No summary available.
መጋቢት A9 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ Aብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- Aቶ መሐመድ Aብዲ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- Aቶ Aብዱራሂም Aብዲ - ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በሶማል ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት በጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን ተጠሪ በAመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በውርስ የተላለፈልኝን መሬት ተከሣሽ በጊዜያዊነት Eንዲገለገልበት ሰጥቼው ለመልቀቅ ፈቃደኛ ያልሆነ ስለሆነ Eንዲያስረክብ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን Aከራክሮ ለክሱ ምክንያት የሆነው ቦታ የተከሣሽ ስለመሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ስለሆነ በከሳሽ በኩል የቀረበው ክስ የማስረጃ ድጋፍ የለውም በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል።
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aክራክሮ የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ በመሻር ይግባኝ ባይ ክስ ባቀረበበት ቦታ ላይ መብት ያለው ስለመሆኑ ማስረጃው የሚያረጋግጥ ስለሆነ መ/ሰጭ ለይግባኝ ባይ ላመልስ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ሲሆን ይህ ችሎትም Aቤቱታው ለሰበር ላቀርብ ይገባል ብሎ ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
125 126 በቅድሚያም ችሎቱ የተመለከተው ተጠሪ በAመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ የክስ ምክንያት ያለው መሆኑን በተመለከተ ነው።
ከላይ Eንደተመለከተው ተጠሪ በጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት Aቤቱታ ዳኝነት የጠየቁት በውርስ የተላለፈላቸውን መሬት Aመልካች በጊዜያዊነት Eንዲገለገሉበት ሰጥተዋቸው ነገር ግን Aመልካች መሬቱን ለመመለስ ፈቃደኛ Aለመሆናቸውን ገልጸው Eንዲመልሱ ይወሰንልኝ በማለት ነው።
የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት” የመንግሥት ንብረት ለማድረግ በወጣው Aዋጅ ቁጥር 47/67 Aንቀጽ 6 መሰረት በከተማ ባለርስትና በከተማ ጭሰኛ መካከል ያለው ግንኙነት Eንደፈረሰ ጭሰኛው ለከተማ ባለርስት ከሚከፍለው ኪራይና ልላ ክፍያ Eንደዚሁም ከማንኛውም Aገልግሎትና Eዳ ነፃ Eንደሆነ ከመደንገጉም በላይ ማንኛውም ጭሰኛ በያዘው የከተማ ቦታ ላይ የይዞታ መብትም Eንደማይኖረው ተመልክቷል።
ለክሱ ምክንያት የሆነው መሬት በAዋጅ የመንግሥት መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ ተጠሪ Aመልካችን ለመክሰስ የማያበቃ መነሻ ምክንያት /Cause of action/ የልላቸው መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 231 ላይ Eንደተመለከተውም ማንኛውም ፍ/ቤት የክስ Aቤቱታ ሲቀርብለት ተከሣሽ የሆነው ወገን ክሱን Eንዲከላከል ከመጥራቱ በፊት ከሳሹ ክሱን ለማቅረብ የሚያስችል መነሻ ምክንያት ያለው ስለመሆኑና ፍ/ቤቱም Aቤቱታውን ተቀብሎ ለማየት ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ መመርመር ይኖርበታል።
በዚህም መሰረት ተጠሪ Aመልካች ላመልስልኝ ይገባል በማለት Aቤቱታ ያቀረበበት መሬት በተጠቀሰው Aዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የመንግሥት ሀብት ስለሆነ ከመነሻው Aቤቱታቸው የክስ ምክንያት Eንደልለው መገንዘብ ሰለሚቻል የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/I/ቁ.
231/1/ሀ/ መሰረት Aቤቱታው ተቀባይነት የለውም ማለት ሲገባው Aከራክሮ ውሣኔ መስጠቱ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ይህንኑ ስህተት ሳያርም መቅረቱ የሕግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ውሣኔ Eንደዚሁም የሶማል ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በዚህ ጉዳይ በሰኔ 13 ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ በAመልካች ላይ ያቀረበው ክስ የክስ ምክንያት የለውም ተብሎ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.