No summary available.
መጋቢት 07 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- Aቶ ኪዳኔ ገ/ጊዮርጊስ ተጠሪ፡- ወ/ሮ Aብርሃ ተስፋሁን መዝገቡን መርምረን ቀጥሎ የተመለከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በትግራይ ክልል ደቡብ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን ተጠሪ የAሁን Aመልካችን ጨምሮ በ7 ተከሳሾች ላይ ባቀረቡት ክስ ንብረትነቱ የሟች Aባታችንና የባለቤታቸው የወ/ሮ ሮማን ቢሆን የሆነውን በመቀል ከተማ የሚገኘውን ቤት ከ1-6 የተጠቀሱት ተከሳሾች ያለEኔ ፈቃድ ለ7ኛ ተከሳሽ /Aመልካች/ የሸጡ ስለሆነ ከሽያጩ ገንዘብ የEኔ ድርሻ ብር 9,375 ስለሚሆን ይህንኑ ገንዘብ Eንዲከፍሉኝ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
Aሁን በዚህ የሰበር ክርክር የልሉት የሥር ከ1-6 ተከሳሾች ቀርበው የይርጋ ክርክር ያነሱ ሲሆን የAሁን Aመልካችም ቀርበው ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት በሕጋዊ መንገድ Eንደገዙትና ውሉም በሚመለከተው መንግስታዊ Aካል የተመዘገበ መሆኑን ገልፀው ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የወረዳው ፍ/ቤት የሽያጩ ውል በሚመለከተው Aካል መጽደቁን የቀረበው ማስረጃ የሚያረጋግጥ ከመሆኑን በላይ የተሸጠውም በብር 3A ሺህ Eንደሆነ መገንዘብ ስለተቻለ ከዚህ ላይ የሟች ድርሻ ብር 15 ሺህ ስለሆነና ይህም 117 118 ለ8 ተወላጆች ሲከፋፈል የከሳሽ ድርሻ ብር 1875 ስለሚሆን ይህንኑ ገንዘብ ከ1-6 የተጠቀሱት ተከሳሾች Eንዲከፍሉ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ከሳሽ በዚህ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለመቀል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ከዚያም ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 337 መሰረት በሁለቱም ፍ/ቤቶች ይግባኙ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
ከዚህ በኋላም የሰበር Aቤቱታ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት Aቅርበው ሰበር ችሎቱም በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የጋራ የሆነውን የውርስ ንብረት በሽያጭ ለማስተላለፍ የሁሉም የጋራ ወራሾች ፈቃድ ማግኘት Aስፈላጊ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ከ1-6 የተጠቀሱት ተጠሪዎች የAመልካችን ፈቃድ ሳያገኙ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ለ7ኛ ተጠሪ በሽያጭ ማስተላለፋቸው Aግባብ Eንዳልሆነ በውሣኔው ላይ Aስፍሮ ከ1-6 ከተጠቀሱት ተጠሪዎች ጋር ውሉ Eንደፀና Eንዲቆይ ነገር ግን Aመልካችን በተመለከተ ውሉ Eንዲፈርስና የቤቱ 1/6ኛ በAመልካች ስም Eንዲመዘገብ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
በክልሉ ሰበር ችሎት 7ኛ ተጠሪ የነበሩት የAሁን Aመልካች በዚሁ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የሰበር Aቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ይህ ሰበር ችሎት የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ ተጠሪ ከቤት ሽያጩ ውል ድርሻዋ Eንዲከፈላት ባቀረበችው ክስ በEሷ ድርሻ ውሉ ላፈርስ ይገባል ተብሎ በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት መወሰኑ ተጠሪ ባሉበት ተጣርቶ ላወሰን የሚገባው ሆኖ በማግኘቱ በዚሁ መሰረት ተጠሪን ጠርቶ ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ Aቤቱታው ያስቀርባል የተባለበት ነጥብ ስለሆነ ከዚሁ Aኳያ Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
ጉዳዩ በወረዳ ፍ/ቤት ሲጀመር የAሁን ተጠሪ ዳኝነት የጠየቁት ከላይ Eንደተመለከተው ለክርክሩ ምክንያት ከሆነው የቤት የሽያጭ ገንዘብ ላይ ድርሻዬ ይከፈለኝ በማለት ነው። ተጠሪ ዳኝነት የጠየቁት በዚህ መልኩ ከሆነ በጭብጥነት የሚያዘውም ነጥብ በክሱ የጠየቁት ገንዘብ ላከፈላቸው ይገባል ወይንስ Aይገባም? የሚለው ነው። ከዚህ Aልፎ የቤት ሽያጭ ውሉ ላፈርስ ይገባል የሚለው ነጥብ ዳኝነት ያልተጠየቀበት ስለሆነ በጭብጥ የሚያዝ Aይሆንም። ጉዳዩን በመጀመሪያ የዳኝነት ሥልጣን የተመለከተውም የወረዳው ፍ/ቤት ውሣኔ የሰጠው ዳኝነት በተጠየቀበት ነጥብ ላይ ተመስርቶ ስለነበር ውሣኔው የሚነቀፍ Aልነበረም። ምክንያቱም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 182 ላይ Eንደተመለከተው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከራካሪ ወገኖች በግልጽ ባላመለከቱት ነገር ላይ ተመስርቶ ውሣኔ መስጠት Eንደማይችል ገደብ የተደረገበት ስለሆነ ውሉ ላፈርስ ይገባል የሚለው የክርክር ነጥብ / Point of Dispute/ ስላልነበር በዚህ ላይ ተመስርቶ ጭብጥ ላያዝ ስለማይችል በተጠየቀው ዳኝነት ላይ ተመስርቶ ለጉዳዩ Eልባት መስጠቱ Aግባብነት የነበረው ሲሆን ከዚህ በኋላም ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከቱት የክልሉ ከፍተኛና ጠቅላይ ፍ/ቤቶች ይግባኙን ሳይቀበሉ መቅረታቸው Aግባብ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ሰበር ችሎቱ ከAመልካች /ከAሁን ተጠሪ/ Aንፃር ውሉ ላፈርስ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ ከሙግት Aመራር Aኳያ Aግባብነት የልለውና የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ/ቁ. 17478 በግንቦት 10 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 16464 በጥቅምት 3 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ፣ የመቀል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ.
3782 በሰኔ 9 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ Eንደዚሁም የወረዳው ፍ/ቤት በመ/ቁ. 02166 በሰኔ 16 ቀን 1998 ዓ.ም 119 120 የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት ተመልሷል።