No summary available.
መጋቢት 12 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ሒሩት መለሰ መድህን ኪሮስ ዓላ መሐመድ Aመልካች፡- የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሰረተ ልማትና ቤቶች ጉዳይ ጽ/ቤት Aቶ ተስፋዬ ዘመድኩን ቀረቡ።
ተጠሪ፡- 1ኛ/ Aቶ ይርጋ ንጋኔ ቀረቡ።
2ኛ/ ወ/ሮ በላይነሽ ሙሽጋ ቀረቡ።
3ኛ/ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበል A2 Aስተዳደር ጽ/ቤት 4ኛ/ Aቶ ሰንበት ታደሰ - ቀረቡ።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
መዝገቡ የተከፈተው Aመልካቹ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር A5469 መጋቢት 6 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝና፣ የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሐምል 25 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ላታረም ይገባዋል በማለት ነሐሴ 16 ቀን 1999 ዓ.ም. Aቤቱታ ስላቀረበ ነው።
የክርክሩን መሰረታዊ ጉዳይ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሰጠው ትEዛዝና በAመልካችና በተጠሪዎች በኩል ለዚህ ፍርድ ቤት በጽሑፍ ከቀረበው ክርክር Eንደተረዳነው Aቶ ይርጋ ንጋኔና ወ/ሮ በላይነሽ መሸጋ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበል A2 Aስተዳደር ጽ/ቤት Eና Aቶ ስንብት ታደሰ 133 134 የግል ንብረታችን የሆነውን የቤት ቁጥር 271 ያላግባብ በመያዝ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበል A2 Aስተዳደር ጽ/ቤት Aከራይ Aቶ ስንብት ታደሰ ደግሞ ተከራይ በመሆን Eየተጠቀሙበት ስለሚገኙ ንብረታችንን Eንዲያስረክቡን በማለት ክስ Aቅርበው ሶስተኛ Eና Aራተኛ ተጠሪ መልስና የመከላከያ ማስረጃ ካቀረቡ በኋላ በሥር ፍ/ቤት ተከሣሾች የነበሩት ሶስተኛ Eና Aራተኛ ተጠሪዎች ለከሳሾች ማለትም ለAንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች ክስ ያቀረበበትን ቤት Eንዲያስረክቡ የፍድራል የመጀመያ ፍርድ ቤት ውሣኔ ሰጥቷል።
Aንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች የፍርድ ባለEዳዎች ማለትም ሁለተኛ Eና ሶስተኛ ተጠሪዎች Eንደ ፍርዱ Eንዲፈጽሙ ትEዛዝ Eንዲሰጥላቸው የAፈፃፀም ክስ Aቅርበው የፍርድ Aፈፃፀሙ በሒደት ላይ Eያለ Aመልካች የካቲት 29 ቀን 1999 ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ በAዲስ Aበባ ከተማ ውስጥ ያሉ ቤቶችን Aስመልክቶ የማስተዳደርና ተገቢውን ውሣኔ የመወሰን ስልጣን በAዋጅ ቁጥር 2/1995 Aንቀጽ 46 መሰረት የቤቶች መሰረተ ልማት ኤጀንሲ መሆኑ Eየታወቀ ኤጀንሲው በክርክሩ ውስጥ ተሣታፊ ሣይሆን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ቤት Aንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች የግል ንብረት ነው ተብሎ የተሰጠው ውሣኔ ተሰርዞ ወደ ክርክሩ ገብተን የመከላከያ ማስረጃችንንና መልሳችን Eንድናቀርብ ይፈቀድልን በማለት በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 358 መሰረት የፍርድ መቃወሚያቸውን Aቅርበዋል።
የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻው የቀረበለት ፍርድ ቤትም Aንድ ሰው የፍርድ መቃወሚያ ላያቀርብ የሚችለው በክርክሩ ሣይካፈል ሲቀርና የተሰጠው ፍርድ መብቱን የሚነካበት ሆኖ ሲገኝ ነው። በዚህ ጉዳይ ቤቱን በቀጥታ ሲያስተዳድር የነበረው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበል A2 Aስተዳደር ጽ/ቤት በተከሣሽነት ቀርቦ የተከራከረ በመሆኑ Aመልካች የተሰጠው ፍርድ Eንዲነሣና ወደ ክርክሩ Eንደገባ ያቀረበው ጥያቄ ተገቢ Aይደለም በማለት ትEዛዝ ሰጥቷል።
Aመልካች የቀበል Aስተዳደርና የAዲስ Aበባ ከተማ መሰረተ ልማትና የቤቶች ኤጀንሲ ሁለት የተለያዩ የሕግ ሰውነት ያላቸው የተለያየ ሥልጣንና ሀላፊነት በማቋቋሚያ Aዋጃቸው የተሰጣቸው ሆኖ Eያለ፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበል A2 Aስተዳደር ጽ/ቤት በተከሳሽነት ስለተከራከረ ፍርዱን ለመቃወም Aትችሉም በማለት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህንን ሰህተት Eንዲያርም ያቀረብነውን ይግባኝ የሰረዘው በAግባቡ ስላልሆነና የሥር ፍርድ ቤት የሥረ ነገር ሥልጣን ሣይኖረው የወሰነብን ስለሆነ በሰበር ላታረም ይገባዋል በማለት የጽሑፍ ክርክር ያቀረበ ሲሆን Aንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች በበኩላቸው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ A2 ቀበል Aስተዳደር በተከሣሽነት ስለተሣተፈ Aመልካቹ በክርክሩ Eንደተሣተፈ ይቆጠራል። የክፍለ ከተማው Aስተዳደር ነገረ ፈጆች ቀበልውን ወክለው የተከራከሩ ስለሆነ የፍርድ መቃሚያ ማመልከቻቸውን ውድቅ መደረጉ በAግባቡ ነው በማለት የተከራከሩ ሲሆን Aራተኛው ተጠሪ Eኔ ተከራይ በመሆኔ ከክርክሩ ውጭ Eንዲሆን በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ Aመጣጥና በዚህ ፍረድ ቤት ያቀረቡት የመከራከሪያ ሃሣቦች ከላይ የተገለፀው ሲሆን፣ Eኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን Eንደመረመርነው Aመልካች መልስና የመከላከያ ማስረጃው Eንዲሰማለትና በክርክሩ ተካፋይ ሣይሆን የተሰጠው ፍርድ Eንዲሰረዝለት ያቀረበውን ጥያቄ ጉዳዩን ያየው የፍድራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ውድቅ ያደረገው በግባቡ ነው ወይስ Aይደለም የሚለው ጭብጥ ማየት Aስፈላጊ ሆኖ Aግኝተነዋል።
No topics extracted.
የተሻሻለው የAዲስ Aበባ Aስተዳደር ቻርተር Aዋጅ ቁጥር 361/1995 ቀበል ማለት የከተማው ሦስተኛ ደረጃ የAስተዳደር Eርከን የሆነ የክፍለ ከተማ Aካል Eንደሆነ በAንቀጽ 2 ንUስ Aንቀጽ 6 LÃ ¾}Å’ÑÑ ሲሆን የቀበል Aስተዳደር ስልጣንና ተግባር” የሚደነግገው የAዋጁ Aንቀጽ 35 የቀበል Aስተዳደር በከተማው Aስተዳደር ሥር ያሉ ቤቶችን የመሸጥ የመለወጥ Eና ከዚህ ጋር ተመሣሣይ ውጤት ላያስከትሉ የሚችሉ ተግባራትን የማከናወን ስልጣንና ሀላፊነት ያለው ስለመሆኑ Aይደነግግም። ቻርተሩ በAዲስ Aበባ ከተማ ሥር ያሉ ቤቶችን የማስተዳደር የመሸጥና ልሎች ውሣኔዎችን 135 136 የሚሰጠው ለAዲስ Aበባ ከተማ Aስተዳደር ሲሆን የAዲስ Aበባ ከተማ Aስተዳደር በበኩሉ ይህንን ተግባር ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማከናወን የAዲስ Aበባ የመሰረተ ልማትና የቤቶች ኤጀንሲን በዋጅ ቁጥር 2/1995 Aቋቁሟል።
ከዚህም የምንረዳው የቀበል Aስተዳደር ለሕብረተሰቡ በቅርበት Aስተዳደራዊ Aገልግሎት ለመስጠት የተቋቋS የከተማው Aስተዳደር በሶስተኛ ደረጃ የሚገ˜ ሲሆን በከተማዋ Aስተዳደር ሥር ያሉ ቤቶችን Aስመልክቶ በሃላፊነት የሚከታተለውና ተገቢውን ውሣኔ መስጠት የሚችለው የመሰረተ ልማትና የቤቶች ጉዳይ ኤጀንሲ ነው። ሁለቱ የቀበል Aስተዳደርና ኤጀንሲው የተለያየ ባህሪ ስልጣንና ሀላፊነት Eንዲሁም ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው Aካላት ናቸው።
Aንድ ወደ ክርክር መግባት ያለበት Aካል በክርክሩ ተሣታፊ ሣይሆን የተወሰነው ውሣኔ መብቱን የሚነካ ሆኖ ሲገኝ ውሣኔው ከመፈፀሙ በፊት ውሣኔው Eንዲነሣና ክርክሩ `c< ባለበት Eንዲቀጥል መጠየቅ Eንደሚችል የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 358 ይደነግጋል። Aመልካች የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለAንደኛና Eና ሁለተኛ ተጠሪዎች Eንዲመለስ ውሣኔ የሰጠበትን ቤት የማስተዳደርና በቤቱ ላይ የተሻለ መብት Aለኝ የሚል ሰው ሲመጣ በሕግ Aግባብ የመፋለም ስልጣንና ኃላፊነት ያለው ከቀበል Aስተዳደር የተለየና ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው Aካል ነው።
Aመልካችና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበል A2 Aስተዳደር የAዲስ Aበባ ከተማ Aስተዳደር ከተማዋን ለማስተዳደር Aስፈላጊ ናቸው ብሎ ያደራጃቸው የመንግሥት Aካላት በመሆናቸው ብቻ ቀበልው በክርክሩ uተከሳሽነት በመሣተፍ Aመልካች በክርክሩ ተሣታፊ ሆኖ ማቅረብ የሚገባውን የመከላከያ መልስና ማስረጃ የማቅረብ Eድል Aግኝቷል ብሎ ለመደምደም Aይ‰ልም።
በመሆኑም Aመልካች በክርክሩ ውስጥ ተሣታፊ ሣይሆን Aሉኝ የሚላቸውን ማስረጃዎችና ልሎች የመከራከሪያ ሃሣቦች ሳያቀርብ የሚያስተዳድረውን ቤት ለAንደኛ Eና ሁለተኛ ተጠሪ Eንዲተላለፍ የተሰጠው ፍርድ Eንዲነሣና ክርክሩ Eሱ ባለበት Eንደገና Eንዲታይ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና በፍድራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aለበት በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
ክርክር የተነሣበትን ቤት Aስመልክቶ A5469 መጋቢት 6 ቀን 1999 ዓ.ም. የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ትEዛዝ ተሽሯል። ፍርድ ቤቱ Aመልካች የሚያቀርበውን ማናቸውንም የሕግና የፍሬ ጉዳይ ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ የመሰለውን ፍርድ ይሰጥ ዘንድ Ñ<Ç¿ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 341 መሰረት ተመልሷል። ይፃፍ።
የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ መዝገብ ነሐሴ 16 ቀን 1999 የሰጠው ትEዛዝ ተሽሯል።
በዚህ ክርክር Áወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ። ይህ ፍርድ ቤት መጋቢት 12 ቀን 2AAA ዓ.ም. በሙሉ ድምጽ ተሰጠ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ 137 138 የሰበር መ/ቁ. 336A6 የካቲት 2A ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ታፈሰ ይርጋ መድህን ኪሮስ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- የIትዮጵያ ልማት ባንክ - ነ/ፈጅ ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡- Eነ Aቶ ደጀኔ Aበበ (5ሰዎች) - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ጉዳÃ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ላቀርብ የቻለው Aመልካች የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት መጋቢት 4 ቀን 1999 ዓ.ም በEሸት የምግብ ውጤቶችና መኖ Aክሲዮን ማህበር የዱቄት ፋብሪካ ላይ ቀደም ብሎ የተሰጠው Eግድ መነሳት የለበትም በማለት የሰጠውን ትEዛዝ Eና የፍ/ከ/ፍ/ቤትም ሐምል 17 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ትEዛዝ ማጽናቱን በመቃወም ነው።
Aመልካች ይህን መሰረት በማድረግ ጥቅምት 11 ቀን 2AAA ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር Aቤቱታ ተጠሪዎች በEሸት የምግብ ውጤቶችና መኖ Aክሲዮን ማህበር ላይ የሒሣብ ይጣራልን ክስ Aቅርበው የዚሁ Aክሲዮን ማህበር ንብረት የሆነው ዱቄት ፋብሪካ Eንዳይሸጥ Eንዳይለወጥ የሚል የEግድ ትEዛዝ በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት Aሰጥተዋል። በበኩላችን ደግሞ ፋብሪካው ለAክሲዮን ማህበሩ ለሰጠነው የብር 14,569,AAA(Aስራ Aራት ሚላዮን Aምስት መቶ ስድሣ ዘጠኝ ሺህ) ብድር በAንደኛ ደረጃ መያዣነት የያዝነው በመሆኑና ብድሩም Eስካሁን ስላልተመለሰ ፋብሪካውን ሸጠን ገንዘባችንን ለማስመለስ Eንድንችል Eግዱ ይነሣልን በማለት ህዳር 12 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ጠይቀናል።
ሆኖም ጉዳዩን የያዘው የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ህዳር 28 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሒሣብ ማጣራቱ ውጤት Eስከሚታወቅበት ጊዜ ድረስ የተሰጠው የEግድ ትEዛዝ የሚነሣበትን ሁኔታ ስላላገኘን Aቤቱታውን Aልተቀበልንም፣ Eግዱ Eንዳለ ይቀጥል ሲል ትEዛዝ ሰጥቷል። Eንደገና ታህሣሥ 11 ቀን 1999 ዓ.ም የተሰጠው Eግድ Eንዲነሣልን ብናመለክትም Aሁንም ፍ/ቤቱ ራሴ የሰጠሁትን የEግድ ትEዛዝ መልሼ የማነሣበት ምክንያት የለም በማለት ጥያቄያችንን ሣይቀበለው ቀርቷል። በዚሁ ጉዳይ ለፍ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኝ ብናቀርብም ይህ ፍ/ቤትም የሥር ፍ/ቤቱን ትEዛዝ በማፅናት ይግባኛችንን ሰርዞብናል።
የሥር ፍ/ቤት ሒሣቡ Eስኪጠራ ድረስ Eግዱ Aይነሣም ሲል የሰጠው ትEዛዝ Aመልካች በAዋጅ ቁጥር 97/9A የተሰጠውን ስልጣን Eንዳይጠቀምበት ገደብ የሚጥል፣ መብት የሚነፍግ ከመሆኑም በላይ በAመልካች ባንክ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ነው ምክንያቱም የሒሣብ ማጣራቱ ሥራ Eንደተመለከትነው የጊዜ ገደብ ያልተቀመጠለት በመሆኑና የብድሩ ገንዘብ ወለድ Eየጨመረ የድርጅቱ ንብረትም Eየተበላሸ በመሆኑ Eግዱ ባለመነሣቱ ምክንያት የሚደርሰው ጉዳት በቀላሉ የሚገመት Aይደለም።
የAክሲዮን ማህበሩ ንብረት የሆነው ዱቄት ፋብሪካ የታገደው ለEዳው ተጠያቂ በሆኑ የማህበሩ Aባላት በሆኑት ሰዎች በነበረው የሒሣብ ክርክር መነሻነት ሲሆን ባንኩ የሚፈለገው ብር 22,AAA,AAA(ሃያ ሁለት ሚላዮን) ደግሞ የማህበሩ Aባላትና የAክሲዮን ማህበሩ የጋራ Eዳ ነው። ፍ/ቤቶቹ የሰጡት ትEዛዝ ደግሞ ባንኩ በAዋጅ ቁጥር 97/9A Eና 98/9A የተሰጠውን በብድር የሰጠውን ገንዘብ የመሰብሰብ ሥልጣን የሚገደብና በሕዝብና መንግሥት ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ነው።
በመሆኑም ሰበር ሰሚው ችሎት የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡትን ትEዛዝ በመሻር Eግዱ Eንዲነሣ Eንዲወሰንልን በማለት Aመልከቷል።
ተጠሪዎቹ (ፋብሪካው) ታህሣሥ 4 ቀን 2AAA ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ Eሽጉ የምግብ ውጤቶችና መኖ Aክሲዮን ማህበር ከAባላቱ መዋጮና 139 140 ከAመልካች ባንክ በተገኘው ብድር በብር 53,AAA,000 የተመሰረተ የዱቄት ፋብሪካ ነው። የAክሲዮን ማህበሩ ቦርድ ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ዓመታት Aባላትን ባለመጥራቱና ሪፖርትም ባለማቅረቡ የተነሣ በስር ፍ/ቤት የሒሣብ ይጣራ ክስ ተመሥርቷል። ንብረቱ Eንዳይባክን ፋብሪካው ሒሣቡ ተጣርቶ Eስከሚያልቅ ጊዜ ድረስ Eንዳይሸጥ Eንዳይለወጥ ታግዶ Eንዲቆይ ማድረግ Aስፈላጊ በመሆኑ ባቀረብነው ጥያቄ መሰረት በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የEግድ ትEዛዝ ተሰጥቶልናል። Aመልካችም Eግዱ Eንዲነሣለት Aመልክቶ በፍ/ቤቱ ተቀባይነት Aላገኘም። በዚሁ ትEዛዝ ላይ ይግባኝ ማለት ሲገባው Aመልካቹ Eንደገና ተመሣሣይ የሆነ የEግድ ይነሣልኝ ጥያቄ መጀመሪያ የEግድ ትEዛዝ ለሰጠውና Eግዱ Eንዲነሣ ጥያቄ ቀርቦለትም Eግዱ Aይነሳም ላለው ፍ/ቤት Aቅርቧል። ይህ ፍ/ቤት ራሱ የሰጠውን ትEዛዝ የሚያስለውጥ ልላ ትEዛዝ መስጠት ስለማይችል የAግድ ይነሣልን ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ በAግባቡ ነው። ፍ/ከ/ፍ/ቤትም የቀረበለትን ይግባኝ መሰረዙ የሚነቀፍ Aይደለም።
Eኛ የEግድ ትEዛዝ Eንዲሰጥልን ያመለከትነው የማጣራት ሥራው Eስኪያልቅ ጊዜ ድረስ ፋብሪካው ካልታገደ የሒሣቡ ጉድለትና የንብረቱ መባከን ሣይታወቅ ተሸፋፍኖ ይቀራል የሚል ስጋት ስላደረብን ነው። ፍ/ቤቶቹም የሰጡዋቸው ትEዛዞች ይህን ስጋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።
የማጣራት ሥራው በAፋጣኝ ላከናወን ያልቻለው Aመልካች የዱቄት ፋብሪካውን በሮች በመበየድ Aጣሪዎች Eንዳይገቡ በመከላከሉ መክንያት ነው።
ጉዳዩን Eየተመለከተ ያለው ፍ/ቤት Aመልካች ብይዱን Eንዲያነሣና የሒሣብ ማጣራት ሥራው Eንዲቀጥል ሲል ትEዛዝ የሰጠ ቢሆንም Eስካሁን የፍ/ቤቱ ትEዛዝ ተግባራዊ Aልሆነም።
በመሆኑም Aመልካች የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት መጀመሪያ Eግዱ Aይነሳም በማለት በሰጠው ትEዛዝ ላይ ይግባኝ ማለት ሲገባው Eንደገና የEግድ ይነሣልኝ ጥያቄ ማቅረቡ Aግባብ ባለመሆኑና የሥር ፍ/ቤƒ ደግሞ ራሴ የሰጠሁትን ትEዛዝ መልሼ ራሴ ላነሣው Aልችልም ያለው በAግባቡ በመሆኑ፣ ፍ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠው ትEዛ´ም የሚነቀፍበት ምክንያት ስለልለ በስር ፍ/ቤቶቹ የተፈፀመ የህግ ስህተት የለም። ሰበር ሰሚው ችሎትም ይህን ተመልክቶ በሥር ፍ/ቤቱቹ የተሰጡትን ትክዛዞች Eንዲያፀናልን ሲሉ Aመልክተዋል።
Aመልካችም የመልስ መልሱን በማቅረብ በAቤቱታው የተጠቀሱትን ክርክሮች ለማጠናከር ሞክሯል።
በበኩላችን ደግሞ በAመልካቹ የቀረበውን የEግድ ይነሣልኝ ጥያቄ የሥር ፍ/ቤቶች ውድቅ ማድረጋቸው በAግባቡ ነው ወይስ Aይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን Eንደመረመርነውም ተጠሪዎች ባቀረቡት መልስ የዱቄት ፋብሪካው የተመሰረተው ከAመልካች ባንክ በብድር በተገኘው ገንዘብ ጭምር መሆኑን ስላመኑና ለዚህ በብድር ለተገኘው ገንዘብም ፋብሪካው በAንደኛ መያዣነት Aልተመዘገበም ብለው ስላልካዱ Aመልካቹ ያቀረበው የEግድ ይነሣልኝ ጥያቄ በAግባቡ መሆኑን ተገንዝበናል።
የሥር ፍ/ቤቱ መጀመሪያ የሰጠው የEግድ ትEዛዝ ደግሞ በAክሲዮን ማህበሩ Aባላት መካከል የሒሣብ ይጣራልን ክስ ቀርቦ በክርክር ላይ ባሉበት ጊዜ ከAባላቱ በAንዱ ወገን ሒሣቡ ሣይጣራ ፋብሪካ Eንዳይሸጥ ለመከላል Eንጂ በብድር ምክንያት በመያዣነት የያዘው ባንክ ገንዘቡን ለማስመለስ በማሰብ Eንዳይሸጠው ለመከልከል Eንዳልሆነ ከትEዛዙ መንፈስ ለመረዳት ችለናል።
Aመልካች ባንክ በዋስትና የያዘውን ንብረት በመሸጥ በብድር የሰጠውን ገንዘብ ከነወለዱ የማስመለስ ስልጣን በAዋጅ ቁጥር 97/9A Aንቀጽ 3 Eና 4 መሰረት የተሰጠው በመሆኑ በዋስትና በያዘው ፋብሪካ ላይ የተሰጠው Eግድ Eንዲነሣለት ጥያቄ ማቅረቡ በAግባቡ ነው። ሆኖም የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የEግድ ይነሣልኝ ጥያቄው ሲቀርብለት Aመልካች በAዋጁ የተሰጠውን ሥልጣን መሰረት በማድረግ መብቱን ለማስጠበቅ Eንዲችል የEግድ ትEዛዙን ላያነሣለት ሲገባ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ የሕግ ስህተት SJ’<” ተመልክተናል።
መጀመሪያ Eግዱ Aይነሣም የሚል ትEዛዝ ተሰጥቶ Eያለ በዚሁ ትEዛዝ ይግባኝ Eንደማለት ተመልሶ Eንደገና Aመልካች ለዚሁ Eግዱ Aይነሣም 141 142 ላለው ፍ/ቤት Eግዱ ይነሣልኝ ማለት Aይችልም ተብሎ በተጠሪ የቀረበውን ክርክር ስንመለከትም የተሰጠው የEግድ ትEዛዝ ጊዜያዊ Eንደመሆኑ መጠን ከጊዜ በኋላ ከሁኔታዎች ጋር በማገናዘብ ላሻሻል፣ ላነሣ ወይም ላሰረዝ የሚችልበት ምክንያት ሲኖር Aስቀድሞ የEግድ ትEዛዝ የሰጠው ፍ/ቤት Eግዱን Eንዲያነሣ ማመልከት Eንደሚ‰ልና ፍ/ቤቱም Eንደየሁኔታው Eግዱን ላያሻሽል፣ላያነሣ ወይም ጨርሶ Eንዲሰረዝ ላያደርግ Eንደሚችል በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 158 የተደነገገ በመሆኑ የተጠሪዎቹ ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ Aላገኘነውም።
በመሆኑም የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመጀመሪያም ይሁን በሁለተኛው ጊዜ የቀረበውን የEግድ ይነሣልኝ ጥያቄ ያለመቀበሉና የEግድ ትEዛዙን ያለማንሣቱ፣ ፍ/ከ/ፍ/ቤትም የሥር ፍ/ቤቱን ትEዛዝ ጉድለት የለበትም በማለት የቀረበለትን ይግባኝ መሰረዙ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ትEዛዞ‡ መሻር ያለባቸው Jነው Aግኝተናቸዋል።
ው ሣ ኔ 1- የፍ/መ/ፊ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 31653 መስከረም 24 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው የEግድ ትEዛዝና ህዳር 28 ቀን Eና መጋቢት 4 ቀን 1999 ዓ.ም Eግዱ Aይነሣም በማለት የሰጣቸው ትEዛዞች Eንደዚሁም የፍ/ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 55387 ሐምል 17 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል። Eግዱም ተነስቷል። ይፃፍ።
2- ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ።