No summary available.
መጋቢት 18 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ሒሩት መለሰ መድኀን ኪሮስ ዓላ መሐመድ Aመልካች፡- የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ - ነ/ፈጅ መሰረት የማነ ቀረበ።
ተጠሪ፡- 1/ የAቶ በቀለ ወ/ማርያም ወራሽ ወ/ሮ ዘለቃወርቅ በቀለ 2/ ወ/ሮ ዘውዲቱ Aርጋው ከጠበቃ ከሙሉጌታ 3/ Aቶ ደረጀ ዘለቀ ገብሩ ጋር ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ክርክር የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን፣ የAሁን ተጠሪዎች በAሁኑ Aመልካች Eና ኮ/ል ወንድወሰን ሰይፉ በተባሉ ግለሰብ ላይ በመስከረም 28 ቀን 1994 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት ክስ፣ የAሁኑ Aመልካች ባለቤትነቱ የAውራሻችን የሟች ሙሉነሽ ወ/ማርያም የሆነው በቀድሞው ወረዳ 2A ቀበል 29 የቤ/ቁ. 313 የሚገኘው ቤት በAውራሻችን ተመርጦ በAዋጅ ያልተወረሰ ሲሆን የAሁን Aመልካች ያለ ሕጋዊ ምክንያት ይዞ ለ2ኛው ተከሣሽ Eያከራየ በመጠቀም ላይ በመሆኑ ተከሣሾቹ ቤቱን Aስረክበው መስከረም A1 ቀን 1968 ዓ.ም. Eስከ ጥር A8 ቀን 1994 ዓ.ም. ድረስ ያጣነውን የኪራይ ገንዘብ በወር ብር 255 ሂሣብ በAጠቃላይ 74‚5AA ብር /ሰባ Aራት ሺህ Aምስት መቶ/ Eንዲከፍሉ ይወሰንልን ሲሉ ዳኝነት ጠይቀዋል።
የAሁን Aመልካች በግንቦት A2 ቀን 1994 ዓ.ም. በሰጠው መልስ ቤቱ በA/ቁ. 47/67 የተወረሰ መሆኑን ገልፆ ይህንን ቤት ይዞ ማስተዳደር ከጀመረ ከሃያ Aራት ዓመት በኋላ የቀረበው ክስ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን፣ ጉዳዩን የማየት ስልጣን ያለውም የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ Eንጂ ፍ/ቤት Aለመሆኑን ተጠሪዎቹ /የሥር ተከሣሾች/ ያቀረቡት ማስረጃ የቦታ ካርታ ሲሆን ይህም የተጠሪዎቹ Aውራሽ ቦታውን መግዛታቸውን Eንጂ የግል ቤታቸው መሆኑን Eንደማያሣይ፣ በልላ በኩል ደግሞ ቤቱ የተጠሪዎች Aውራሽ ነው ቢባል Eንኳን የኪራይ ገንዘቡን ለመመለስ በሕግ የተጣለበት ግድታ Aለመኖሩን በመዘርዘር ተከራክሯል።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤትም የAመልካችን መቃወሚያዎች ውድቅ በማድረግ የቂርቆስ ክ/ከተማ የመሬት Aስተዳደር ጽ/ቤትን ዋቢ በማድረግ ቤቱ ማኀደር የልለው መሆኑን ጠቅሶ ተከራካሪ ወገኖች ያቀረቡትን ማስረጃ በመመዘን ከሣሾች /የAሁን ተጠሪዎች/ Aውራሻቸውን ባለቤት ላያደርጋቸው የሚችሉ ጠቋሚ ማስረጃዎች ሲያቀርቡ Aመልካች ግን በረጅም ጊዜ ቤቱን Aስተዳድረዋለሁ ከማለት ውጭ ባለቤትነቱን ላያሣይ የሚችል ማስረጃ Aላቀረበም በሚል ቤቱ ለAሁን ተጠሪዎች Eንዲመለስ Eና የተጠየቀው የኪራይ ገንዘብ ብር 74‚5AA Eንዲከፈላቸው ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበበት የፍ/ከ/ፍ/ቤትም ይህንን ውሣኔ Aጽንቶታል።
Aመልካች በስር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለዚህ ችሎት የሰበር ማመልከቻውን በግንቦት 16 ቀን 1994 ዓ.ም. ጽፎ Aቅርቧል። የሰበር ማመልከቻውም ይዘት ሲጠቃለል የAሁን ተጠሪዎች በውርስ ይገባናል የሚሉት ቤት የAውራሻቸው የግል ቤት ለመሆኑና መርጠውት ምርጫቸው የፀደቀላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ሣይቀርብ የግል ቤቴ ወይም ንብረቴ ነው ለማለት የሚቻለው Aግባብ ካለው መንግሥታዊ Aካል የባለቤትነት ደብተር በማቅረብ ሆኖ ሣለ የሥር ፍ/ቤቶች Aመልካች ቤቱን ለተጠሪዎቹ Eንዲያስረክብ Eና የቤቱን ኪራይ ብር 74‚5AA ከነወለዱ Eንዲከፍል በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚል ነው። ይህም ችሎት የAመልካቹን Aቤቱታ ተመልክቶ ተጠሪን በማስቀረብ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክራቸውን Aድርገዋል። ችሎቱም የግራ ቀኙን ክርክር Eና የስር ፍ/ቤቶችን ውሣኔዎች Aግባብ ካላቸው ሕጎች ጋር Aገናዝቦ መርምሯል። Eንደተመረመረውም ከሁሉ Aስቀድሞ ምላሽ የሚሻው ጭብጥ የፍ/መ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች የቀረበለትን ክስ መርምሮ የመወሰን ስልጣን Aለው ወይ? የሚለው ሆኖ ተገኝቷል።
የAሁኑ የሰበር Aመልካች የክርክሩ መንስኤ የሆነው ቤት በA/ቁ.
47/67 ተወርሶ ሲያስተዳድረው መቆየቱን በመግለጽ የተከራከረ ቢሆንም የስር ፍ/ቤቱ ስለመወረሱ ተገቢው ማስረጃ Aልቀረበም በሚል ቤቱ ለAሁን ተጠሪዎች Eንዲመለስ ወስኗል። በመሰረቱ Aዋጅ ቁጥር 47/67ን መነሻ Aድርጎ Aላግባብ የምርጫ ቤቴ ተወስዷል በሚል የሚቀርቡ Aቤቱታዎች Aዋጁን ለማስፈፀም በተቋቋመው የሚኒስቴር መ/ቤƒ በኩል Eየተመረመሩ ተገቢውን ውሣኔ ማግኘት ያለባቸው ስለመሆኑ በAዋጁ ተመልክቷል። በተመሣሣይ ሁኔታ ምርጫ ቤቴን በቀላጤ፣ በቃል ትEዛዝ ወይም በመመሪያ ከሕግ ውጭ ተወሰደብኝ በሚል የሚቀርቡ Aቤቱታዎችን በA/ቁ. 11A/87 መሰረት KIትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቀርበው መወሰን Eንደሚገባቸው በሕጉ ተመልክቷል። ከEነዚህ ክፍሎች የሚሰጡ የባለቤትነት ማስረጃዎችን መሰረት Aድርገው በሚቀርቡ የባለቤትነት ጥያቄዎች ላይ ፍ/ቤቶች Eንደነገሩ ሁኔታ ስልጣን ከሚኖራቸው በቀር ተወርሰዋል ተብለው በመንግሥታዊና ሕዝባዊ ተቋማት ቁጥጥር ስር ያሉ ቤቶች ይመለሱልኝ Eንዲሁም ውዝፍ ኪራይ ይከፈለኝ በሚል የሚቀረቡ Aቤቱታዎችን መሰረት Aድርገው ፍ/ቤቶች የቤቱን መወረስና Aለመወረስ ለማረጋገጥ ማስረጃዎችን መርምረው የሚደርሱባቸው መደምደሚያዎች ¾›ስፈፃሚ Aካላቱን ስልጣን Eና ተግባር በግልጽ የሚቃረን ከመሆኑም በተጨማሪ ለፍ/ቤቶች በሕግ ያልተሰጠ ስልጣን ነው። በተያዘው ጉዳይ የAሁን ተጠሪዎች ክርክር በተነሣበት ቤት ላይ ከAስፈፃሚ Aካላቱ የባለቤትነት ማረጋገጫ ባላቀረቡበት ሁኔታ የAሁን ተጠሪዎችን ባለቤት ላያደርጓቸው የሚችሉ ጠቋሚ ማስረጃዎች Aቅርበዋል በሚል ለፍ/ቤቶች ባልተሰጠ የስልጣን ክልል በመግባት Aመልካች በAዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሰዋል ሲል ያቀረበውን መከራከሪያ ውድቅ በማድረግ ቤቱ ለተጠሪዎች ይመለስ ሲሉ መወሰናቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
No topics extracted.
111 112 ው ሣ ኔ
Aመልካች ክርክር የተነሣበትን ቤት ለመመለስም ሆነ ውዝፍ ኪራይ ለመክፈል Aይገደድም ብለናል።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ክርክር ያስነሣው በቀድሞው ወረዳ 2A ቀበል 29 የቤት ቁጥር 313 የሆነው ቤት በA/ቁ/ 47/67 ተወርሷል Aልተወረሰም የሚለውን ጭብጥ የመመርመር ስልጣን የለኝም ብሎ ክሱን በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 231/1/ለ/ መሰረት ወድቅ ላያደርገው ሲገባ Aከራክሮ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ በመ/ቁ.
148A6 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የሰጠው ትEዛዝ ተሽሯል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ