No summary available.
ጥር 29 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ተገኔ ጌታነህ መስፍን Eቁበዮናስ Aብዱራሂም Aህመድ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- Eነ ወ/ሮ ሙሉነሽ Aለሙ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ከተማሽ ቸርነት - Aልቀረቡም።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው Aመልካቾች በተጠሪ ላይ ያቀረቡት ክስ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/5 መሰረት በበታች ፍ/ቤቶች ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ የAሁን Aመልካቾች በተጠሪ ላይ በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በAዲስ Aበባ ከተማ በወረዳ 9 ቀበል 07 ክልል የሚገኘውን ቁጥር 1288 የሆነውን ቤት በውርስ ያገኙት መሆኑን ገልፀው ይህንኑ ቤት ቆልፈን Eንደሄድን ተከሳሽ በሀይል በመክፈት ስለገቡበት Eንዲያስረክቡንና ኪራይም Eንዲከፍሉ ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
ተጠሪም በሰጡት መልስ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባነሱት ክርክር ከሳሾች በመ.ቁ. 02330 በዚሁ ቤት የሁከት ይወገድልን ክስ መስርተው ፍ/ቤቱም ውሣኔ የሰጠ ስለሆነ በተመሳሳይ ጉዳይ ድጋሜ ክስ መቅረቡ በAግባቡ ስላልሆነ ፍ/ቤቱ ውድቅ ላያደርገው ይገባል በማለት መልስ ሰጥተዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክሩን መርምሮ ተከሳሽ በዚህ ጉዳይ Aስቀድሞ ውሣኔ መስጠቱን ለማስረዳት ያቀረቡትን የፍ/ቤት ውሣኔ ፍ/ቤቱ Eንደተመለከተው ከሳሾች ወራሽነታቸውን ገልፀው ተከሳሽ ቤቱን ትልቀቅልን በማለት ክስ መስርተው ፍ/ቤቱም ውሣኔውን ሲሰጥ ይህንኑ ጭብጥ በመከተል ተከሳሿ ቤቱን በይዞታነት የምትጠቀምበት መሆኗን ከቀበልው Aረጋግጦ ከሳሾች Eንደ ክሳቸው ባለማስረዳታቸው ጥያቄያቸውን ባለመቀበል መዝገቡን Eንደዘጋ መረዳት የተቻለ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/5 መሰረት በፍርድ የተወሰነው ክርክር ሥረ-ነገርና የተያዘው ጭብጥ Aንድ ዓይነት ከሆነና ፍርድ የተሰጠበት ከሆነ ተከራካሪ ወገኖች ድጋሜ ክስ ማቅረብ Eንደማይችሉ ስለተደነገገ ከሳሾችም በዚህ መዝገብ ያቀረቡት ክስ Aስቀድሞ ከቀረበው ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ በAግባቡ የቀረበ Aይደለም በማለት ክሱን በብይን ሳይቀበለው ቀርቷል።
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የልለው ነው በማለት Aጽንቷል።
ይህ ሰበር ችሎትም የቀረበለትን Aቤቱታ መርምሮ Aመልካቾች በድጋሜ ያቀረቡት Aቤቱታ Aስቀድሞ ውሣኔ ያገኘ ስለመሆኑ ተጠሪ ባሉበት ተጣርቶ ላወሰን Eንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ ከላይ Eንደተጠቀሰው ጉዳዩ Aስቀድሞ ውሣኔ ያገኘ ነው? ወይንስ Aይደለም? የሚለው በመሆኑ ይህንኑ ጭብጥ ይዘን Aቤቱታውን Eንደሚከተለው መርምረናል።
በመ/ቁ. 02330 Aመልካቾች በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረቱት በወረዳ 9 ቀበል A7 ክልል ከወላጆቻችን በውርስ ያገኘነውና በይዞታችን Aድርገን 103 104 የምንጠቀምበት የቤት ቁጥር 1288 የሆነውን ቤታችንን በቁልፍ ቆልፈነው Eንዳለ Eንዳንገባ፣ Eንዳንወጣና Eንዳንገለገልበት በማድረግ ተከሳሽ ሁከት የፈጠረችብን ስለሆነ ሁከ~ Eንዲወገድና ቤታችንን ለቃ Eንድትወጣ ይወሰንልን በማለት ነው።
በልላ በኩልም ለዚህ የሰበር Aቤቱታ ምክንያት በሆነው መዝገቡ ላይ ያቀረቡት ክስ ደግሞ ከላይ Eንደተመለከተው ይህንኑ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ተጠሪ ቁልፉን ከፍተው በመግባት በኃይል የያዙት ስለሆነ ያስረክቡን በማለት ነው።
በሁለቱም መዝገቦች ላይ Aመልካቾች የጠየቁት ዳኝነት /Relief/ Aቤቱታ የቀረበበትን ቤት ለመረከብ ቢሆንም በAቤቱታቸው ላይ የጠቀሱት ዝርዝር ፍሬ ነገር ሲታይ ግን በመጀመሪያው መዝገብ የተፈጠረው ሁከት ተወግዶ ቤቱን Eንረከብ በማለት የጠየቁ Eንደመሆኑ ሁከት Aለ የለም የሚለው ነጥብ በጭብጥ ተይዞ የሚፈታ ሲሆን በልላ በኩልም በሁለተኛው መዝገብ ባቀረቡት Aቤቱታ ቤቱ ያለAግባብ የተወሰደባቸው መሆኑን በመግለጽ Eንዲመለስላቸው የጠየቁ በመሆኑ በዚህ መዝገብ በጭብጥ ላያዝ የሚችለው ፍሬ ነገር ሁከት Aለ ወይንስ የለም የሚል ሳይሆን ባለቤትነት የመፋለም ክስን /petitory action/ የሚመለከት በመሆኑ በጭብጥም ተይዞ የሚፈታው ፍሬ ነገር ይሄው ባለቤትነትን Aስመልክቶ የቀረበው ክስ ስለሚሆን በሁለቱ መዝገቦች ላይ የቀረበው ክርክር በጭብጥ የተለያየ ስለሆነ የሥር ፍ/ቤቶች Aስቀድሞ ውሣኔ ባገኘ ጭብጥ ላይ ድጋሜ ክስ መቅረቡ ተገቢ Aይደለም በማለት ሁለተኛውን ክስ ሳይቀበሉ መቅረታቸው የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 06644 ኅዳር 8 ቀን 1996 ዓ.ም የሰጠው ብይን Eንደዚሁም የፍድራል ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 26636 በመጋቢት 12 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
Aመልካቾች በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 06644 በተጠሪ ላይ ያቀረቡት Aቤቱታ Aስቀድሞ በመ.ቁ. 02330 ውሣኔ ካረፈበት የተለየ በመሆኑ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ግራ ቀኙ በፍሬ ጉዳይ ረገድ ያደረጉትን መርምሮ የመሰለውን ውሣኔ Eንዲሰጥ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 341 መሰረት ተመልሶለታል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።