No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 3A1A1 ኀዳር 24 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- Aቶ ገዛኸኝ Aድነው ጠበቃ ደሴ ሙላት ተጠሪ፡- Eነ ወ/ሮ ዳሳሽ ባይነሳኝ /3 ሰዎች/ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ ጉዳይ ክርክሩ የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን ተጠሪዎች በAሁን Aመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ የ1ኛ ተጠሪ ባለቤትና የልሎቹ ተጠሪዎች Aባት የሆኑት Aቶ Aድነው Aወቀ በልደታ ክ/ከተማ ቀበል A2 ክልል የቤት ቁጥር 56A/ሀ/Eና /ለ/ የሆኑ ቤቶች የነበራቸው ሲሆን ተከሣሽ የቤ/ቁ.
56A/ለ/ የሆነውን ቤት በኃይል ገብቶ Eየተጠቀመበት ስለሚገኝ ይህንኑ ቤት Eንዲያስረክበን ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
Aመልካችም በሰጠው መልስ ክስ የቀረበበት የቤት ቁጥር 56A/ለ/ Eራሴ የሰራሁትና በስሜ የተመዘገበ ስለሆነ ክሱ ከኪሣራ ጋር ላሰረዝ ይገባዋል በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተከሣሽ ለክሱ መነሻ ወደሆነው ቤት በኃይል Eንዳልገባ ነገር ግን 1ኛ ተጠሪ ባለበት የ2ኛ Eና 3ኛ ተጠሪዎች ደግሞ Aውራሽ የነበሩት Aቶ Aድነው Aወቀ ፈቅደውለት ቤቱን ለመስራቱ መገንዘብ የተቻለ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1179 መሰረት ተጠሪዎች ቤቱ የተሰራበትን ዋጋ ከፍለው ቤቱን መረከብ ይችላሉ ካለ በኋላ ግምቱ መሰላት ያለበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 118A በተደነገገው መሰረት መሆን ስለሚገባው ከዚሁ Aኳያ የቤቱን ዋጋ ¼ኛ ከሳሾች ለተከሳሽ ከፍለው ቤቱን ይረከቡ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ይግባኝ የቀረበለትም የፍ/ከ/ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ ይግባኙን ባለመቀበል የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ Aጽንቷል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ሲሆን ይህ ሰበር ችሎት Aቤቱታው ለሰበር ቀርቦ መጣራት Eንደሚገባው በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ Aመልካች ክስ የቀረበበትን ቤት ላያስረክብ ይገባል? ወይንስ Aይገባም የሚለው በመሆኑ ይህንኑ ጭብጥ በመያዝ Aቤቱታው Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
በፍ/ብሕር ሕጉ ስለ ንብረት በጠቅላላው በሚደነግገው ሶስተኛ መጽሐፍ ሥር በAንቀጽ 1178/1/ ባለመሬቱ በግልጽ Eየተቃወመው ማንም ሰው በልላ ሰው መሬት ላይ ሕንጻ የሰራ Eንደሆነ uI”í¨< ላይ Aንዳችም መብት ላኖረው Eንደማይችል የተመለከተ ሲሆን ነገር ግን ባለመሬቱ ሳይቃወም በመሬቱ ላይ ሕንፃ የሰራ ሰው የዚሁ ሕንጻ ባለሀብት ላሆን Eንደሚችል ቀጥሎ በሚገኘው በቁጥር 1179/1/ ላይ ተመልክቷል። Eንዲህ በሆነ ጊዜም ባለመሬቱ ከባለ ሕንፃው ጋር የተስማሙበትን ግምት በመክፈል ወይም በግምቱ ያልተስማማ Eንደሆነ በቁጥር 118A በተመለከተው መሰረት የሕንፃውን ግምት በመክፈል ሕንፃውን ማስለቀቅ Eንደሚችል ተደንግጓል።
ሕጉU በዚህ መልኩ የተቀረጸ ሲሆን በተያዘው ጉዳይ Aመልካች ለክሱ ምክንያት የሆነውን ቤት የ1ኛ ተጠሪ ባለቤት የ2ኛ Eና 3ኛ ተጠሪዎች ደግሞ Aባትና Aውራሽ የሆኑት Aቶ Aድነው Aወቀ በነበራቸው መሬት ላይ Aመልካች ቤት Eንዲሰሩ ፈቅደውላቸው ቤቱን የሰሩ መሆኑ” የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በውሳኔው ላይ Aስፍሯል።
ከላይ በተቀጠሰው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1179/2/ መሰረት በልላ ሰው መሬት ላይ ቤት /ሕንፃ/ የሰራ ሰው የሕንፃውን ግምት ተቀብሎ ሕንፃውን ለባለመሬቱ ለማስረከብ የሚገደደው ባለመሬቱ ሳይቃወም ሕንፃውን የሰራ በሚሆንበት ጊዜ 203 204 ነው። ነገር ግን በተያዘው ጉዳይ Aመልካች ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት የሰራው የ1ኛ ተጠሪ ባለቤትና የቀሪዎቹ ተጠሪዎች Aውራሽ የሆኑት ሟች Aቶ Aድነው Aወቀ ሳይቃወሙ በቀሩበት ሁኔታ ሳይሆን ይልቁንም ፈቃዳቸውን ሰጥተዋል በተባለበት ሁኔታ ከመሆኑም በላይ ሕጉ በወጣበት ዘመን ግለሰቦች በመሬት ባለቤትነት ረገድ መብት የነበራቸው ቢሆንም Aሁን ባለው ሁኔታ ደግሞ በI.ፍ.ድ.ሪ. ሕገ መንግሥት መሬት በግል ባለቤትነት መያዙ ቀርቶ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት Eንዲሆን የተደረገ ስለሆነ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ተጠሪዎች የመሬቱ ባለቤት ስለሆኑ Aመልካች በመሬቱ ላይ የሰራውን ቤት የዋጋ ግምቱን ¼ኛ ከተጠሪዎች ተቀብለው ቤቱን ያስረክቡ በማለት የሰጠው ውሣኔ በዚህ ረገድ ከነበረው ሕግም ሆነ ከሕገ መንግሥታችን ጋር የተጣጣመ ሆኖ Aልተገኘም። የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህንኑ ሳያርም መቅረቱ የሕግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.
የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
Aመልካች ለክሱ ምክንያት የሆነውን ቤት ለተጠሪዎች ላያስረክቡ Aይገባም ተብሎ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።