No summary available.
ጥቅምት 14 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ መስፍን Eቁበዮናስ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- 1ኛ Aቶ ዳባ ደበል - ቀረቡ 2ኛ .. ደምሴ በዳዳ ቀረቡ 3ኛ ወ/ሮ Aለሚ ተ/ፃዲቅ ቀረቡ 4ኛ .. ደግነሽ ጫሞራ ቀረቡ 5ኛ ቄስ ኤፍሬም መኰንን ቀረቡ መልስ ሰጭ፡- የAቶ ደበበ ተፈራ ወራሾች 1ኛ ወ/ሮ ሸዋማማሽ ደበበ 2ኛ ሻ/ቃ ጌቱ ደበበ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር Aቤቱታ የቀረበው የAዲስ Aበባ ከተማ ሰበር ሰሚው ችሎት በመ/ቁጥር A3678 መጋቢት 7 ቀን 1999 ዓ.ም በሰጠው ትEዛዝ ላይ ቅር በመሰኘት ነው።
ጉዳዩም ባጭሩ Eንደሚከተለው ነው።
የAሁን መልስ ሰጭዎች ለሰበሩ Aቤቱታ መነሻ በሆነው ጉዳይ ከሣሽ የነበሩ ሲሆን ክሱን በቅድሚያ ተቀብሎ ላየው ለAዲስ Aበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ የAውራሻችን የAቶ ደበበ ተፈራ ንብረት የሆነውን በAቃቂ ከተማ የሚገኘውን የወፍጮ ቤት ድርጅት በወቅቱ የነበሩት የቀበል ተመራጮች ከፋፍለው ለAምስቱም Aመልካwች በመስጠታቸው Eና Aውራሻችን ከዚሁ ድርጅት በቀር ልላ ያልነበራቸው መሆኑን በማረጋገጥ 97 98 በAዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ይኸው ንብረት Eንዲመለስላቸው ያቀረቡት Aቤቱታ ተቀባይነት Aግኝቶ የከተማ ልማትና የቤት ሚ/ር በቁጥር 8A/ደ/2135/83 ንብረቱ Eንደመለስላቸው ተወስኗል። ስለሆነም ንብረቱን ለማስረከብ ፈቃደኞች ባለመሆናቸው በፍርድ ኃይል ላያስረክቡን ይገባል የሚል ሲሆን ለዚህም Aቤቱታቸው ማስረጃዎቻቸውን ዘረዝረው Aቅርበዋል።
የAሁን Aመልካwችም ይኸው ንብረት በAዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የተወረሰ በመሆኑ ለረዥም ጊዜ ከመንግሥት ተከራይተን ለመንግሥትም ኪራይ Eየከፈልን የምንኖርበት ንብረት በመሆኑ ልንከሰስ Aይገባም በማለት ተከራክረዋል።
የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ ክርክር ያስነሣው ንብረት ለመልስ ሰጭዎች Aውራሽ Eንዲመለስላቸው የተወሰነ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ቀርቧል። ማስረጃውም በሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር የተሰጠ ነው። በAዋጅ ቁጥር 47/67 Aንቀጽ 31 መሰረት Aዋጅን የማስፈፀም ሥልጣን የተሰጠው ለዚሁ የሥራና ቤቶች ሚ/ር በመሆኑ ንብረቱ ላመለስላቸው ይገባል። በልላ በኩል የAሁን Aመልካwች ቤቶቹ የተወረሱ ናቸው ከማለት በቀር ለመልስ ሰጭዎች Eንዲመለሱ Aልተወሰነም በማለት Aልተከራከሩም። ያልተመለሱ ስለመሆኑም በማስረጃ Aስደግፈው Aላስረዱም ስለሆነም ክስ የቀረበበትን ንብረት Aምስቱም Aመልካwች ለመልስ ሰጭዎች ያስረክቡ ሲል ወስኗል።
ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም በየደረጃው ላሉት ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት Eና ሰበር ሰሚው ችሎት ቢያቀርቡም Aቤቱታው ተቀባይነት የለውም በሚል
No topics extracted.