የዚሁ ቤት ባለሃብት Eንደሆነ ግምት ከሚወሰድ በቀር የቤቱ ባለሃብትነት በልላ ሰነድ ላረጋገጥ Aይችልም የሚል Eንድምታ የለውም። በEርግጥ Aመልካች ቤቱን ላረከቡ ይገባል Aይገባም የሚለው ከግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ Aንፃር ተመርምሮ የሚወሰን ቢሆንም Aመልካች ግን ክስ በቀረበበት ቤት ላይ መብት ወይም ጥቅም ያላቸው መሆኑን Aላረጋገጡም ማለት ስለማይቻል የሥር ፍ/ቤቶች የቤቱ የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት Aለመቅረቡን ብቻ መሰረት Aድረገው ልሎቹን የAመልካች ማስረጃዎች dÁÑ“´u< ›SM"‹ በንብረቱ ላይ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም TK†¨< ስህተት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 48823 በሰኔ 27 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ብይን Eንዲሁም የፍ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 31862 ህዳር 03 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ ተሽረዋል።
No topics extracted.
Aመልካች ክስ በተመሰረተበት ንብረት ላይ ጥቅም ወይም መብት ስላላቸው የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን Aከራክሮ የመሰለውን Eንዲወስን ጉዳዩ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 341 መሰረት ተመልሷል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ።