No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 25A26 ግንቦት 14 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aብዱልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ መድኀን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- ወ/ሮ ሁዳ መሐመድ - ጠበቃ Aቶ ይልማ Aቻሜ ቀረበ።
ተጠሪ፡- ሀጂ Aህመድ Aህመዲን፣ ጠበቃ ደምሴ ኪዳኔ ቀረቡ።
መዝገቡን የተቀጠሪው፣ ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው Aመልካች የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሚያዝያ 6 ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት የሰበር Aቤቱታ በማቅረቡ ነው። የክርክሩ” ፍሬ ጉዳይ በተመለከተ፣ Aመልካች ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በከሳሽነት ቀርባ ከተከሳሽ ጋር ታህሣሥ 8 ቀን 1991 ዓ.ም. በተደረገ የቤት ሽያጭ ውል፣ በAዲስ Aበባ ከተማ ወረዳ 6 ቀበል A2 ክልል የቤት ቁጥር AA3 የሆነው ቤት በብር 65A,AAA /ስድስት መቶ ሀምሣ ሺህ ብር/ ገዝቼAለሁ። በዚህ ጊዜ ብር 7A,AAA /ሰባ ሺህ ብር/ የመጀመሪያ ክፍያ የከፈልኩ ሲሆን የቤቱን ካርታ Eና የባለቤትነት ደብተር ማረጋገጫ ተረክቤAለሁ። ተከሣሽ በውሉ መሰረት Eንዲፈጽም ማስጠንቀቂያ ብሰጠው ፈቃደኛ ስላልሆነ፣ በፍርድ ተገድዶ ቤቱን Eንዲያስረክብና የውል ግÈታውን Eንዲፈጽም ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ ያቀረበች ሲሆን፣ ተጠሪው የከፍተኛው ፍርድ ቤት መጥሪያና ክስ ደርሶAቸው መልሳቸውን፣ ይዘው ባለመቅረባቸው ጉዳዩ በልK<በት Eንዲታይ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ትEዛዝ ሰጥቷል። ተጠሪው ፍርድ ቤቱ በልለበት Eንዲታይ ትEዛዝ ከሰጠ ከሶስት ወር በኋላ ወደ ክርክሩ ለመግባት Eንዲፈቀድለት የጠየቀ 65 66 ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ የAመልካችን የሰነድና የጽሑፍ ማስረጃ መርምሮ ተጠሪው ታህሣሥ 8 ቀን 1991 ዓ.ም. u}Å[Ѩ< የቤት ሽያጭ ውል መሰረት ቤቱን ከነይዞታው ለAመልካች Eንዲያስረክብ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተጠሪው በዚህ ውሣኔ ይግባኝ ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለይግባኝ ሰሚ ችሎት በማቅረብ ውሉ ሥልጣን በተሰጠው Aካልና በማይንቀሳቀስ ንብረት መመዝገቢያ መዝገብ ያልተመዘገበ በሽያጭና በግዢ Eንዲሁም በምስክሮች የተፈረመበት ስላልሆነ በውል ልገደድ Aይገባኝም በማለት የተከራከሩ ሲሆን መልስ ሰጭም ተጠሪው በይግባኝ ያቀረቡት ክርክር ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክሯል። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ውሉ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1723 ንUስ Aንቀጽ 1 ስልጣን ባለው Aካል ፊት ያልተፈረመ ስለሆነና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 172A ንUስ Aንቀጽ 1 መሰረት Eንደ ረቂቅ ሆኖ ስለሚቆጠር፣ ይግባኝ ባይ /ተጠሪው/ የሚገደድበት ውል የለም በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሯል። Aመልካች ይህ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውሣኔ ተጠሪው በከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሰሰበት ጊዜ የፍርድ ቤት መጥሪያ ክስና ማስረጃ ደርሶት Eያለ፣ ቀርቦ ያልተከራከረ በሥር ፍ/ቤት ያልተነሳ Aዲስ ክርክር በመቀበል የተሰጠ ውሣኔ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሥነ ሥርዓት ግድፈት Aለበት የሚልና የውል ሕግ ድንጋጌዎችን Aተረጓጎም Aስመልክቶ በፍርድ ቤቱ የተሰጠው ትርጉም ተገቢ Aለመሆኑን የሚዘረዝር የሰበር Aቤቱታ Aቅርባለች። ተጠሪው በበኩሉ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በሥር ያልታየ Aዲስ ጭብጥ ይዞ ዳኝነት ላሰጥ Eንደሚችል በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 182 ንUስ Aንቀጽ 2 የተደነገገ በመሆኑ የውሉን ፎርም መሟላት“ Aለመሟላƒ መርምሮ መወሰኑ ተገቢ ስለሆነ፤ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የተሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል። Aመልካች የመልስ መልስ ያቀረበች ሲሆን በሰበር Aቤቱታዋ ያነሳቻቸውን ነጥቦች በማጠናከር ተከራክራለች።
የክርክሩ ፍሬ ጉዳይና በሰበር በግራ ቀኙ በኩል የቀረበው የሕግ መከራከሪያ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ተጠሪው የፍርድ ቤት መጥሪያና የከሳሽ ክስና ማስረጃ ደርሶት በከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርቦ ያላነሳቸውን መከራከሪያዎች በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት Aንስቶ መከራከሪያ ማድረግ ይችላል ወይስ Aይችልም? ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ተከራካሪዎች በሥር መከላከያ Aድርገው ላያነሳቸው የሚገቡ ነገር ግን በሥር ቀርበው ያላነሷቸውን ክርክሮች ራሱ በማንሣት ውሣኔ መስጠቱ ተገቢ ነው Aይደለም? የሚሉትን ጭብጦች መመርመር Aስፈላጊ ሆኖ Aግኝተነዋል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ ተጠሪው Aመልካች ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስና ማስረጃ Eንደዚሁም የፍርድ ቤቱ መጥሪያ ደርሶት በወቅቱ ቀርቦ የመከላከያ መልሱንና ማስረጃውን Aላቀረበም። ተጠሪው ያለበቂ ምክንያት ክሱ በሚሰማበት ጊዜ ሣይቀርብ k`„ መከራከሪያውን ባለማቅረቡና የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 74 በሚደነግገው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም በሰላሣ ቀን ውስጥ ወደ ክርክሩ Eንዲገባ ጥያቄ ባለማቅረቡ ጉዳዩ በልለበት ታይቶ ተወስኗል። ተጠሪው የከፍተኛው ፍረድ ቤት ወደ ክርክሩ EንÅገባ ያልፈቀደልኝ በAግባቡ Aይደለም በማለት ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይግባኝ Aላቀረበም። ይግባኝ ባይ የፍርድ ቤቱ መጥሪያ ደርሶት ቀርቦ ባልተከራከረበት ሁኔታ፣ በልለበት ታይቶ በተሰጠው ውሣኔ ላይ በሚያቀርበው ይግባኝ በሥር ቀርቦ በመከላከያነት ላያቀርባቸው የሚችለውን ሁሉንም የመከራከሪያ ነጥቦች በማንሣት የይግባኝ ቅሬታው መሰረት ማድረግ Eንደማይችል ከፍትሐብሕር ሕግ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 328 ንUስ Aንቀጽ 2 ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል። ምክንያቱም Eንኳንስ የፍርድ ቤት መጥሪያ ደርሶት የቀረበበትን ክስና ማስረጃ ለማስተባበል በሕጉ መሰረት ባለመቅረቡ ጉዳዩ በልለበት ታይቶ የተወሰነበት ተከራካሪ ጉዳዩ Eሱ ባለበት ታይቶና ክሱ ወይም የመከላከያ መልሱና ማስረጃው ተሰምቶ የተወሰነበት ወገን 67 68 በይግባኝ ደረጃ በሥር ፍርድ ቤት ያላነሳውን Aዲስ መከራከሪያ ማቅረብ Eንደማይችል የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 328 ንUስ Aንቀጽ 2 ይደነግጋል። በመሆኑም በልለበት ውሣኔ የተሰጠበት ተከራካሪ በሥር ቀርቦ መከላከያ ላያደርጋቸው የሚገባውን የመከራከሪያ ነጥቦች በይግባኝ ቅሬታው የመከራከሪያ ነጥብ Aድርጎ ለማንሳት ከላይ የተጠቀሰው የሕግ ድንጋጌ የማይፈቅድ ሲሆን ተከራካሪው Eንኳን ቢያነሣው ይግባኙን የሚያየው ፍርድ ቤት ውድቅ ላያደርገው ይገባል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
በልለበት ውሣኔ የተሰጠበት ሰው በልለበት በተሰጠው ውሣኔ ላይ ላያነሣቸው የሚገባው የይግባኝ ቅሬታ ነጥቦችና የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ተቀብሎ ላመረምራቸው የሚችላቸው መከራከሪያዎች Eጅግ በጣም ውስን ናቸው። ይኸውም በክርክሩ ገብቶ የመከላከያ መልስና ማስረጃውን ባያቀርብም በከሣሽ በኩል የቀረበው ክስና ማስረጃ Eሱን በሕግ Aግባብ ኃላፊ የማያደርግ ሆኖ Eያለ ፍርድ ቤቱ፣ የከሳሽን ክስና ማስረጃ ሲመዝን በፈፀመው የጎላ ስህተት ምክንያት ፍትሐዊ ያልሆነ ውሣኔ የተወሰነበት መሆኑን የሚያረጋግጡና ማንም ተከራካሪ ወገን ባያነሣቸውም ፍርድ ቤቱ በራሱ Aነሳሽነት ላያነሣቸው የሚገቡ መሰረታዊ የሕግ ጉዳዮች በማለõ ውሣኔ መስጠቱን የሚያመለክቱ መሆን ይኖርባቸዋል። በያዝነው ጉዳይ ተጠሪው ውሉ በገዢና በሻጭ ያልተፈረመ መሆኑን በምስክሮች ፊት ያልተፈረመ መሆኑና ውሉ በሚመለከተው ስልጣን ባለው Aካል Aለመመዝገቡን በይግባኝ መከራከሪያ ነጥቦች Aድርጎ ያቀረበ ሲሆን ይግባኙን የሰማው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ችሎትም ተቀብሎታል። ሆኖም Eነዚህ መከራከሪያ ነጥቦች ተጠሪው በተከሳሽነት ቀርቦ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ላያነሣቸውና ላከራከርባቸው የሚገቡ የመከላከያ ነጥቦች ናቸው። ተጠሪው የፍርድ ቤቱ መጥሪያ፣ የAመልካች ክስና ማስረጃ ደርሶት በራሱ ቸልተኝነት ምክንያት ለሥር ፍርድ ቤት በመከራከሪያነት Aላቀረባቸውም። በክርክሩ ሂደት ባለመቅረቡም ጉዳዩ በልለበት ተሰምቶና ተመርምሮ ተወስኗል። ስለሆነም ተጠሪው Eነዚህን የመከራከሪያ ነጥቦች የይግባኝ ቅሬታ Aድርጎ ማቅረቡና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም መከራከሪያውን ተቀብሎ ውሣኔ መስጠቱ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪው በልለበት Aይቶ በሰጠው ውሣኔ ላይ የተፈፀመ የሕግ ወይም የፍሬ ጉዳይ ስህተት በልለበት ሁኔታ ፍርድ ቤቱ በራሱ ላያነሣቸው የማይፈቀድለትን የተጠሪን መከራከሪያዎች ለምን ራሱ Aነሣው የሚል ይዘት ያለው በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ፣ በሕግ በልዩ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር፣ በይግባኝ የሚደረገው ክርክር በሥር ፍርድ ቤት የተነሣና የታየ ጉዳይ የሚመለከት Eደሆነና፣ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሥር ፍርድ ቤት ክርክሩን በሚመራበት ማስረጃ በሚቀበልበት ወይም በሚመዝንበት Eና ውሣኔ በሚሰጥበት ወቅት የፈፀማቸውን የሕግና የፍሬ ጉዳይ ስህተቶች ለማረም Eንደሆነ ግልጽ ነው። በዚህ ሂደት ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በሥር ፍርድ ቤት ያልታ¿ና ያልተያዙ ጭብጦች መርምሮ Eንደሚወስን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 182 ንUስ Aንቀጽ 2 ይደነግጋል። ሆኖም ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በዚህ ድንጋÑ@ የተሰጠው ስልጣን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተከራካሪዎች በሥር ፍ/ቤት በመከላከያነት ላያነሷቸው የሚችLD†¨< ነገር ግን ያላነሷቸውን የመከራከሪያ ነጥቦች በራሱ Aነሳሽነት በማንሣት ውሣኔ የመስጠትን ሁኔታ የሚጨምር Aይደለም። በያዝነው ጉዳይ ተጠሪው የከፍተኛው ፍርድ ቤት መጥሪያና የAመልካች ክስና ማስረጃ ደርሶት ክርክር በሚያሰማበት ወቅት ባለመቅረቡ ጉዳዩ በልለበት ታይቶ ተወስኗል። ተጠሪው በሕጉ የተቀመጡትን ሁኔታዎች በማክበር ቀርቦ በመከላከያ መልሱ ላያነሣቸው የሚገቡ የውሉን ፎርም የተመለከቱ የመከራከሪያ ነጥቦች በራሱ ቸልተኝነት ምክንያት ባለማቅረቡ፣ ጉዳዩ በልለበት ታይቶ ውሣኔ ተሰጥቷል። ስለሆነም ተጠሪው መከላከያ ላያደርጋቸው የሚገባቸውን ነጥቦች በሥር ፍርድ ቤት ቀርቦ ባልተከራከረበትና ባላነሣበት ሁኔታ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በይግባኝ ተቀብሎና በራሱ Aነሳሽነት Aንስቶ መሻሩ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 328 ንUስ Aንቀጽ 2 Eና ከፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 69 70 182 ንUስ Aንቀጽ 2 ድንጋጌዎች መንፈስና ዓላማ ጋር የማይጣጣም Eና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 19A95 ሚያዝያ 6 ቀን 1998 ዓ.ም. ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥር 14 ቀን 1997 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል። ይፃፍ።
የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሥነ ሥርዓት ሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ስላተሻረ ተጠሪው የከፍተኛው ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ መሰረት በውሉ የገባውን ግድታ የመፈፀም ኃላፊነት Aለበት ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻሉ።
ይህ ፍርድ በፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ግንቦት 14 ቀን 2AAA ዓ.ም. በሙሉ ድምጽ ተሰጠ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ የሰበር መ/ቁ. 2589A መጋቢት 18 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ሂሩት መለሰ መድህን ኪሮስ ዓላ መሐመድ Aመልካች፡- የIት/መድን ድርጅት - ነ/ፈጅ ኃይሉ ተሰማ ቀረበ መ/ሰጭ፡- Eነ ዝናሽ Aሰፋ /2ሰዎች/ - ቀረበች **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ የካሣ ክፍያን የተመለከተ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የAሁን መ/ሰጭዎች የሥር 1ኛ ተከሣሽ /Aቶ መኰንን ደበበ/ ንብረትነቱ የሥር 2ኛ ተከሣሽ /የAቅም ግንባታ ሚኒስቴር/ የሆነውን ተሽከርካሪ በቢሾፍቱ ከተማ ሲያሽከረክሩ Aባታችንን ገጭተው የገደሉ ስለሆነና ሟች Aባታችን Aስተዳዳሪያችን ስለነበሩ ከቀን ገቢያቸው ከብር 22.AA /ሃያ ሁለት ብር/ ላይ 6A% የሚሆነውን ለEኛ ይሰጡን ስለነበር በሟች ምክንያት ጉዳት ደርሶብናል፣ ስለዚህ ካሣ ይከፈለን በማለት በOሮ/ብ/ክ/መ/ምስ/ሸ/ዞ/ ከፍ/ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ነው። በወቅቱ ጣልቃ ገብ የነበረው የAሁን Aመልካች Aደጋው በደረሰበት ወቅት የሟች የቀን ገቢ ብር 22.AA Aልነበረም፣ ሟች Eስከ 65 ዓመታቸው ድረስ ይኖራሉ የተባለው ተቀባይነት የለውም፣በመ/ሰጭ የተጠየቀው ልዩ ልዩ ወጪ በማስረጃ Aልተደገፈም፣ መ/ሰጪዎች ለAካለ መጠን የደረሱ ስለሆነ ካሣ ላከፈላቸው Aይገባም በማለት ተከራክሯል። ከዚህ በኋላ በቃል ክርክር ወቅት የሥር 2ኛ ተከሣሽ ቀርቦ Aደጋው የደረሰው በEኛ ተሽከርካሪ መሆኑ ባይካድም በሾፍሩ ጥፋት ምክንያት Aይደለም ሲል ተከራክሯል። ፍ/ቤቱም መኪናውን ሲያሽከረክር የነበረው የሥር 1ኛ ተከሣሽ /ሹፍሩ/ ጥፋተኛ መሆናቸው በትራፊክ ፖላስ ማስረጃ ስላልተረጋገጠ ጥፋተኛ 71 72 Aይደሉም፣ የሥር 2ኛ ተከሣሽ ደግሞ Aደጋውን ያደረሰው የEሱ ንብረት የሆነው መኪና መሆኑን ስላመነ Eና የመኪናው ባለቤት ስለሆነ ተጠያቂ ነው፣የካሣ ክፍያውን በተመለከተ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2A95/2/ Eና 8A7 Eስከ 825 ካሣው የሚከፈለው በቀለብ መልክ Eንደሆነ ከመግለጽ ውጭ ካሣ መጠየቅ የሚችሉትን ሰዎች በEድሜ ለይቶ Aላስቀመጠም፣ Aባት ልጆቹን Eስኪያረጁ ድረስ Eንኳን ቢረዳቸው የሚከለክለው ሕግ የለም፣ ስለሆነም ጣልቃ ገብ /የIት/መድን ድርጅት/ ለመ/ሰጭዎች ብር 21,AAA /ሃያ Aንድ ሺህ/ ይክፈል ሲል ወሰነ።
የሥር ጣልቃ ገብ /የIት/መድን ድርጅት/ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ Aቅርቦ ፍ/ቤቱ የIት/መድን ድርጅት የደንበኛው (የAቅም ግንባታ ሚ/ር) ተወካይ ወይም ጠበቃ Eስካልሆነ ድረስ ደንበኛው ከ3ኛ ወገኖች ጋር በሚያደርገው ክርክር ጣ/ገብቶ Eንዲከራከር የሚፈቅድለት ሕግ የለም። በመሆኑም የIት/መድን ድርጅት ደንበኛውን ወክሎ ደንበኛው ላያነሣ የሚችለውን ክርክር በማንሣት መከራከር የሚችለው ምናልባት የሚመጣውን ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ ደንበኛውን ከክርክሩ Aስወጥቶ ከቀረበ ነው። ከዚህ ውጪ ደንበኛው Eየተከራከረ ሳለ Aንድ ጊዜ ከደንበኛው ጋር በልላ ጊዜ ደግሞ ከ3ኛ ወገን ጋር መከራከር የሚችልበት የሕግ Aግባብ ስለልለና ድርጅቱ ለደንበኛው ጥብቅና የመቆም መብቱ ከፖላሲው ስለማይመነጭ Eሱን የማይመለከተውን ክርክር ማቅረቡ ያለAግባብ ነው በማለት የይግባኝ ቅሬታውን ውድቅ Aድርጎታል።
የሰበር Aቤቱታው የቀረበውም ይህንን ውሣኔ ለማስለወጥ ሲሆን የAቤቱታው Aጠቃላይ ይዘትም በጣልቃ ገብነት የመከራከር መብቴን Aስመልክቶ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ሕግን የተከተለ Aይደለም፤ ለAካለ መጠን ለደረሱ ሰዎች የክርክሩ መነሻ የሆነው ካሣ Eንዲከፈል የተሰጠው ውሣኔም ስህተት ነው የሚል ነው።
ይህ ችሎት የሥር ፍ/ቤቶችን ውሣኔዎች Aግባብ ካለው ሕግ ጋር Aገናዝቦ መርምሯል። የAሁን መ/ሰጭዎች Aስተዳዳሪያችን የነበሩት Aባታችን በተሽከርካሪ ተገጭተው በመሞታቸው ምክንያት የተቋረጠብን ገቢ ይከፈለን በማለት በክልሉ ምስ/ሸ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት የAቅም ግንባታ ሚ/ርን ከነ ሾፍሩ ከከሰሱ በኋላ ፍ/ቤቱ ተገቢ ነው ያለውን ካሣ በወቅቱ ጣልቃ ገብ የነበረው የAሁኑ Aመልካች ይክፈል በማለት ውሣኔ መስጠቱን፣ Eንዲሁም Aመልካች ይህንን ውሣኔ በመቃወም ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ Aቅርቦ ፍ/ቤቱ Aመልካች የደንበኛው ጠበቃ ስላልሆነ በጣልቃ ገብነት ቀርቦ የደንበኛውን ክርክር Eያነሣ መከራከር Aይችልም በማለት መወሰኑን መዝገቡ ያስረዳል።
በመሰረቱ በጣልቃ ገብ /የIት/ሙድን ድርጅት/ Eና በሥር 2ኛ ተከሣሽ (የAቅም ግንባታ ሚ/ር) መካከል የመድን ውል መኖሩ Aላከራከረም።
የAቅም ግንባታ ሚ/ር ተሽከርካሪ ጉዳት በማድረሱ ምክንያት ክስ ቀርቦ ካሣ መክፈል Eንዳለበት ከተወሰነ በመድን ውሉ ላይ Eስከተገለፀው መጠን ድረስ ያለውን ካሣ የመክፈል ኃላፊነቱ የAመልካች Eንደሚሆን Aያጠራጥርም።
ስለሆነም የክርክሩ ውጤት በAመልካች መብት ወይም ጥቅም ላይ Aዎንታዊም ሆነ Aሉታዊ ተጽEኖ የሚያሣድር መሆኑ ግልጽ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ የAቅም ግንባታ ሚ/ር ተሽከርካሪ ባደረሰው ጉዳት ምክንያት የካሣ ክፍያ ጥያቄን የያዘ ክስ ሲቀርብ ጉዳዩ Aመልካችን ስለሚመለከተው በክርክሩ ውስጥ ጣልቃ በመግባት የኋላ ኋላ ላመጣበት የሚችለውን ማንኛውንም ኃላፊነት ቢቻል ለማስወገድ ባይቻል ለመቀነስ የሚያስችለውን ክርክር ማቅረቡ ተገቢ ነው። በAንድ ክስ ልሎች ተከራካሪ ወገኖች በክርክር ላይ ባሉበት ጊዜ በጉደዩ ያገባኛል የሚል ማንኛውም 3ኛ ወገን ከፍርድ ውሣኔ በፊት ጣልቃ ገብቶ መከራከር Eንደሚችል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41/1/ ላይ የተደነገገ በመሆኑ Aመልካች የደንበኛው ጠበቃ ስላልሆነ ጣልቃ ገብቶ መከራከር Aይችልም በማለት በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የOሮ/ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 3534A ሰኔ 1 ቀን 1998 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
የOሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት የAሁን Aመልካች ጣ/ገብቶ የመከራከር መብት ያለው መሆኑን ተገንዝቦ በጉዳዩ ጣልቃ ›eÑw„ Eንዲያከራክረውና በሕጉ መሰረት Eንዲወስን ብለናል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ። መዝገቡ ተዘግቷል።
ይመለስ።