No summary available.
መጋቢት 25 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ መድህን ኪሮስ ዓላ መሐመድ Aመልካች፡- የIትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ነገረ ፈጅ ሣሙኤል ክፍሉ ተጠሪ፡- ከበደ ታደሰ ተወካይ ግዛው ከበደ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
መዝገቡ የቀረበው Aመልካች የOሮሚያ ብሕራዊ ክልል የደቡብ ምEራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 9 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ Eና የOሮሚያ ብሕራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ህዳር 3 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ይታረምልኝ በማለት ታህሣስ 7 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር Aቤቱታ በመጠየቁ ነው። የክርክሩ መነሻ ተጠሪው ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ከOሮሚያ ብሕራዊ ክልል የማEድንና Iነርጅ ቢሮ በተሰጠኝ ፈቃድ መሰረት Aስቆፍሬ ያከማቸሁትን 10,850 /Aስር ሺ ስምንት መቶ ሃምሳ/ ሜትር ኪዩብ በAስራ ዘጠኝ መኪና Aስጭኖ የተጠቀመበት በመሆኑና ቦታውን በመያዝ የወደፊት ጥቅም ያስቀረብኝ ስለሆነ ብር 488,250 /Aራት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺ ሁለት መቶ ሐምሳ ብር/ Eንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት በሥር ተከሳሽ በሆነው የድራጋዶስ የመንገድ ሥራ ድርጅት ያቀረበው ክስ ሲሆን Aመልካቹ ወደ ክርክሩ የገባው ቦታው ከማናቸውም ሰው የይገባኛል ጥያቄ ነፃ ነው በማለት ያስረከበኝ የIትዮጵያ መንገድ ባለስልጣን ስለሆነ ቦታውን Aስመልክቶ ለተነሳው ክርክር በሶስተኛ ወገን ተከሳሽነት ጣልቃ Eንዲገባ ተከሳሹ በማመልከቱና ክሱን ያየው ፍርድ ቤት ትEዛዝ በመስጠቱ ነው። Aመልካች በሶስተኛው ወገን ተከሳሸነት ቀርቦ ክርክር የተነሣበትን ቦታ ለተከሳሹ ያስረከበው በAዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ሐላፊነት መሆኑንና ከሳሽም የመንግስት ሐብት ከሆነው መሬት ገረጋንቲ በማምረት የማገኘው የወደፊት ጥቅም ተቋርጦብኛል በማለት ለመክሰስ ህጋዊ መሰረት Eንደልለው ተከሳሽ ወስዷል ለተባለው ገረጋንቲ በሐላፊነት ላጠየቅ የማይችል መሆኑን በማንሣት ተከራክሯል። ክርክሩን በመጀመሪያ ያየው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተከሳሹ የከሳሽን 10,400 /Aስር ሺህ Aራት መቶ/ ኪዩብ ሜትር ገረጋንቲ የተጠቀመ ለመሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል በማለት የመንገድ ስራ ድርጅቱና Aመልካች የገረጋንቲው ጠቅላላ ዋጋ ብር 360,000 (ሦስት መቶ ስልሣ ሺ ብር) Eንዲከፍሉ ወስኗል። Aመልካች ይግባኝ Aቅርበው የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሣኔ በማሻሻል Aመልካች ከመንገድ ሥራ ድርጅቱ ጋር በጋራ ለተጣራው ብር 150,000 /Aንድ መቶ ሐምሳ ሺ ብር/ ይክፈሉ በማለት ወስኗል።
Aመልካች ጉዳዩን Aይቶ የመወሰን ስልጣን የፍርድ ቤቶች Aይደለም።
መሬቱንም ለመንገድ ስራ ድርጅቱ የሰጠነው በAዋጅ ቁጥር 80/1989 ድንጋጌ መሰረት ሆኖ Eያለና መሬት የመንግስት መሆኑ Eየታወቀ በህገ መንግስቱ Aንቀጽ 40 Eና በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 1460-1488 የተደነገጉት ድንጋጌዎች ታልፈው የተሰጠ ውሣኔ በመሆኑ በሰበር ላታይ ይገባዋል የሚል Aቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ተጠሪው በበኩሉ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን Aይቶ የመወሰን ስልጣን Aለው። የEኔ ክስ በገንዘቤና በድካሜ ያመረትኩትን 10,850 /Aስር ሺህ ስምንት መቶ ሀምሳ/ ኪዩብ ገረጋንቲ የAመልካች ወኪል Aላግባብ ወስዶ የተጠቀመበት በመሆኑ ዋጋውን ይክፈለኝ የሚል በመሆኑ በሰበር Aቤቱታው Aመልካች የጠቀሰው የህገ መንግስቱ ድንጋጌም ሆነ የፍታብሕር ህግ ድንጋጌች ከተያዘው ጭብጥ ጋር ግኑኝነት የላቸውም በማለት መልስ ሰጥቷል።
Aመልካች መሬቱን በሚመለከት ካልሆነ በቀር የመንገድ ሥራ ድርጅቱ 155 156 Aላግባብ ወስዶ ጥቅም ላይ Aውሎታል ለሚለው ገረጋንቲ ተጠያቂና ሐላፈ የምንሆንበት የህግ መሰረት የለም በማለት የመልስ መልስ Aቅርቧል።
በከፍተኛው ፍርድ ቤት Eና በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በኩል የተሰጠው ውሣኔና ግራ ቀኙ በሰበር ያቀረቡት ክርክር ይዘት ከላይ በAጭሩ የተገለፀ ሲሆን Eኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን Eንደመረመረነው Aመልካች የሶስተኛ ወገን ተከሳሽነት ጣልቃ Ñw ሆኖ በተከራከረበት ጉዳይ ፍርድ ቤቱ ለወሰነው የገንዘብ መጠን በAንድነትና በነጠላ ሐላፊ ነው ተብሎ የተሰጠው ውሣኔ ህጋዊ መሰረት Aለው ወይስ የለውም የሚለውን ጭብጥ ማየት Aስፈላጊ ሆኖ Aግኝተነዋል።
ከከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመረዳት Eንደሚቻለው ተጠሪው በመጀመሪያ ያቀረቡት ክስ ሁለት የክስ ምክንያቶች ያሉት ነው። የመጀመሪያው በሥር ተከሳሽ የነበረው ድራጋዶስ የመንገድ ሥራ ድርጅት 10,850 /Aስር ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ/ ኪዩብ ገራጋንቲ Aምር ቼ AስቀምÂ Eያለ ከEኔ ፈቃድ ውጭ Aላግባብ ስለተጠቀመበት ዋጋውን Eንዲከፍለኝ የሚል ሲሆን ሁለተኛው ተከሳሽ ስልጣን ካለው ከOሮሚያ የማEድንና Iነርጅ ቢሮ ፈቃድ Aውጥቼ በEጄ Aድርጌ ገረጋንቲ Eያመረትኩ ከምጠቀምበት ስፍራ በመግባት የምርት ሥራዬን ስላስተጓጎለ ከቦታው Aገኝ የነበረው የወደፊት ጥቅም ታስቦ ካሣ ላከፍለኝ ይገባል የሚል ነው።
No topics extracted.
በሥር ተከሳሽ የሆነው የድራጋዶስ የመንገድ ሥራ ድርጅት Aመልካችን በሶስተኛ ወገን ተከሳሸነት በክርክሩ ጣልቃ Eንዲገቡ የጠየቀው ተጠሪው በሁለተኛ ደረጃ ላቀረበው ክስ ነው። የመንገድ ሥራ ድርጅቱ ቦታውን ገረጋንቲ Eያመረትኩ Eንድጠቀምበት ከማናቸውም ሰው የይገባኛል ጥያቄ ነፃ መሆኑን AረጋÓጠው ያስረከቡኝ የወላሶ Ÿ}T Aስተዳደርና የIትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በመሆናቸው ከየቦታው Aላግባብ በመግባት የወደፊት ገቢዬን Aሳጥቶኛል የሚለውን የከሳሸ ክስ Aስመልክቶ Eነዚህ Aካላት በሶስተኛ ወገን ተከሳሽነት Eንዲጠሩ Aመልክቷል። ከዚህ Aንፃር ስንመለከተው Aመልካቹ ለተከሳሹ ቦታውን ያስረከበ መሆኑን Aልካደም። Aመልካች ቦታውን ለመንገድ ሥራ ድርጅት ያስረከበው በAዋጅ ቁጥር 89/1989 መሰረት መሆኑን በመጥቀስ ተክራክሯል። ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪው በቦታው ላይ ገረጋንቲ Eያመረትኩ Aገኝ የነበረው የወደፊት ጥቅም ስለተቋረጠ ተከሳሽ ካሣ ላከፍለኝ ይገባል በማለት ያቀረበውን ጥያቄ በማለፍ ተጠሪው ተከሳሽ Aላግባብ ወስዶ ተጠቅሞበታል ያለውንና በማስረጃ ተረጋግጧል ብሎ ፍርድ ቤቱ ያመነበትን 10,400 /Aስር ሺ Aራት መቶ/ ኪዩብ ሜትር ጠቅላላ ዋጋ Eንዲከፍል ወስኗል። በመሆኑም የሶስተኛ ወገን ጣልቃገብ ተከሳሽ ሐላፊነት የሚመነጨው ከተከሳሹ ሐላፊነት በመሆኑና በዚህ ጉዳይ ተከሳሽ Aላግባብ ቦታውን በመያዝ የከሳሽን የወደፊት ጥቅም በማስቀረትህ ካሣ ትከፍላለህ ተብሎ ያልተወሰነበት በመሆኑ Aመልካች በሐላፊነት የሚጠየቅበት ህጋዊ መሰረት የለም።
ሁለተኛው የተጠሪው የክስ ምክንያት ድራጋዶስ የመንገድ ሥራ ድርጅት Aላግባብ Eኔ ያመረትኩትን ገረጋንቲ ተጠቅሟልና ዋጋውን ይክፈለኝ የሚለው ነው። በዚህ ጉዳይ በሥር ፍርድ ቤት ተከሳሽ የሆነው የመንገድ ሥራ ድርጅት Aመልካች በሶስተኛ ወገን ተከሳሽነት ጣልቃ ገብ Eንዲሆን ያልጠየቀ ከመሆኑም በላይ የመንገድ ሥራ ድርጅቱ Eራሱን የቻለ የህግ ሰውነት ያለው ሥራውን በሚያከናውንበት ሰAት Aላግባብ በሰው ሐብትና ንብረት ላይ ጉዳት ቢያደርስ ተጠያቂ የሚሆነው የመንገድ ሥራ ድርጅቱ Eንጂ ኮንትራክት ሰጭ የሆነው Aመልካች ባለመሆኑ የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ሆነ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት Aመልካች ተከሳሹ Aላግባብ ለተጠቀመበት ገረጋንቲ በሶስተኛ ወገን ተከሳሽነት ከተከሳሹ ጋር የAንድነትና የነጠላ ሐላፊነት Aለበት በማለት የሰጡት ውሣኔ የፍታብሕር ሥነ ሥርAት ሕግ ቁጥር 43 ንUስ Aንቀጽ 1 ጋር የሚጣጣም ሆኖ Aላገኘውም።
የሥር ፍርድ ቤቶች በመጀመሪያ ተከሳሽ የሆነው የመንገድ ሥራ ድርጅት Aመልካቹ Eንዲያስረዳለትና በሐላፊነት Eንዲጠየቅለት ባልጠየቀበት ጉዳይ Eንደዚሁም በተከሳሽ በኩል ጥፋት Eንኳን ቢኖር Aመልካቹ በሶስተኛ ወገን ተከሳሽነት ቀርቦ ለጥፋቱ ተጠያቂ የሚሆንበት ከህግ ወይም ከውል 157 158 የመነጨ ግድታ መኖሩን ሣያረጋግጡና ¾ፍታHብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 43 ድንጋጌዎች” በመተላለፍ መሰረታዊ የህግ ስህተት ፈጽመዋል በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ውሣኔና የOሮሚያ ብሕራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ህዳር 3 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
Aመልካች ለተጠሪው ብር 150,000 /Aንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር/ የመክፈል ሐላፊነት የለበትም:: ለሚመለከተው ይፃፍ።
ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኛቸው የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
ይህ ፍርድ መጋቢት 25 ቀን 2000 ዓ.ም በሙሉ ድምጽ ተሰጠ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ቤ/ኃ የሰበር መ/ቁ. 354A3 ግንቦት 14 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ መድህን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ዓላ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- Aቶ ዓብዱልነጢፍ ሙሕ ከጠበቃው ጋር ቀርቧል ተጠሪ፡- 1/ትEግሥት በርሃ ወኪል - ቀረበ።
2/ ደምስስ ተማም ከጠበቃው ጋር ቀርቧል።
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የተነሣው በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ከጉራጌ ዞን የወልቂጤ Aካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን ግራ ቀኙ የንግድ መደብርን በተመለከተ ሲከራከሩ ቆይተው ፍ/ቤቱ Aመልካቹን ረቺ የሚያደርግ ውሣኔ ከሰጠ በኋላ ተጠሪዎች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6'ን' መሰረት Aድርገው ዳኝነት Eንደገና Eንዲታይ Aቤቱታ በማቅረባቸው መዝገቡ ዳግመኛ ተንቀሣቅሶ ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6/3/ መሰረት ለAመልካቹ መጥሪያ በተጠሪዎችና በቀበል በኩል ልኮለት ተጠሪዎቹ በመሐላ ቃል Aስደግፈው Aመልካቹ መጥሪያ ደርሶት ደረሰኝ Aልሰጥም ብሐል በሚል በልለበት ጉዳዩ Eንዲታይ ባቀረቡት Aቤቱታና የጎምሽ ቀበል ገ/ማ/ጽ/ቤት Aመልካቹ መጥሪያው ደርሶት ለመቀበሉ ደረሰኝ ለመሰጠት ፈቃደኛ Aልሆነም ሲል የፃፈውን ደብዳቤ በመመርኮዝ ጉዳዩን Aመልካቹ በልለበት መርምሮ ቀደም ሲል የሰጠውን ውሣኔ በመሻር ተጠሪዎቹን ረቺ ያደረገ ውሣኔ በታህሣሥ 3A ቀን 1999 ዓ.ም ሰጥቷል።
ከዚህ በኋላ Aመልካቹ በወልቂጤ Aካባቢ ከ/ፍ/ቤት መጋቢት 19 ቀን 1999 ዓ.ም የተፃፈ Aቤቱታ ይዞ በመቅረብ፣ በፍ/ቤቱ ቀርቤ ያልተከራከርኩት 159 160 መጥሪያ ሥላልደረሰኝ በመሆኑና ይህም በቂ ምክንያት በመሆኑ የሰጠው ውሣኔ ተነስቶ በጉዳዩ ላይ መልስ ሰጥቼበት ይወሰን ሲል ፍ/ቤቱን ጠይቋል።
የወልቂጤ Aካባቢ ከ/ፍ/ቤትም የAመልካቹን Aቤቱታ መርምሮ ሚያዝያ 16 ቀን 1999 ዓ.ም በሰጠው ትEዛዝ የተጠሪዎቹን በመሐላ ቃል ተደግፎ የቀረበ Aቤቱታና የቀበልውን ደብዳቤ በማውሣት መጥሪያ Aልደረሰኝም ተብሎ የቀረበው Aቤቱታ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78/2 ድንጋጌ መንፈስ ባሟላ መልኩ የቀረበ ባለመሆኑ Aቤቱታው ተቀባይነት የለውም ሲል መዝገቡን ዘግቶታል።
በዚህ ትEዛዝ ቅር የተሰኙት Aመልካች ቅሬታቸውን በየደረጃው ላሉ ፍ/ቤቶች ቢያቀርቡም የወልቂጤ Aካባቢ ከ/ፍ/ቤት የሰጠው ትEዛዝ Eስከ ክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ድረስ ባሉት ፍ/ቤቶች ፀንቷል።
የጉዳዩ Aመጣጥ ከላይ Eንደተዘረዘረው ሲሆን ይህ መዝገብ ለዚህ ለፍ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ላቀርብ የቻለውም Aመልካች ጥር 29 ቀን 2AAA ዓ.ም በተፃፈ የሰበር ማመልከቻ የቀበል ገ/ማህበሩ በቁ/A27/99 በሚያዝያ 16 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ የፍ/ቤት መጥሪያ ለAሁን Aመልካች Eንዳልሰጠኝ Eያረጋገጠ Eና መጥሪያውን ተቀብዬ Aልፈርምም ማለቴ በምስክር ሣይረጋገጥ የስር ፍ/ቤቶች መጥሪያ ደርሶት ለመከራከር ፈቃደኛ Aልሆነም በሚል ውሣኔ¨< ተነስቶ መከራከሪያዬን Eንዳላቀርብ መከልከላቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ሲሉ Aቤት በማለታቸው ነው።
ይህም ችሎት የAመልካቹን Aቤቱታ ተመልክቶ፣የስር ፍ/ቤቶች Aመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78/2/ መሰረት ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው በAግባቡ መሆን Aለመሆኑን ለመመርመር ተጠሪዎቹን Aስቀርቦ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክራቸውን Aካሂደዋል። Eኛም ጉዳዩን Eንደሚከተለው መርምረናል።
በመሰረቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78/2/ ተከሣሹ መጥሪያ በሚገባ ያልደረሰው መሆኑን ገልፆ ሲያመለክት Eና ፍ/ቤቱም ተከሣሹ ቀርቦ መልስ ያልሰጠው በበቂ ምክንያት መሆኑን የተረዳው ሲሆን ትEዛዙን ወይም ብይኑን በማንሣት ክርክሩ Eንደገና Eንዲሰማ Eንደሚያደርግ ይደነግጋል። በልላ በኩል ደግሞ ማንኛውም ግለሰብ ለቀረበበት ክስ መልስ የመስጠት መብት Eንዳለው ይታወቃል። ይህ ከሆነ ደግሞ Aንድ ፍ/ቤት የAንደኛውን ተከራካሪ መከራከሪያ ላለመስማት በተቻለው መጠን ይኸው ተከራካሪ በቀነ ቀጠሮው ያልቀረበው በቂ ባልሆነ ምክንያት መሆኑን የቀረቡለትን ማስረጃዎች በሚገባ መርምሮ ማረጋገጥ Eንደሚኖርበት መገንዘብ Aያዳግትም። በተያዘው ጉዳይ የሥር ፍ/ቤት Aመልካቹ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78 መሰረት መጥሪያ Eንዳልደረሰው ገልፆ Aቤቱታ ሲያቀርብም ቀድሞ ከተጠሪዎቹ በቀረበለት በመሐላ ቃል የተደገፈ ማመልከቻ ላይ Aመልካቹ መጥሪያ ተቀብሎ ደረሰኝ Aልሰጥም ሲል Aይተዋል ተብለው የቀረቡትን ምስክሮችም ሆነ መጥሪያው በቀበልው በኩል ሲሰጥ የነበሩƒ ምስክሮች Eንዲሰሙ Aላደረገም። Eንደውም ከዚህ በኋላ ቀደም ሲል የጎምሽ ቀበል ገ/ማ/Aስ/ጽ/ቤት የላከውን ደብዳቤ ፃፉ የተባሉት የቀበልው ሰራተኛ Eራሣቸው በሚያዝያ 16 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ ልላ ደብዳቤ ክስም ሆነ መጥሪያ ደርሶን የሰጠነው ነገር የለም ሲሉ በቀበልው ስም የሰጡት ማረጋገጫ መኖሩን ለመገንዘብ ተችሐል። ይህ በሆነበት ሁኔታ ደግሞ Aመልካቹ መጥሪያ ደርሶት ያለበቂ ምክንያት ስላለመቅረቡ ተረጋግጧል ለማለት Aይቻልም። ከዚህ ይልቅ ቀበልው ሚያዝያ 16 ቀን 1999 ዓ.ም የፃፈው ደብዳቤ የሚያረጋግጠው Aመልካቹ ቀርቦ ያልተከራከረው መጥሪያው ሣይደርሰው መሆኑ” ነው። በመሆኑም Aመልካቿ በሥር ፍ/ቤት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78 መሰረት ያቀረበው ማመልከቻ ተቀባይነት ላያገኝ ይገባው የነበረ መሆኑ” ተረድተናል። በAጠቃላይ የሥር ፍ/ቤቶች Aመልካቹ ቀርቦ ያልተከራከረው መጥሪያ ደርሶት ነው ሲሉ uደረሱበት መደምደምያ የAመልካቹን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ’¨< ብለናል።
ው ሣ ኔ 1/ Aመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78 መሰረት ያቀረቡት Aቤቱታ ውድቅ መደረጉ Aግባብ vKመሆኑ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የወልቂጤ Aካባቢ 161 162 ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/ A1871 ሚያዝያ 16 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝም ሆነ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 17917 ሰኔ 13 ቀን 1999 ዓ.ም Eና የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 18594 ጥር 2 ቀን 1999 ዓ.ም የከ/ፍ/ቤቱን ትEዛዝ በማጽናት የሰጧቸው ትEዛዞች ተሽረዋል። ይፃፍ።
2/ የወልቂጤ Aካባቢ ከ/ፍ/ቤት Aመልካች ቀርበው ያልተከራከሩት በበቂ ምክንያት TKƒU መጥሪያ ሣይደርሳቸው መሆኑን ተገንዝቦ ውሣኔውን በማንሣት የAመልካችን መከራከሪያዎች ተቀብሎ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የመሰለውን Eንዲወስን ጉዳዩ ተመልሶለታል።
3/ ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ።
4/ Eግዱ ተነስቷል። ለሚመለከተው ይፃፍ።
5/ መዝገቡ ተዘግቷል። ወደ መ/ቤት ይመለስ።