No summary available.
ኀዳር 24 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የAዲስ Aበባ ከተማ መስተዳደር ታረቀኝ ሞላ ቀረበ።
ተጠሪ፡- ተክለማርያም መኮንን ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለAቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዳይ ተጠሪ ባቀረበው የቤት ይለቀቅልኝ ጥያቄ ላይ የተመሰረተ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀረመበት የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ተጠሪ የከሰሰው Aዳነ ገብሩ Eና ወ/ሮ ፈትለወርቅ ጌታቸው የተባሉትን ሰዎች ሲሆን፣ Aመልካች ክርክሩ ውስጥ የገባው ለክርክሩ መነሻ በሆነው ቤት ላይ የተነሣው ጥያቄ ይመለከተዋል ስለተባለ ጣልቃ Eንዲገባ ታዞ ነው። ተጠሪው ክስ የመሰረተውም በወረዳ 17 ቀበል 15 ክልል የሚገኝ ቁጥር 367/ለ/ የሆነው ቤት የግል ንብረቴ ሲሆን Aዳነ ገብሩ በተባለው ተከሣሽ በውል Aከራይቼው ሲጠቀምበት ቆይቶAል። በልላ በኩል ደግሞ ከኔ ፈቃድ ውጪ ለወ/ሮ ፈትለወርቅ ጌታቸው Aከራይቶታል። ስለዚህ ተከሣሾች ኪራዩን Eንዲከፍሉና ቤቱን Eንዲያስረክቡኝ ላወስንልኝ ይገባል በማለት ነው።
ፍ/ቤቱም ከተከሣሾች Eና ከጣልቃ ገቡ የቀረቡትን የመከራከሪያ ነጥቦች ከሰማ በኋላ፣ 1ኛ ተከሣሽ Eና ጣልቃ ገቡ ቤቱን ለከሣሽ ያስረክቡ፣ ከመስከረም ወር 1993 ዓ.ም. ጀምሮ Eስከ ሰኔ 3A ቀን 1994 ዓ.ም. ድረስ ያለውን የኪራይ ገንዘብም በAንድነትና በነጠላ ይክፈሉ ሲል ወስኖAል። በዚህ ውሣኔ ላይ ከAሁኑ Aመልካች ይግባኝ የቀረበለት የፍ/ከ/ፍ/ቤትም ውሣኔው ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቶAል። የሰበር Aቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው፡ የሰበር ችሎቱ Aመልካች ሚያዝያ 4 ቀን 1998 ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ የቀረበውን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን Aስቀርቦ ክርክሩን ሰምቶAል። Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲታይ የተወሰነው ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት የሰራው ባልተፈቀደለት የከተማ ቦታ ላይ ነው Eየተባለ ቤቱን ላረከብ ይገባል የመባሉን Aግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም በጭብጥነት የተያዘው ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር ይዘት መገንዘብ Eንደቻልነው ተጠሪ ቤቱን ሰርቻለሁ uሚል Kልላ ሰው በውል Aከራይቶ ከመገኘቱ በቀር በቦታው ላይ ቤት Eንዲሰራ Aግባብ ካለው ባለስልጣን የተፈቀደለት ወይም በቦታው የመጠቀም መብት ያገኘ መሆኑ” Kማስ[ǃ Áቀረበው ማስረጃ የለም። የሥር ፍ/ቤቶችም Aቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ የሰጡት ማስረጃ Aግኝተናል በማለት ሳይሆን፣ Aመልካች ቤቱ ያረፈበት የከተማ ቦታ ለመወረሱ /የመንግሥት ንብረት ለመሆኑ/ ማስረጃ Aላቀረበም የሚል ምክንያት በመስጠት Eና ቤቱ በሕገ ወጥ መንገድ የተሰራ ነው ከተባለም የሚመለከተውና ሥልጣን ያለው Aካል ነው ተገቢውን Eርምጃ የሚወስደው የሚል ትችት በማከል ብቻ ነው።
ለሁሉም ግልጽ Eንደሆነው የከተማ ቦታና ትርፍ ቤትን የመንግሥት ንብረት ለማድረግ የ¨ጣው Aዋጅ ቁ. 47/67 ከታወጀ ወዲህ የከተማ ቦታ የመንግሥት ሃብት ሆኖAል። ይህ ማለት በግል የሚያዝ የከተማ ቦታ የለም ማለት ነው። ግለሰቦች በከተማ ቦታ የመጠቀም /የመያዝ/ መብት የሚኖራቸው Aግባብ ባለው የመንግሥት Aካል /ባለስልጣን/ ሲሰጣቸው ነው። በተያዘው ጉዳይ የምናየው ግን ተጠሪ በቦታው ላይ ይጠቀም ዘንድ /ቤቱን Eንዲሰራ/ ሳይፈቀድለት ነው ቤት ሰርቼ Aከራየሁ የሚል ክርክር ያቀረበው። የከተማ ቤት Aሰራርና Aጠቃቀም” በተመለከተ በ¨ጣው Aዋጅ ቁ. 292/78 በAንቀጽ 7/1/ Eንደተደነገገው ከሚመለከተው ባለስልጣን ፈቃድ ሳይኖር የተሰራ የከተማ ቤት ሕጋዊነት Aይኖረውም። ቤቱ Eንዲወረስ ወይም EንÇ=ፈርስ Eንደሚደረግም ሕጉ ያመለክታል። ከዚህ Aንፃር የተጠሪ ክርክር ሲታይ ተቀባይነት ያለው Aይደለም። Aቤቱታ የቀረበበት ውሣኔም Eነዚህን ሁኔታዎች Eና ሕጉን ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
Aቤቱታ የቀረበባቸው የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 2A911 ታህሣሥ 22 ቀን 97 ዓ.ም. የሰጠው Eና የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 378A3 መጋቢት 13 ቀን 98 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪ ያቀረበው የቤት ልረከብ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
No topics extracted.
ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ።
መዝገቡ ይመለስ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ
የካቲት 4 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- Aቶ ገ/EግዚAብሕር ከበደው - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ት ሰላዊት ወ/ገብርኤል - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ክርክር የተጀመረው በትግራይ ክልል በመቀል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን ተጠሪ በAመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ የሟች Eናቴ ወ/ሮ ድንቅነሽ ድምጹ ወራሽ ስሆን በAውራሽ ስም የተመዘገበውንና በመቀል ከተማ የሚገኘውን 1A ክፍል ቤት Eኔ በማላውቀው ሁኔታ ተከሣሽ ይዞ በማከራየት ላይ ስለሚገኝ የ13 ወር የቤት ኪራይ በጠቅላላው ብር 35,000 /ሰላሳ Aምስት ሺህ/ በመክፈል ቤቱን Eንዲያስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ተከሣሽም ቀርበው ለክሱ በሰጡት መልስ ከሳሽ የሟች ወ/ሮ ድንቅነሽ ድምጹ ልጅ መሆኗን Eንደማይክዱ ነገር ግን ከሟች ጋር በ1977 ዓ.ም.
ተጋብተን Aብረን ስንኖር ልጆች የወለድን ከመሆኑም በላይ ክስ የቀረበበትንም ቤት Aብረን ሰርተናል። የሚያከራክረው ቤትና ቦታ ግማሹ የራሴ ሲሆን ግማሹ ደግሞ የሟች ወ/ሮ ድንቅነሽ ድምጹ ስለሆነ ከሣሽ ከልሎች ወራሾች ጋር በመሆን ድርሻዋን ብትካፈል Aልቃወምም ብለው የቤት ኪራይን በተመለከተ ቤቱ በወር ብር 2AAA /ሁለት ሺህ/ ይከራይ Eንደነበረ Aምነው ነገር ግን ከሰኔ 29 ቀን 1995 ዓ.ም. Eስከ ሕዳር 1997 ዓ.ም. ድረስ ያለውን ሟች በሕይወት Eያለች በጋራ የተጠቀምንበት ሲሆን ቀሪውንም ከከሳሽ ጋር 187 188 በጋራ ስለተጠቀምንበት ክሱ ያለAግባብ ስለቀረበ ላሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶ ክስ ከቀረበበት ቤት መካከል 5 ክፍል ቤት የከሳሽ Eናትና ተከሣሽ በ1977 ዓ.ም. ከተጋቡ በኋላ በ1994 ዓ.ም. የተሰራ መሆኑ ስለተረጋገጠ ግማሹ የተከሳሽ ሆኖ ግማሹ ደግሞ ከሳሽን ጨምሮ ወራሾች Eንዲካፈሉት ቀሪው 4 ክፍል ቤት ደግሞ ከመጋባታቸው በፊት መሰራቱ ማስረጃ ስለተረጋገጠ ከሣሽና ልሎች የሟች ወራሾች Eንዲከፋፈሉት በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
Eንደዚሁም ቤቱ ያረፈበትን የቦታ ይዞታ በተመለከተ የቦታው ስፋት በማዘጋጃ ቤት ደንብ መሰረት ለሁለት ለማካፈል የሚቻል ከሆነ ግማሹን ከሳሽና ልሎች ወራሾች Eንዲወሰዱ ቀሪውን ግማሽ ደግሞ ተከሣሽ Eንዲወሰዱ የማዘጋጃ ቤት ደንብ ቦታውን ለሁለት ለማካፈል የማይቻል ከሆነም ቤቱና ቦታው ተሸጦ ከላይ በተመለከተው ዓይነት ወራሾችና ተከሣሽ Eንዲከፋፈሉ በማለት በAብላጫ ድምጽ ውሣኔ ሰጥቷል።
የAነስተኛው ድምጽ ደግሞ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የተሰራበት ቦታ የከሳሽ Eናት ወ/ሮ ድንቅነሽ ድምጹ ተከሣሽን ከማግባቸው በፊት የነበራቸው ይዞታ ስለሆነ ተከሳሽ መብት የሚኖራቸው በዚህ ቦታ ላይ ከጋብቻ በኋላ ለተሰራዉ ቤት ግማሹን በተመለከተ ስለሆነ የዚህን ቤት ግምት ይዞ Eንዲሄድ ከሚወሰን በስተቀር ከጋብቻ በፊት የከሳሽ Eናት ባረጋገጡት ቦታና ቤት ላይ መብት ላኖረው Aይገባም የሚል ነው።
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ በAብላጫ ድምጽ የተሰጠውን የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ በመሻር የAነስተኛውን ድምጽ Aጽንቷል።
Aመልካች በዚሁ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የሰበር Aቤቱታ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ቢያቀርቡም መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aልተፈጸመም በማለት ችሎቱ Aቤቱታውን ሳይቀበለው ቀርቷል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችሎትም የቀረበለትን የሰበር Aቤቱታ መርምሮ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤትና የቦታ ይዞታን ክፍፍል Aስመልከቶ በትግራይ ክልል ጠ/ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ Aግባብነƒ ተጣርቶ ላወሰን የሚገባው መሆኑን በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን የሰበር Aቤቱታውም Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የተሰራበትን ቦታ የተጠሪ Eናት ወ/ሮ ድንቅነሽ ድምጹ ከAመልካች ጋር ከመጋባታቸው በፊት ይዘውት Eንደነበር በዚሁ ቦታም ላይ Aመልካችን ከማግባታቸው በፊት 5 ክፍል ቤት ሰርተው Eንደነበር ቀሪው 4 ክፍል ቤት ደግሞ ከAመልካች ጋር ከተጋቡ በኋላ Eንደተሰራ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ በማስረጃ ተረጋግጧል።
በልላ በኩልም በፍድራሉ የቤተሰብ ሕግም ሆነ በAዋጅ ቁጥር 33/91 በታወጀው የትግራይ ክልል የቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 85 መሰረት ከጋብቻ በፊት የነበረ የባልና ሚስት ንብረት የግል ንብረት Eንደሚሆን የተመለከተ ቢሆንም የከተማ ቦታን የመንግሥት ንብረት ለማድረግ በወጣው Aዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የከተማ ቦታ በግል ባለቤትነት ላያዝ Eንደማይችል ከመደንገጉም በላይ በI.ፍ.ዲ.ሪ ሕገመንግሥት Aንቀጽ 4A/3/ ላይ መሬት የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት Eንደሆነ ስለተደነገገ ግለሰቦች በመሬት ላይ የይዞታ መብት Eንጂ የባለቤትነት መብት ላኖራቸው ስለማይችል የተጠሪ Eናት ቤቱ በተሰራበት ቦታ ላይ Aመልካችን ከማግባታቸው በፊት የነበራቸው የይዞታ መብትም ቢሆን ከተጠሪ ጋር ከተጋቡ በኋላ በነበራቸው የቦታ ይዞታ ላይ ተጨማሪ ቤት Eንዲሰራ በፈቀዱት መሰረት Aራት ክፍል ተጨማሪ ቤት በጋራ ስለመስራታቸው የተረጋገጠ በመሆኑ ጋብቻው በሞት ምክንያት ሲፈርስ Aመልካች ከሚደርሳቸው ቤት በተጨማሪ በቦታው ላይ የይዞታ መብትም የሚገባቸው በመሆኑ በዚሁ መሰረትም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቦታውን ወራሾችና Aመልካች በማዘጋጃ ቤት ደንብ መሰረት Eኩል ለመካፈል የሚችሉ ከሆነ Eኩል Eንዲካፈሉት Eኩል ለማካፈል ካልተቻለም ተሸጦ ገንዘቡን 189 190 በውሣኔው መሰረት Eንዲካፈሉ በማለት የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ ሆኖ ሳለ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህንን ውሣኔ በመሻር በጋብቻ ጊዜ የተሰራውን ቤት የግማሹን የዋጋ ግምት Aመልካች ላወስድ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ ካለመሆኑም በላይ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎትም ይህንኑ ስህተት ሳያርም መቅረቱ የሕግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የመቀል ዞን ማEከላዊ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 1498 በሐምል 14 ቀን 1997 ዓ.ም. በAብላጫ ድምጽ የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕግ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።