No summary available.
ሚያዝያ 2 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ሂሩት መለሰ መድህን ኪሮስ ዓላ መሐመድ Aመልካች፡- የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ነ/ፈጅ ቀርቧል።
ተጠሪ፡- ሴርኮ Eስራኤላ¨<ያን - ጠበቃ ቀርበዋል።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የተያዘው ክርክር የጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን ተጠሪ ከሣሽ በመሆን በAመልካቹ ላይ ሚያዝያ 12 ቀን 1996 ዓ.ም ያቀረበው ክስ፣ የAሁን Aመልካች ቤቴን ያለሕግ Aግባብ ይዞ በመቆየቱ ከመጋቢት 9 ቀን 1971 ዓ.ም ጀምሮ Eስከ የካቲት 9 ቀን 1994 ዓ.ም ላለው ጊዜ ያጣሁትን ጥቅም Eና የደረሰብኝን ጉዳት ብር 363,931/ሦስት መቶ ስልሳ ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ Aንድ/ ከወጪና ኪሣራ ጋር ይክፈለኝ የሚል ነው።
የAሁን Aመልካች ቀርቦ በሰጠው መልስ የተለያዩ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን ያቀረበ ሲሆን ከመቃወሚያዎቹም Aንዱ በAዋጅ ቁ.193/92 Aንቀጽ 2/3/ መሰረት ከAዋጅ ውጭ የተወረሱ ቤቶች በመንግስት Eጅ ለቆየበት ጊዜ ለታጣ ገቢ ክፍያ መጠየቅ ስለማይቻል ክሱ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤትም የቀረበውን መቃወሚያ ከግንዛቤ በማስገባት በሰጠው ውሣኔ ቤቱ በመንግስት Eጅ የቆየው ከAዋጅ ውጭ ተወስዶ በመሆኑ Aዋጅ ቁ.193/92 በዚህ ጉዳይ ተፈፃሚነት ይኖረዋል ስለዚህ ወደ ፍሬ ጉዳይ 113 114 ክርክሩ መግባት ሣያስፈልግ የተጠሪውን ክስ ውድቅ Aድርጌዋለሁ በማለት መዝገቡን ዘግቶታል።
ተጠሪው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፍ/ከ/ፍ/ቤት Aሰምተዋል።
የፍ/ከ/ፍ/ቤትም Aመልካችን Aስቀርቦ ግራ ቀኙን በማከራከር መዝገቡን መርምሮ በሰጠው ውሣኔ የክፍያው ጥያቄ ከዋጅ ቁ. 193/92 Aኳያ ተቀባይነት የለውም ተብሎ በስር ፍ/ቤት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ቢቀርብም የዚህ Aይነቱ መቃወሚያ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 244 ስር ያልተሸፈነና የፍሬ ጉዳይ ክርክር ስለሆነ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ ውሣኔ Eስከሰጠበት ድረስ በቁጥር 341 መሰረት ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ወደ ስር ፍ/ቤት የሚመልሰው ሆኖ Aልተገኘም፣ በልላ በኩል Aመልካቹ በስር ፍ/ቤት ያቀረባቸው ልሎች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ላይ ፍ/ቤቱ ብይን ሣይሰጥ በዚሁ ነጥብ ላይ ተመስርቶ የሰጠው ፍርድ Aመልካቹን ረቺ ቢያደረግም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ላይ ብይን ባለመስጠቱ Aመልካች መስቀለኛ ይግባኝ ያላቀረበ በመሆኑ ፍ/ቤቱ በራሱ Aስተያየት ላመለከተው የሚችል ሆኖ Aልተገኘም በሚል Aመልካቹ Aላግባብ ለበለፀገበት ብር 62,970 /ስልሣ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ/ ከተለያዩ ወጪና ኪሣራ ጭምር ለተጠሪው Eንዲከፍል ወስኗል።
የፍ/ከ/ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ Aመልካቹ ይግባኛቸውን ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል።
የፍ/ከ/ፍ/ቤት Eና የፍ/ጠ/ፍ/ቤት በዚህ ጉዳይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ፈጽመዋል በማለት Aመልካቹ ለዚህ ችሎት ሰኔ 22 ቀን 1999 ዓ.ም Aቤቱታ Aቅርበዋል።
ይህም ችሎት የAመልካቹን Aቤቱታ መሰረት በማድረግ በዚህ ጉዳይ Aመልካች ለፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ካቀረባቸው የመልስ መቃወሚያዎች ውስጥ Aንዱ ተቀባይነት Aግኝቶ ክሱ ውድቅ ቢደረግለትም መስቀለኛ ይግባኝ ካላቀረበ በስተቀር በቀሪዎቹ ነጥቦች ላይ የቀረበው ክርክር ላታይለት Aይገባም የመባሉን Aግባብነት ለማጣራት ተጠሪን Aስቀርቦ ግራ ቀኙን Aከራክሯል። መዝገቡንም Aግባበነት ካላቸው ህጐች Aንፃር መርምረናል።
ከመዝገቡ መረዳት Eንደተቻለው Aመልካች ለቀረበበት ክስ በስር ፍ/ቤት ቀርቦ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ያላቸውን Aምስት ነጥቦችን Eና መቃወሚያዎቹ ቢታለፉ በሚል ደግሞ ለክሱ ዝርዝር መልሱን Aቅርቧል። የመ/ደ/ፍ/ቤቱም በሰጠው ውሣኔ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከተባሉት ነጥቦች Aንዱን መርምሮ፣ ወደ ፍሬ ጉዳይ ክርክር መግባት ሣያስፈልግ ክሱን ውድቅ Aድርጌዋልሁ በማለት ወስኗል። ይህ ከሆነ ደግሞ ፍ/ቤቱ Aመልካቹ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሲል ያቀረበውን ነጥብ Eንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነቱ ተቀብሎ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ Aግባብ ቀሪ መቃወሚያዎችንና የፍሬ ጉዳይ ክርክሮችን ሣይመረምር ክሱን ውድቅ ማድረጉን ለመገንዘብ ተችሐል። በማንኛውም ቀመር የክሱ ውድቅ መደረግ Aመልካችን ተጠቃሚ ወይም ረቺ የሚያደርግ Eንደመሆኑ Aመልካቹ ቀሪ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች Eና የፍሬ ጉዳይ ክርክሮች ላመረመሩ ይገባ ነበር ሲል ይግባኝ Eንዲል የሚጠበቅበት Aይሆንም።
No topics extracted.
በልላ በኩል ደግሞ የፍ/ከ/ፍ/ቤት Aመልካቹ ይግባኝ ላጠይቅ ሲችል Aልጠየቀም በሚል የAመልካች መቃወሚያ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ Aይደለም ለዚህ ጉዳይም Aግባብነት የለውም በማለት Aመልካቹ ልሎቹን መከራከሪያዎች Eንዳመነ ያህል ልሎቹን መቃወሚያዎችና የፍሬ ነገር ክርክሮች ሣይመረመሩ ውሣኔ መስጠቱ የAመልካቹን ፍትህ የማግኘት መብት በEጅጉ የሚያጣብብ ሆኖ ተገኝቷል። በEርግጥ የፍ/ከ/ፍ/ቤት የቀረበው መቃወሚያ ከፍ/ብ/ስ/ህ/ቁ. 244 Aንፃር Aግባብነት የለውም ማለቱ የሚነቀፍ ባይሆንም፣ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ክሱን ውድቅ ለማድረግ የተከተለው Aካሄድ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተቀባይነት ሲያገኝ በሚፈፀመው Aግባብ ከመሆኑ Aንፃር ልሎች በፍ/ቤቱ ያልተመረመሩ መቃወሚያዎችና መከራከሪያዎች መኖራቸው ግልጽ ነው። ይህ በሆነበት ሁኔታ ከፍተኛ ፍ/ቤቱ መቃወሚያው በማንኛውም ምክንያት ውድቅ ሲደረግ Eንደሚፈፀመው ሁሉ 115 116 በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 341 መሰረት ቀሪ መቃወሚያዎችንና መከራከሪያዎችን መርምሮ የመሰለውን Eንዲወስን ወደ ስር ፍ/ቤት ላመልሰው ሲገባ Aመልካቹ ይግባኝ Aልጠየቁምና ቀሪ መከራከራያዎቻቸው Aይታዩም ሲል ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። የፍ/ጠ/ፍ/ቤትም የፍ/ከ/ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የለበትም ሲል ይግባኙን መሰረዙ በተመሣሣይ ሁኔታ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ነው።
ው ሣ ኔ
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 39329 ሚያዝያ 14 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ብይን ውድቅ መደረጉን ተገንዝቦ የቀሩትን መቃወሚያዎችና መከራከሪያዎች መርምሮ የመሰለውን Eንዲወስን ጉዳዩ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 341 መሰረት ይመለስለት ብለናል።
የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 40110 በግንቦት 30 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
የፍ/ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 27255 መጋቢት 26 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ ተሽሯል። ይፃፍ።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ። መዝገቡ ተዘግቷል።