No summary available.
መ.ቁ. 275A6 ሐምል 19 ቀን 1999 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ Aብዱልቃድር መሐመድ Aብዱራሂም Aህመድ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- Eነ ሣሙኤል ውብሸት - ቀረቡ ተጠሪ፡- ብዙነህ በላይነህ - Aልቀረበም መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀረብ የቻለው Aመልካቾች ተጠሪ በይዞታችን ላይ የፈጠረው ሁከት ይወገድልን የሚል Aቤቱታ ለጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት Aቅርበው ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን Aከራክሮ ተጠሪ በAመልካቾች ላይ የፈጠረው ሁከት ላወገድ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቶ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የሶማል ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የከፍተኛ ፍ/ቤቱን ውሣኔ በመሻር ሁከት የለም በማለት ውሣኔ በመስጠቱ Aመልካቾች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዳዩ ለሰበር ችሎት Eንዲቀረብ በተሰጠው ትEዛዝ ተጠሪ የAመልካቾች Aቤቱታ ደርሷቸው መልስ የሰጡ ሲሆን Aመልካቾችም የመልስ መልስ በመስጠት Aቤቱታቸውን Aጠናክረው ተከራክረዋል።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ Aመልካቾች በጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በጅጅጋ ከተማ ቀበል A6 የሚገኝና የምንኖርበት ቤት በAዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሶ ቀበልው የሚያስተዳድረውና ላለፉት 2A ዓመታት በተከራይነት ኖረንበታል። ይሁን Eንጂ ተከሣሽ ይሄው ቤት የAውራሼ የሟች ወ/ሮ ተዋበች ዘርፉ ነው በማለት Eኛ በልለንበት ይህንኑ ከቀበልው Aስተዳደር በኪራይ የያዝነውን ቤት Eየተገለገለበት ሰለሆነ የተፈጠረው ሁከት ይወገድልን በማለት ጠይቀዋል።
ተጠሪም በበኩሉ በሰጠው መልስ ለክሱ መነሻ ምክንያት የሆነው ቤት ከAክስቱ በውርስ የተላለፈለት ንብረት መሆኑን በመግለጽ Aቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ቤቶች የጅጅጋ ከተማ Aስተዳደር መሆናቸውን ከሣሾችም በEነዚሁ ቤቶች በሕጋዊ መንገድ Eየኖሩ Eንደሆነ ከቀረበው ማስረጃ ማረጋገጥ የተቻለ ስለሆነ በተከሣሽ በኩል የተፈጠረው ሁከት በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1149(3) መሰረት Eንዲወገድ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ክርክሩን በይግባኝ የተመለከተውም የሶማል ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን Aከራክሮ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ቤቶች በAዋጅ ያልተወረሱ ስለመሆናቸው የሚመለከተው የቀበል Aስተዳደር ያረጋገጠ ከመሆኑም በላይ ይግባኝ ባይ (ተጠሪ) የቤቱ ባለንብረት የነበሩት ግለሰብ ወራሽ መሆናቸው ባቀረቡት ማስረጃ ስለተረጋገጠ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በተጠሪ በኩል የተፈጠረው ሁከት ላወገድ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ ከጭብጡ ያፈነገጠ ነው በማለት ሽሯል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችሎትም Aቤቱታው ለሰበር ቀረቦ መታየት Aለበት በማለት ትEዛዝ የሰጠው ለክርከሩ ምክንያት የሆነውን ቤት የቀበልው Aስተዳደር Eያከራየ ገቢ ይሰበስብ ነበር ከተባለ በAዋጅ Aልተወረሰም በሚል የተጠሪ የውርስ ሀብት ነው ¾መባሉ” Aግባብነƒ ለማጣራት ሲሆን ከዚሁ Aኳያም Aቤቱታው Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
Aመልካቾች በጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረቱት ከጅጅጋ ከተማ ቀበል Aስተዳደር በተከራይነት የምንኖርበትን ቤት ተጠሪ ወራሽ ነኝ በማለት ያለAግባብ ይዘው የሚገኙ ስለሆነ የተፈጠረው ሁከት ይወገድልን በማለት ነው።
ሁከት ይወገድልኝ የሚል Aቤቱታ የሚያቀርብ ወገን በንብረቱ ላይ የይዞታ መብት Eንዳለውና በEርግጥም የሚያዝበት መሆኑ” ማረጋገጥ Eንደሚገባው ከፍ/ብ/ሕ/ቁ/114A ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል።
በተያዘው ጉዳይ Aመልካቾች ሁከት ተፈጥሮብናል ¾ሚሉuት” ቤት በኪራይ ውል መነሻነት ይዘው Eንደሚገኙና የይዞታ መብት Eንዳላቸው በጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ በማስረጃ Aረጋግጠዋል።
የAመልካቾች Aቤቱታ ሁከት ይወገድልን የሚል ከሆነ ክርክሩ የይዞታ መብትን /possessory action/ የሚመለከት በመሆኑ በጭብጥ ተይዞ Eልባት ላሰጠው የሚገባው ነጥብ ሁከት ተፈጥሯል ወይስ Aልተፈጠረም የሚለው ነው።
ይሁንና ተጠሪ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡት ክርክር ለክሱ ምክንያት የሆነው ቤት በውርስ የተላለፈልኝ የግል ቤቴ ሰለሆነ የAመልካቾች Aቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት Eንጂ ሁከት Aልፈጠርኩም በማለት Aይደለም።
ተጠሪ በባለቤትነት ረገድ የሚያነሱት ክርክር ሁከት ተፈጥሯል ወይስ Aልተፈጠረም ተብሎ ለሚያዘው ጭብጥ ተገቢነት የልለውና Eራሱን የቻለ ባለቤትነት” የመፋለም ክስ /petitory action/ በሚመለከተው ላይ Aቅርበው ከሚታይ በስተቀር ሁከት Eንዲወገድ በቀረበ ክስ የባለቤትነት ክርክር ማንሣት Aግባብነት Aይኖረውም። ስለሆነም የሶማል ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በተጠሪ በኩል ባለቤትነትን የመፋለም ክስ ባልቀረበበትና Aመልካቾች ሁከት ይወገድልን በማለት ባቀረቡት ክስ ተጠሪ የቤቱ ባለቤት ናቸው በማለት ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ሰህተት ሆኖ ተገኝቷል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 149/97 በየካቲት 16 ቀን 1998 ዓ.ም. ተጠሪ በAመልካቾች ላይ የፈፀመው ሁከት ይወገድ በማለት የሰጠው” ውሣኔ በማጽናት የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት 193 194 በመ/ቁ. A5/1/91/99 በኀዳር 2 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስላለበት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።