No summary available.
ሚያዝያ 14 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ሀሰን Iብራሂም ተጠሪ፡- Iብራሂም ይመር ሐሰን መዝገቡን መርምረን ቀጥሎ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ ያለAግባብ የተያዘብኝ ቤት ይለቀቅልኝ በሚል Aመልካች ባቀረበው ክስ መነሻነት የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክሱን ያስተናገደው የደሴ ወረዳ ፍ/ቤት ተጠሪን በማስቀረብ የግራ ቀኝ ወገኖችን ክርክር ሰምቷል። በመጨረሻም ከሳሽ የቤቱ ባለሀብት መሆኑን በማስረጃ Aረጋግጧል በማለት ተጠሪ ቤቱን Eንዲለቅና ለAመልካች Eንዲያስረክብ ወስኖAል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ውሣኔውን በመቃወም ለደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ በድጋሚ ተሰምቶAል። በመቀጠልም ፍ/ቤቱ ተጠሪ በቤቱ ላይ የተሻለ መብት ስላለው ለAመልካች ላያስረክብ Aይገባም በማለት የወሰነ ሲሆን፣ በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የAማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤትም ውሣኔው ጉድለት የለበትም ብሎAል። የሰበር Aቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
ይህ የሰበር ችሎትም Aመልካች ህዳር 9 ቀን 2AAA ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን Aስቀርቦ ክርክሩን ሰምቶAል። Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲታይ የተወሰነው ክርክር የተነሳበት ቀደም ሲል ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ መሰረት በAመልካች ስም ስለመመዝገቡ ማስረጃ ቀርቦAል Eየተባለ በቤቱ ላይ የተሻለ መብት 217 218 ያለው ተጠሪ ነው የመባሉን Aግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
በመዝገቡ ከሰፈረው የግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር Eና የስር ፍ/ቤቶች ከሰጡAቸው ውሣኔዎች ይዘት መገንዘብ Eንደቻልነው ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት በሚመለከተው የAስተዳደር ክፍል ተመዝግቦ የሚገኘው በAመልካቹ ስም ነው። ወደኋላ ያለውን የቤቱን ታሪክ ስንመለከትም ቀደም ሲል ብርሃኔ Aድማሱ፣ ጣይቱ Aድማሱ Eና Aበበ ፋሪስ የተባሉት ሰዎች ንብረት Eንደነበረ፣ Eነዚህ ሰዎች ከAመልካች ብር 12,000(Aስራ ሁለት ሺህ) በመበደራቸው ቤቱን ለ15 ዓመት በመያዣ ለAመልካች መስጠታቸውን በተባለው 15 ዓመት ውስጥ ገንዘቡን ካልመለሱ Aመልካች ቤቱን በስሙ ለማዞር Eንዲችል መስማማታቸውን Aመልካችም በተባለው 15 ዓመት ውስጥ ገንዘቡ ስላልተመለሰልኝ በውላችን መሰረት ቤቱ በኔ ስም Eንዲመዘገብ ይወሰንልኝ በማለት ለፍ/ቤት ክስ Aቅርቦ ማስወሰኑን፣ በዚህ ረገድ የተሰጠው የፍ/ቤት ውሣኔም በይግባኝ ቀርቦ Aለመሻሩን ለመገንዘብ ችለናል። ይህ Eንግዲህ ከAመልካች Aንፃር ያለው ሁኔታ ሲሆን፣ ተጠሪ ደግሞ ቤቱ Eኔም ከተባሉት ሰዎች በይዞታ ተሰጥቶኛል በማለት ነው የተከራከረው። ክርክሩን በይግባኝ የሰሙት ፍ/ቤቶች በወረዳ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ በመለወጥ የወሰኑትም ተጠሪ Aለኝ ለሚለው የመያዣ ውል ከፍተኛ ግምት በመስጠት Eና Aመልካች ቤቱን በስሙ ያስመዘገበው ያለAግባብ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት Eንደሆነ ከውሣኔው ይዘት ለመገንዘብ ችለናል።
በበኩላችን Eንደምናየው ክርክሩ ውስብስብነት የልለው Eጅግ ግልጽ ቀላልም ነው። Aመልካችም ሆነ ተጠሪ ከቀድሞ የቤቱ ባለቤቶች Ò` የመያዣ ውል ማድረጋቸው” በተመሳሳይ ሁኔታ የገለፁ ቢሆንም፤
Aመልካች ግን Aንድ Eርምጃ ወደፊት በመሄድ የመያዣ ውል ነው ያለውን መሰረት በማድረግ ክስ መስርቶ ቤቱ በሱ ስም Eንዲመዘገብ AስወስኖAል። ይህ ውሣኔ በማንኛውም ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ያልተሻረ ሲሆን፣ Aመልካችም በውሣኔው መሰረት በሚመለከተው የAስተዳደር Aካል ቤቱን በስሙ Aስመዝግቦ የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ AግኝቶAል።
ከዚህ Eንግዲህ በግልጽ መገንዘብ የሚቻለው በAሁኑ ደረጃ የቤቱ ባለቤት ላባል የሚችለው Aመልካች Eንደሆነ ነው /በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1195 የተቀመጠው ድንጋጌ ይመለከ…ል/። ይግባኙን የሰሙት ፍ/ቤቶች ተጠሪ Aለኝ የሚለውን የመያዣ ውል በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 3052 በተደነገገው መሰረት የተመዘገበ Eና በሕግ የሚታወቅ ስለመሆኑ Eንኳን ሳያረጋግጡ በቤቱ ላይ ከAመልካች የተሻለ መብት Aለው ወደሚለው መደምደሚያ መድረሳቸው Aግባብ Aይደለም። የመያዣ ውሉ በሕግ የታወቀ ቢሆን Eንኳን ተጠሪን በቀጥታ የቤቱ ባለቤት የሚያደርገው Aይደለም። ከሁሉ በላይ ደግሞ Aመልካች ቤቱን በስሙ ያስመዘገበው በፍ/ቤት ባሰጠው ውሣኔ መሰረት በመሆኑና ይህ ውሣኔም በበላይ ፍ/ቤት ያልተሻረ በመሆኑ በAሁኑ ደረጃ የስም ዝውውሩ ትክክል Aልነበረም ወደሚለው ነጥብ መግባት የሚቻልበት ምንም የሕግ ምክንያት የለም። ሲጠቃለል በሕግ በግልጽ የተረጋገጠ የባለቤትነት መብት ያለው Aመልካች ሆኖ ሳለ ከዚህ ውጪ በሆነ ሁኔታ /በሕላና ግምት ላይ በመመስረት/ ፍርድ መስጠቱ በማንኛውም መለኪያ ተቀባይነት ላኖረው Aይችልም። ስለዚህም Aቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
219 220 2. Aከራካሪው ቤት የAመልካች ንብረት መሆኑን በማስረጃ በማረጋገጥ የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በፍ/ብ/መ/ቁ. 13033 የካቲት 3A ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቶAል።
መዝገቡ ይመለስ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ዙ/ዘ