No summary available.
የሰበር ፋይል ቁ. 27739 ጥቅምት 28 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ መስፍን Eቁበዮናስ ሒሩት መለሰ Aብዱራሂም Aህመድ Aመልካች፡- Aቶ ድንቁ ገላው ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዋለ Eሸቴ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ የሰበር Aቤቱታ መቅረብ ምክንያት የሆነው Aመልካች ጽፈው Áቀረቡት ማመልከቻ ነው።
የጉዳዩ የሥር Aመጣጥ Aመልካች ከሳሽ በመሆን በጭልጋ ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ያቀረቡት ክስ ተጠሪ ቤት ሰርቼ ባዶ ቦታ ስላለኝ ግዛኝ ብለው በሽማግልዎች Aስማሚነት ቦታውን በብር 35AA (ሶስት ሺህ Aምስት መቶ) ገዝቼ ቤት ሰርቼበታለሁ፣ በቤቱም የልብስ ስôት ድርጅት Aቋቁሜ Eየሰራሁበት ነው፣ ሆኖም ተጠሪ ቤቱን በስሜ ስላላዛወሩልኝ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2892 መሰረት ተገደው Eንዲፈጽሙ ይደረግልኝ የሚል ነው።
ተጠሪም በበኩላቸው ውሉ በሚመለከተው Aካል ቀርቦ ያልፀና ከመሆኑም በላይ በማታለልና በተንኮል የተፈፀመ በመሆኑ ሕጋዊነት የለውም በማለት ተከራክረዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ የሽያጭ ውሉ ይፀድቃል፣ ውሉ ለውልና ማስረጃ ቀርቦ Eንዲፀድቅና ስመ ንብረቱ ለAመልካች Eንዲዛወር የሚል ውሣኔ ሰጥቷል። ያሁኗ ተጠሪ በውሣኔው ቅር ተሰኝተው ለሰሜን ጎንደር መስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱም መሬት መሸጥ የተከለከለ በመሆኑ ውሉ ለሕግ ተቃራኒ ነው በማለት የወረዳውን ፍርድ ቤት ውሣኔ በመሻር Eና Aመልካች ለቤት ማሰሪያ ያወጡትን ወጭ በሕግ የመጠየቅ መብት በመጠበቅ ወስኗል። የከፍተኛው ፍርድ ቤƒ ውሣኔ በAመልካች ይግባኝ ባይነት ቀርቦ ከተመረመረ በኋላ ክሱ ሙሉ የባለቤትነት መብትን ለመገልገል ለመሸጥ፣ ለመለወጥ ወይም ለሶስተኛ ወገን ለማስተላለፍ Eንዲቻል የቀረበ፣ በልላም በኩል ተጠሪ ንብረቱ ያላግባብ ከEጄ ወጥቷል በማለት ባልተከራከሩበት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ባልተጠየቀው ጉዳይ ዳኝነት ሰጥቷል በሚል ውሣኔውን በመሻር የከፍተኛው ፍርድ ቤት ስመ ንብረቱ ላዛወር ይገባዋል ወይስ Aይገባውም በሚል ጭብጥ ላይ ብቻ ተመሥርቶ በማከራከር Eንዲወስን ጉዳዩን መልሶታል የፍተኛው ፍርድ ቤትና በድጋሚ ጉዳዩን Aይቶ መሬት መሸጥ ሕገወጥ መሆኑን ተችቶ ተጠሪ ተገደው ለAመልካች ላያስተላልፉ Aይገባም በማለት ወስኗል። የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም Eንደገና ይግባኝ ቀርቦለት የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሣኔ ካፀና በኋላ Aመልካች ለቤቱ ማሰሪያ ያወጡትን ወጪ በተመለከተ መብታቸውን በመጠበቅ ቤቱን Aፍርሰው ቁሣቁሱን ከወሰዱ በኋላ ቦታውን ለተጠሪ Eንዲያስረክቡ በማለት በዚህ ነጥብ ላይ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በዝምታ ያለፈውን በማሻሻል ወስኗል። Aመልካች የሰበር Aቤቱታውን ያቀረቡት በዚህ መነሻ ሲሆን የAቤቱታው A”ኳር ነጥብ የወረዳው ፍርድ ቤት ውሣኔ ላፀና ይገባዋል የሚል ነው።
ይህ ሰበር ፍርድ ቤት በAመልካች የቀረuለትን Aቤቱታ ከመረመረ በኋላ ተጠሪን Aስቀርቦ ግራ ቀኙን Aከራክሯል። ክርክራቸውንም ከሕግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል። ፍርድ ቤቱ መዝገቡን Eንደመረመረው ገና ከጅምሩም ክሱን ለማስተናገድ የሚያስችል የክስ መሰረት Eንደነበርና Eንዳልነበር ተመልክቷል። በዚህም መሰረት ለክርክሩ መነሻ የሆነው ጉዳይ ባዶ ቦታን የሚመለከት Eንደመሆኑ የመሬት ባለቤት መንግሥት መሆኑ ግልጽ ሆኖ Eያለና በAመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው ውል ከመነሻውም ፈራሽ መሆኑ Eየታወቀ ወይም መታወቅ ሲኖርበት ጉዳዩ የክስ መሰረት Eንዳለው ተቆጥሮ መስተናገዱ ተገቢ ሆኖ Aልተገኘም። ምንም Eንኳ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የከፍተኛው ፍርድ ቤት በሕገ ወጥ ውል ሣቢያ የAመልካችን 81 82 ክርክር ውድቅ ማድረጋቸው Aግባብ ቢሆንም የAመልካችን ጥያቄ ውድቅ ማድረግ የነበረባቸው ጉዳዩን ከክስ መሰረት መኖርና Aለመኖር Aኳያ በማጤን ነበር። ምክንያቱም የክስ መሰረት ሣይኖር ጉዳዩ Eንዲስተናገድ በመደረጉ Aመልካችና ተጠሪ በየደረጃው በተሰጡ ውሣኔዎች AንÈ የፍርድ ባለመብት በልላ ጊዜ ደግሞ የፍርድ ባለEዳ ለመሆን ተዳርገዋል። ለዚህም Aመልካች በወረዳው ፍርድ በተደረገው ክርክር የፍርድ ባለመብት ሲሆኑ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተሰጠው ውሣኔ የፍርድ ባለEዳ መሆናቸውን መጥቀሱ ይበቃል።
ሆኖም የክስ ማመልከቻው የቀረበለት የወረዳው ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.
231/1/ መሰረት ማመልከቻው የክስ መሰረት መኖሩን Aላመለከ}ም በማለት ተጠሪን ሣያስቀርብ ክሱን መዝጋት ሲኖርበት ግራ ቀኙን Aከራክሮ መወሰ’< ተገቢነት Eንደልለው Eየታወቀ የመጨረሻ ውሣኔ የሰጠው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህን ነጥብ ትቶ ጉዳዩ የክስ መሰረት Eንዳለው Aድርጎ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ውሣኔው መሻሻል ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.
የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. A5873 ኀዳር 11 ቀን 1999 ዓ.ም፣ Eንዲሁም የሰሜን ጎንደር መስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. A522A ታህሣሥ 4 ቀን 1997 ዓ.ም በዋሉት ችሎ„ት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎ ክሱ ከመነሻውም የክስ መሰረት የልለው ነው ብለናል። ይፃፍ።
በዚህ ጉዳይ ለAፈፃፀም የሚቀርብ ነገር ባለመኖሩ የጭልጋ ወረዳ ፍርድ ቤት የAፈፃፀም መዝገቡን Eንዲዘጋ የዚህ ውሣኔ ግልባጭ ይድረሰው።
መዝገቡ ተዘግቷል።