No summary available.
የካቲት 4 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- Aቶ ገ/EግዚAብሕር ከበደው - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ት ሰላዊት ወ/ገብርኤል - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ክርክር የተጀመረው በትግራይ ክልል በመቀል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን ተጠሪ በAመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ የሟች Eናቴ ወ/ሮ ድንቅነሽ ድምጹ ወራሽ ስሆን በAውራሽ ስም የተመዘገበውንና በመቀል ከተማ የሚገኘውን 1A ክፍል ቤት Eኔ በማላውቀው ሁኔታ ተከሣሽ ይዞ በማከራየት ላይ ስለሚገኝ የ13 ወር የቤት ኪራይ በጠቅላላው ብር 35,000 /ሰላሳ Aምስት ሺህ/ በመክፈል ቤቱን Eንዲያስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ተከሣሽም ቀርበው ለክሱ በሰጡት መልስ ከሳሽ የሟች ወ/ሮ ድንቅነሽ ድምጹ ልጅ መሆኗን Eንደማይክዱ ነገር ግን ከሟች ጋር በ1977 ዓ.ም.
ተጋብተን Aብረን ስንኖር ልጆች የወለድን ከመሆኑም በላይ ክስ የቀረበበትንም ቤት Aብረን ሰርተናል። የሚያከራክረው ቤትና ቦታ ግማሹ የራሴ ሲሆን ግማሹ ደግሞ የሟች ወ/ሮ ድንቅነሽ ድምጹ ስለሆነ ከሣሽ ከልሎች ወራሾች ጋር በመሆን ድርሻዋን ብትካፈል Aልቃወምም ብለው የቤት ኪራይን በተመለከተ ቤቱ በወር ብር 2AAA /ሁለት ሺህ/ ይከራይ Eንደነበረ Aምነው ነገር ግን ከሰኔ 29 ቀን 1995 ዓ.ም. Eስከ ሕዳር 1997 ዓ.ም. ድረስ ያለውን ሟች በሕይወት Eያለች በጋራ የተጠቀምንበት ሲሆን ቀሪውንም ከከሳሽ ጋር 187 188 በጋራ ስለተጠቀምንበት ክሱ ያለAግባብ ስለቀረበ ላሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶ ክስ ከቀረበበት ቤት መካከል 5 ክፍል ቤት የከሳሽ Eናትና ተከሣሽ በ1977 ዓ.ም. ከተጋቡ በኋላ በ1994 ዓ.ም. የተሰራ መሆኑ ስለተረጋገጠ ግማሹ የተከሳሽ ሆኖ ግማሹ ደግሞ ከሳሽን ጨምሮ ወራሾች Eንዲካፈሉት ቀሪው 4 ክፍል ቤት ደግሞ ከመጋባታቸው በፊት መሰራቱ ማስረጃ ስለተረጋገጠ ከሣሽና ልሎች የሟች ወራሾች Eንዲከፋፈሉት በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
Eንደዚሁም ቤቱ ያረፈበትን የቦታ ይዞታ በተመለከተ የቦታው ስፋት በማዘጋጃ ቤት ደንብ መሰረት ለሁለት ለማካፈል የሚቻል ከሆነ ግማሹን ከሳሽና ልሎች ወራሾች Eንዲወሰዱ ቀሪውን ግማሽ ደግሞ ተከሣሽ Eንዲወሰዱ የማዘጋጃ ቤት ደንብ ቦታውን ለሁለት ለማካፈል የማይቻል ከሆነም ቤቱና ቦታው ተሸጦ ከላይ በተመለከተው ዓይነት ወራሾችና ተከሣሽ Eንዲከፋፈሉ በማለት በAብላጫ ድምጽ ውሣኔ ሰጥቷል።
የAነስተኛው ድምጽ ደግሞ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የተሰራበት ቦታ የከሳሽ Eናት ወ/ሮ ድንቅነሽ ድምጹ ተከሣሽን ከማግባቸው በፊት የነበራቸው ይዞታ ስለሆነ ተከሳሽ መብት የሚኖራቸው በዚህ ቦታ ላይ ከጋብቻ በኋላ ለተሰራዉ ቤት ግማሹን በተመለከተ ስለሆነ የዚህን ቤት ግምት ይዞ Eንዲሄድ ከሚወሰን በስተቀር ከጋብቻ በፊት የከሳሽ Eናት ባረጋገጡት ቦታና ቤት ላይ መብት ላኖረው Aይገባም የሚል ነው።
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ በAብላጫ ድምጽ የተሰጠውን የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ በመሻር የAነስተኛውን ድምጽ Aጽንቷል።
Aመልካች በዚሁ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የሰበር Aቤቱታ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ቢያቀርቡም መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aልተፈጸመም በማለት ችሎቱ Aቤቱታውን ሳይቀበለው ቀርቷል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችሎትም የቀረበለትን የሰበር Aቤቱታ መርምሮ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤትና የቦታ ይዞታን ክፍፍል Aስመልከቶ በትግራይ ክልል ጠ/ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ Aግባብነƒ ተጣርቶ ላወሰን የሚገባው መሆኑን በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን የሰበር Aቤቱታውም Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የተሰራበትን ቦታ የተጠሪ Eናት ወ/ሮ ድንቅነሽ ድምጹ ከAመልካች ጋር ከመጋባታቸው በፊት ይዘውት Eንደነበር በዚሁ ቦታም ላይ Aመልካችን ከማግባታቸው በፊት 5 ክፍል ቤት ሰርተው Eንደነበር ቀሪው 4 ክፍል ቤት ደግሞ ከAመልካች ጋር ከተጋቡ በኋላ Eንደተሰራ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ በማስረጃ ተረጋግጧል።
በልላ በኩልም በፍድራሉ የቤተሰብ ሕግም ሆነ በAዋጅ ቁጥር 33/91 በታወጀው የትግራይ ክልል የቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 85 መሰረት ከጋብቻ በፊት የነበረ የባልና ሚስት ንብረት የግል ንብረት Eንደሚሆን የተመለከተ ቢሆንም የከተማ ቦታን የመንግሥት ንብረት ለማድረግ በወጣው Aዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የከተማ ቦታ በግል ባለቤትነት ላያዝ Eንደማይችል ከመደንገጉም በላይ በI.ፍ.ዲ.ሪ ሕገመንግሥት Aንቀጽ 4A/3/ ላይ መሬት የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት Eንደሆነ ስለተደነገገ ግለሰቦች በመሬት ላይ የይዞታ መብት Eንጂ የባለቤትነት መብት ላኖራቸው ስለማይችል የተጠሪ Eናት ቤቱ በተሰራበት ቦታ ላይ Aመልካችን ከማግባታቸው በፊት የነበራቸው የይዞታ መብትም ቢሆን ከተጠሪ ጋር ከተጋቡ በኋላ በነበራቸው የቦታ ይዞታ ላይ ተጨማሪ ቤት Eንዲሰራ በፈቀዱት መሰረት Aራት ክፍል ተጨማሪ ቤት በጋራ ስለመስራታቸው የተረጋገጠ በመሆኑ ጋብቻው በሞት ምክንያት ሲፈርስ Aመልካች ከሚደርሳቸው ቤት በተጨማሪ በቦታው ላይ የይዞታ መብትም የሚገባቸው በመሆኑ በዚሁ መሰረትም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቦታውን ወራሾችና Aመልካች በማዘጋጃ ቤት ደንብ መሰረት Eኩል ለመካፈል የሚችሉ ከሆነ Eኩል Eንዲካፈሉት Eኩል ለማካፈል ካልተቻለም ተሸጦ ገንዘቡን 189 190 በውሣኔው መሰረት Eንዲካፈሉ በማለት የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ ሆኖ ሳለ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህንን ውሣኔ በመሻር በጋብቻ ጊዜ የተሰራውን ቤት የግማሹን የዋጋ ግምት Aመልካች ላወስድ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ ካለመሆኑም በላይ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎትም ይህንኑ ስህተት ሳያርም መቅረቱ የሕግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የመቀል ዞን ማEከላዊ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 1498 በሐምል 14 ቀን 1997 ዓ.ም. በAብላጫ ድምጽ የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕግ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።