No summary available.
ግንቦት 14 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ መድህን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- የAፓርትማ 79/6 የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበር Eና የሥራ Aስፈጻሚ ኮሚቴ Aባላት ተጠሪ፡- ወ/ት ዘርAዳም Aሰጋኸኝ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ የሥነ ሥርዓት ህግን የተመለከተ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የAሁን ተጠሪ በAመልካች የሕብረት ቤት ስራ ማህበር ውስጥ በAባልነቴ ከተሰሩት ቤቶች መካከል ድርሻዬ የሆነውን ቤት የስራ Aስፈጻሚ Aባላት የሆኑት ግለሰቦች በወቅቱ ለEኔ ባለማስረከባቸው ምክንያት በቤቱ ላይ ለታየ ጉድለት ማሟያና ማሰሪያ ብር 80,000፣ /ሰማኒያ ሺህ ብር/ ቤቱን በወቅቱ ተረክቤ ቢሆን ኖሮ በማከራየት ላገኝ Eችል የነበረውን ጥቅም ብር 24,000፣ /ሃያ Aራት ሺህ ብር/ Eንዲሁም ልሎች ጉዳቶች በድምሩ 320,000/ሦስት መቶ ሃያ ሺህ ብር/ ላከፍሉኝ የገባል በማለት በፍደ/የመጀ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ነው። የAሁን Aመልካቾች በሰጡት መልስ ክሱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5 የሚታገድ ከመሆኑም በላይ በይርጋ የታገደ ነው በማለት ተከራክረዋል። ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ክሱ በይርጋ ይታገዳል ወይስ Aይታገድም? ጉዳዩ ከዚህ በፊት በውሳኔ ያለቀ ነው ወይ? የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2143 ከውል ውጪ በሆነ ኃላፊነት ጉዳት ደረሰብኝ የሚል ወገን ክሱን ማቅረብ ያለበት ጉዳቱ በደረሰ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መሆን 93 94 Eንዳለበት ስለሚደነግግና የAሁን ተጠሪ ደግሞ ክሱን ያቀረቡት ጉዳቱ ከደረሰ ከ13 ዓመት በኋላ ስለሆነ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው በማለት ብይን ሰጥቷል።
የAሁን ተጠሪ በዚህ ብይን ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍደ/ከፍ/ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ፍ/ቤቱ ይግባኙ የቀረበበት ጉዳይ ከዚህ በፊት በፍርድ ቤት የታየ ስለሆነ Eንደገና ዳኝነት ላጠየቅበት ስለማይገባ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5 ይግባኙ Aያስቀርብም የሚል ብይን ሰጥቶ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ በማጽናት ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል።
የAሁን ተጠሪ በዚህም ብይን ቅር በመሰኘት ለፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ Aቅርበው ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ የፍደ/ከፍ/ፍ/ቤት ይግባኙን Aያስቀርብም ለማለት የሰጠው ምክንያት የፍደ/የመጀ/ደ/ፍ/ቤት ከሰጠው ብይን ጋር የሚገናኝ Aይደለም፣ በAሁን ተጠሪ የቀረበውን ቅሬታ መሰረት ያደረገም Aይደለም፤
ፍ/ቤቱ መዝገቡን የዘጋው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 337 መሰረት በመሆኑ ፍርዱን የሰጠው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 342 ላይ Eንደተመለከተው የነገሩን ጭብጥ በመለወጥ ወይም በማሻሻል ነው ለማለት የሚቻልበት የህግ ምክንያት የለም፣ ይግባኙ Aያስቀርብም ማለትም ፍርድ መስጠት ማለት Aይደለም፤ በመሆኑም ፍ/ቤቱ በAንድ በኩል ይግባኙ Aያስቀርብም Eያለ በልላ በኩል ደግሞ የይግባኝ ክርክር ሰምቶ ላሰጥ የሚችለውን ፍርድ መስጠቱ ትክክል Aይደለም፤
በAጠቃላይ ፍ/ቤቱ የተከተለው Aካሄድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉ ከተደነገገው የክርክር Aመራር ሥነ ሥርዓት የወጣ በመሆኑ ይግባኙ የቀረበለት የፍደ/ከፍ/ፍ/ቤት ተሸሯል፣ የፍደ/የመጀ/ደ/ፍ/ቤት ብይን በሰጠበት የይርጋ ጥያቄ ላይ ተመስርቶ የቀረበለትን ይግባኝ በመመርመር ተገቢ ነው የሚለውን ትEዛዝ/ውሳኔ/ Eንዲሰጥበት ጉዳዩ ለፍደ/ከፍ/ፍ/ቤት ተመልሶለታል በማለት ወስኗል።
የሰበር Aቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ ለማስለወጥ ሲሆን ይህ ችሎት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔዎች Aግባብ ካለው ህግ ጋር Aገናዝቦ በመመርመር የፍደ/ከፍ/ፍ/ቤት በፍደ/የመጀ/ደ/ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ይግባኝ ቀርቦለት ይግባኙን መልስ ሰጭን መጥራት ሳያስፈልግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 337 SW[ƒ የሰረዘው በመሆኑ በዚህ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ሁለተኛ ይግባኝ ለፍደ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቀርቦ መታየቱ Aግባብ መሆን Aለመሆኑ ተጣርቶ መወሰን ያለበት ነጥብ ሆኖ ስላገኘው ጉዳዩ ለሰበር Eንዲቀርብ Aድርጓል።
መዝገቡን Eንደመረመርነው የፍደ/የመጀ/ደ/ፍ/ቤት የቀረበለትን ክስ በይርጋ የታገደ ነው በማለት ብይን ሰጥቶ የፍደ/ከፍ/ፍ/ቤት ደግሞ ጉዳዩን በይግባኝ ከተመለከተ በኋላ ጉዳዩ ከዚህ በፊት በፍርድ ቤት የታየ ስለሆነና Eንደገና ዳኝነት ላጠየቅበት ስለማይገባ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5 ይግባኙ Aያስቀርብም በማለት ይግባኙን በብይን ሰርዞት በዚህ ብይን ላይ የቀረበለትን ይግባኝ የፍደ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ተቀብሎ በመመርመር የፍደ/ከፍ/ፍ/ቤት የሰጠውን ብይን ሽሮ የመጀ/ደ/ፍ/ቤቱ ብይን በሰጠበት የይርጋ ጥያቄ ላይ ተመስርቶ የቀረበለትን ይግባኝ በመመርመር ተገቢ ነው የሚለውን ትEዛዝ/ውሳኔ/ ይስጥ በማለት ጉዳዩን ለከፍ/ፍ/ቤት የመለሰው መሆኑን ተገንዝበናል።
No topics extracted.
በመሰረቱ Aንድ ፍ/ቤት ወይም ችሎት የቀረበለትን ጉዳይ መመርመር ከመጀመሩ በፊት በጉዳዩ ላይ የዳኝነት ስልጣን ያለው መሆንና Aለመሆኑን ማረጋገጥ የኖርበታል። የፍደ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ተቀብሎ በማየት ውሳኔ የሰጠበት ጉዳይ በመጀ/ደ/ፍ/ቤት ብይን ተሰጥቶበት ከፍ/ፍ/ቤትም በይግባኝ Aይቶ ብይን የሰጠበት በመሆኑ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘ ጉዳይ ነው።
በፍደራል ፍ/ቤቶች Aዋጅ ቁ. 25/1988 Aንቀጽ 10/1/ መሰረት የፍደ/ከፍ/ፍ/ቤት በይግባኝ Aይቶ የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸውን ጉዳዮች (መሰረታዊ የሕግ ስህተት ካለባቸው) Aይቶ የመወሰን ሥልጣን ያለው የፍደ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት Eንጂ ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ ባለመሆኑ የስር ፍ/ቤት (የፍደ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት) ይህንን የፍደ/ከፍ/ፍ/ቤት በይግባኝ Aይቶ የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠበትን ጉዳይ በይግባኝ Aይቶ ውሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል፡ 95 96