No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 3A631 ኀዳር 1A ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ወ/ሮ ዘቢዳ ሙሣ - ጠበቃ ወርቅዬ ዓባይነህ ተጠሪ፡-
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀረብ የቻለው ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት የሥር 2ኛ ተከሣሽና የAሁን Aመልካች ለተጠሪዎች ላያስረክቡ ይገባል ተብሎ በበታች ፍ/ቤቶች በመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት Aመልካች ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ የAሁን ተጠሪዎች በAሁን Aመልካችና በሥር 2ኛ ተከሣሽ በድሬዳዋ ከተማ ከፍተኛ 3 ቀበል 15 Aስተዳደር ጽ/ቤት ላይ ባቀረቡት ክስ በድሬዳዋ ከተማ ከፍተኛ 3 ቀበል 15 ክልል የሚገኘውና ቁጥር 722 የሆነው ቤት ከሣሾች በውርስ የተላለፈልን ባለቤት ስንሆን Aባታችን በሞት ከተለየ ጊዜ ጀምሮ 2ኛ ተከሣሽ ለ1ኛ ተከሣሽ Aከራይቶ ስለሚገኝ Eንዲያስረክበን በተደጋጋሚ ተጠይቆ ፈቃደኛ ያልሆነ ስለሆነ በሕገወጥ መንገድ ይዘው Aከራይና ተከራይ በመሆን በEጃቸው የቆየበትን ከሳሾች ስም ካዛወርንበት ጊዜ ጀምሮ የቤቱን ኪራይ ባልተነጣጠለ ኃላፊነት Eንዲከፍሉና ቤቱን Eንዲያስረክቡ ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
የከሳሾች ክስና ማስረጃ ለተከሳሾች ደርሶ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና ለፍሬ ጉዳዩም ሙሉ መልስ በመስጠት ተከራክረዋል።
በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የተነሣው ክርክርም ከAዋጅ ውጭ የተወሰዱ ንብረቶችን ባለቤትነት በማጣራት የመመለስ ሥልጣን የተሰጠው ለIትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ስልሆነ ፍ/ቤቱ ይህን ጉዳይ ለማየት ሥልጣን የለውም። Eንደዚሁም ጉዳዩ በፍ/ቤት መታየት የሚችል ነው ከተባለም ሥልጣኑ የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ሳይሆን የድሬዳዋ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው የሚል ነው።
የመቃወሚያ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክሩን መርምሮ ከሣሾች ክስ ያቀረቡት ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት 2ኛ ተከሣሽ በሕገወጥ መንገድ ለ1ኛ ተከሣሽ Eያከራየ ስለሆነ ላለቁልን ይገባል በማለት Eንጂ ስለመወረሱ ያነሱት ክርክር ስለልለ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን Aለው፣ የድሬዳዋ ከተማ ነክ ፍ/ቤትም ይህን ጉዳይ ለማየት ሥልጣን የለውም በማለት መቃወሚያውን ሳይቀበለው የቀረ ሲሆን ግራ ቀኙ በፍሬ ጉዳይ ረገድ ያደረጉትን ክርክር መርምሮ ለክሱ ምክንያት የሆነውን ቤት ተከሳሾች ለከሳሾች ላያስረክቡ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የድሬዳዋ ፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዟል።
የሥር 1ኛ ተከሳሽም በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የሰበር Aቤቱታ በማቅረባቸው ፍ/ቤቱ የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ ለክሱ ምክንያት የሆነው ቤት ለተጠሪዎች Eንዲመለስ መወሰኑ Aግባብነቱ ለሰበር ችሎት ቀርቦ ላጣራ Eንደሚገባ በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም ነጥብ ይህን ጉዳይ ለማየት የድሬዳዋ ፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ሥልጣን ነበረውን? የሚለው በመሆኑ ይህንኑ ነጥብ በጭብጥነት ይዘን Aቤቱታውን Eንደሚከተለው መርምረናል።
ተጠሪዎች በድሬዳዋ ፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በAመልካችና በሥር 2ኛ ተከሣሽ የቀበልው Aስተዳደር ላይ ክስ የመሰረቱት በውርስ የተላለፈልንን የግል ቤት በሕገወጥ መንገድ ይዘው ስለሚገኙ ያስረክቡን በማለት ነው። ተጠሪዎች በክሳቸው ቤቱ በAዋጅ ሳይወረስ በሕገወጥ መንገድ ተይዞብናል የሚሉ ከሆነ 107 108 በልላ Aነጋገር ቤቱ ከAዋጅ ውጭ ተወርሷል ማለት ነው። ከAዋጅ ውጭ ተወርሰዋል የሚባሉ ቤቶችን ደግሞ ባለቤትነታቸውን በማጣራት ውሣኔ ለመስጠት በAዋጅ ቁጥር 11A/87 ለIትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን Aጀንሲ ሥልጣን ተሰጥቶታል። በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 231/1/ለ/ ላይ Eንደተመለከተው ክስ የቀረበለት ፍ/ቤት በክሱ ላይ የተገለጸው ጉዳይ ከሥልጣኑ ውጭ መሆኑን ሲረዳው ተከሳሹን ሳያስጠራ የክስ Aቤቱታውን በመሰረዝ ከሳሹን ማሰናበት ይኖርበታል። በዚሁ መሰረት ተጠሪዎች ባቀረቡት Aቤቱታ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በሕገወጥ መንገድ Eንደተወሰደባቸው የገለጹ ስለሆነና በሕገወጥ መንገድ ተወስዷል ከተባለም በልላ Aገላለጽ ቤቱ ከAዋጅ ውጭ ተወስዷል ማለት ስለሆነ የድሬዳዋ ፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ የሥረ-ነገር ሥልጣን Eንደልለው ተገንዝቦ ከመነሻውም Aቤቱታቸውን ላሰርዝ ሲገባ Aለመሰረዙ በAግባቡ ካለመሆኑም በላይ በዚህ ሁኔታ ተከሳሾችን ከጠራ በኋላ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን Eንደልለው በመግለጽ የመጀመሪያ ደረጃ መቃሚያ ሲቀርብለት መቃወሚያውን ተቀብሎ Aቤቱታውን ውድቅ ማድረግ ሲገባው ሳይቀበለው መቅረቱ Eንደዚሁም ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የድሬዳዋ ፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንኑ ስህተት Aለማረሙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የድሬዳዋ ፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. A223A በየካቲት 26 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ Eንደዚሁም የድሬዳዋ ፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. A29A2 በሚያዝያ 29 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የድሬዳዋ ፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ይህን ጉዳይ ለማየት የሥረ-ነገር ሥልጣን የለውም ተብሎ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።