No summary available.
ግንቦት 19 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብዱልቃደር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ ታፈሰ ይርጋ መድሕን ኪሮስ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- Aቃቂ ቃላቲ ክ/ከ/ቀ/10/11 A/ጽ/ቤት Aልቀረቡም ተጠሪ- Eነ ወ/ሮ ብዙወርቅ ሸዋንግዛው ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ቀጥሎ የተመለከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በAዲስ Aበባ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ተጠሪዎች በAመልካችና በሥር 2ኛ Eና 3ኛ ተከሳሾች ላይ ባቀረቡት ክስ ከወላጅ Aባታችን በውርስ የተላለፈልንን በAቃቂ ቃላቲ ክ/ከተማ ቀበል 10 ክልል የሚገኝ ቤታችንን 1ኛ ተከሳሽ ከAዋጅ 47/67 ውጭ ያለAግባብ በመያዝ ለ2ኛ Eና 3ኛ ተከሳሾች በማከራየት ላይ ስለሚገኝ ይህንኑ ያለ Aግባብ ይዘው የሚገኙትን ቤታችንን ለቀው Eንዲያስረክቡ ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
1ኛ ተከሳሽ የAሁን Aመልካች ቀርቦ በሰጠው መልስ ክስ የቀረበባቸው ቤቶች በAዋጅ 47/67 መሰረት የተወረሱ ወይንም ያልተወረሱ ለመሆናቸው የሚጠቁም ማስረጃ በ1983 ዓ.ም በመዘረፉ ምክንያት ማቅረብ Aልቻልንም።
በAሁኑ ሰAት ይህ ክስ መመስረቱ Aግባብነት የልውና ተከራዮችን የሚጐዳ ነው። ጉዳዩም መታየት ያለበት በፍ/ቤት ሳይሆን በÝራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በኩል ስለሆነ መዝገቡ ላዘጋ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የሥር 2ኛ Eና 3ኛ ተከሳሾችም በበኩላቸው ባቀረቡት መልስ ከሳሾች ቁጥራቸው 204(1) Eና 204/2/ የሆኑት ቤቶች ላመለሱልን ይገባል በማለት ቀደም ሲል ለወረዳ 27 ፍ/ቤት ክስ Aቅረበው ፍ/ቤቱም ጉዳዩን Aይቶ ለመወሰን በሕግ ሥልጣን የተሰጠው ለIትዮጵያ Ýራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ስለሆነ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለውም በማለት ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ በድጋሚ ለፍ/ቤቱ ክሱ መቅረቡ ከፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 5 Aኳያ ተቀባይነት ስለልለው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ Aቅርበዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የAዲስ Aበባ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዳዩ Aስቀድሞ ውሳኔ ያገኘ ነው ተብሎ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በተመለከተ የወረዳ 27 ፍ/ቤት ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን ያለው የIትዮጵያ Ýራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ነው ከማለት በስተቀር የፍሬ ጉዳይ ክርክሩን ተመልክቶ ውሳኔ ያልሰጠ በመሆኑ ክርክሩ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 5 ሥር ስለማይወድቅ በዚህ ረገድ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ Aግባብነት የለውም በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል። ከዚህም ልላ 1ኛ ተከሳሽ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት ሳይሆን የIትዮጵያ Ýራይቬታይዜሽን ነው በማለት ያቀረበውን መቃወሚያ Aስመልክቶም በAዋጅ 110/87 መሰረት ለኤጀንሲው ሥልጣን የተሰጠው በቃል ትEዛዝ፣ በቀላጤ ወይንም በመመሪያ Aንድ ንብረት ተወስዶ በሚገኝበት ጊዜ Eንደሆነ ስለተመለከተና ከሳሾች በዚህ መንገድ ቤቱ ተወስዶብኛል ያላሉ ስለሆነ መቃወሚያው ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ Aድርጓል።
ከዚህ በኋላም በፍሬ ጉዳይ ረገድ የተደረገውን ክርክር ከማስረጃው ጋር Aገናዝቦ መርምሮ ክስ የቀረበባቸው ቤቶች የተወረሱ ስለመሆናቸው በማስረጃ ያልተረጋገጠ ስለሆነ 1ኛ ተከሳሽ ከ2ኛ Eና 3ኛ ተከሳሾች ጋር ያደረገውን የኪራይ ውል በማቋረጥ ለከሳሾች ቤቱቹን Eንዲያስረክቡ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 5 ላጠቅስ የሚገባው Aንድ የክስ ምክንያት በተከራካሪ ወገኖች ወይም ከEነዚህ ወገኖች ጥቅም የሚያገኙ 129 130 3ኛ ወገኖች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ከተሰጠ በተመሳሳይ የክስ ምክንያት ክስ በሚቀርብበት ጊዜ ሲሆን በተያዘው ጉዳይ የቀድሞ ወረዳ 27 ፍ/ቤት የቤት ይለቀቅልኝ ክርክሩን ለማየት ሥልጣን ያለው ልላ Aካል ስለሆነ ጉዳዩን Aላስተናግድም በማለት በብይን መዝገቡን በመዝጋቱ በቀረበው የክስ ምክንያት ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ካለመስጠቱም በላይ በAዋጅ ቁጥር 361/95 Aንቀጽ 41/ረ/ መሰረት የከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የከተማው Aስተዳደር ከያዛቸው ቤቶች ጋር የሚቀርቡ ክሶችን ለማከራከር የሥረ ነገር ስልጣን ያለው በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት በዚህ ረገድ የቀረበውን መቃወሚያ ባለመቀበል ጉዳዩን Aይቶ መወሰኑ በAግባቡ ነው በማለት የሥር ፍ/ቤትን ውሳኔ Aጽንቷል።
የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ችሎትም የሰበር Aቤቱታ ቀርቦለት መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aልተፈጸመም በማለት Aቤቱታውን ሳይቀበለው ቀርቷል።
ለዚህ ችሎትም የሰበር Aቤቱታ የቀረበው ይህንኑ ለማስለወጥ ሲሆን ይህ ችሎትም የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ በሥር ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ Aመልካች ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት የሥረ-ነገር ሥልጣን የለውም በማለት ያቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተጠሪዎች ባሉበት ተጣርቶ ላወሰን የሚገባው መሆኑን በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
No topics extracted.
የሰበር Aቤቱታውም ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ Aኳያ Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
በAዲስ Aበባ ከተማ ነክ መ/ደ/ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ Aመልካች ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት የሥረ ነገር ሥልጣን የለውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበው ከAዋጅ ውጭ የተወሰደን ንብረት ባለቤትነት Aጣርቶ ለመመለስ በAዋጅ ቁጥር 110/87 መሰረት ሥልጣን የተሰጠው ለIትዮጵያ Ýራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ነው በማለት ሲሆን ፍ/ቤቱም መቃወሚያውን ሳይቀበለው የቀረው ለኤጀንሲው ሥልጣን የተሰጠው ንብረቱ በቃል ትEዛዝ በመመሪያ ወይንም በቀላጤ ተወስዶ በሚገኝበት ጊዜ Eንደሆነ በAዋጁ ላይ ስለተመለከተና ከሳሾች በዚህ መንገድ ክስ የቀረበበት ቤት ተወሰደብን ያላሉ ስለሆነ ፍ/ቤቱ ሥልጣን Aለው በማለት ነው።
በልላ በኩልም ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍ/ቤት የከተማ ነክ የመ/ደ/ፍ/ቤት ጉዳዩን ለማየት ሥረ ነገር ሥልጣን Aለው ያለው የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት Eንዳለው ክስ የቀረበበት ቤት በቀላጤ፣ በመመሪያ ወይንም በቃል ትEዛዝ ተወስዷል ስላልተባለ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን Aለው በማለት ሳይሆን የከተማው Aስተዳደር ከያዛቸው ቤቶች ጋር u}ÁÁ² የሚቀርቡ ክሶችን ለማከራከር የሥረ ነገር ሥልጣን ያለው የA/Aበባ ከተማ ነክ ፍ/ቤት Eንደሆነ በAዋጅ ቁጥር 361/95 Aንቀጽ 41 ላይ የተመለከተ ስለሆነ ፍ/ቤቱ ሥልጣን Aለው በሚል ነው።
ይሁንና ተጠሪዎች ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በቀላጤ፣ በቃል ትEዛዝ ወይንም በመመሪያ ተወስዶብናል ያላሉ በመሆኑ በA/ቁ. 110/87 መሰረት ጉዳዩ በIትዮጵያ Ýራይቬታይዜሽን በኩል የሚታይ Aይደለም መባሉ ተገቢነት የነበረው ቢሆንም በAዋጅ ቁጥር 361/95 Aንቀጽ 41/ረ/ ስር ለከተማ ነክ ፍ/ቤት ሥልጣን የተሰጠው የA/Aበባ ከተማ Aስተዳደር በባለቤትነት ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች Ò` ተያይዘው የሚቀርቡ ጉዳዩችን በተመለከተ ስለሆነና ይህም ባለቤትነቱ የከተማው Aስተዳዳር ስለመሆኑ ክርክር ሳይኖርበት ከባለቤትነት በመለስ የሚነሱ ክርክሮችን በተመለከተ Eንደሆነ መገንዘብ የሚቻል ሲሆን በተያዘው ጉዳይ ተጠሪዎች ለክሱ ምክንያት የሆነው ቤት በውርስ የተላለፈልን የግል ቤታችን ነው በማለት ባለቤትነትን የመፋለም ክስ /petutory action/ ያቀረቡ በመሆኑና በቤቱ ባለቤትነት ላይም ክርክር Eስከቀረበበት ድረስ ከተጠቀሰው የAዋጁ ድንጋጌ Aኳያ የከተማ ነክ ፍ/ቤት የሥረ ነገር ሥልጣን ላኖረው የማይችል በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች የከተማ ነክ ፍ/ቤት ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን Aለው በማለት ተመልክተው ውሳኔ መስጠታቸው ለAዋጁ የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት Eንደሆነ መረዳት የተቻለ ስለሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
131 132