No summary available.
ሐምል 26 ቀን 1999 ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aሰግድ ጋሻው ተሻገር ገ/ሥላሴ Aብዱራሒም Aህመድ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ Aመነው Aመልካች፡- Aቶ በቀለ በድዬ መልስ ሰጪ፡- 1ኛ/ የወጋገን ባንክ Aዋሳ ቅርንጫፍ 2ኛ/ የቡል ሆራ ከተማ Aስተዳደር 3ኛ/ Aቶ ሁሴን ወልድ መዝገቡን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር ዳኝነት ሳይከፈልበት በነፃ ክስ ለማቅረብ Eንዲፈቀድ ከሚቀርብ ጥያቄ ጋር በተያያዘ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
32A/3/ የተመለከተውን ድንጋጌ Aተረጓጎም የሚመለከት ነው።
ክሱ የቀረበለት የቦረና ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የAሁን Aመልካች ዳኝነት ሳይከፍልበት በነፃ ክስ ለማቅረብ የሚችል ሆኖ Aልተገኘም። ስለሆነም ተገቢውን የዳኝነት ገንዘብ መክፈሉ በተረጋገጠ ጊዜ መዝገቡን የማንቀሳቀስ መብት Aለው በማለት Aሰናብቶታል።
በዚህ ትEዛዝ ቅር በመሰኘት Aመልካች የይግባኝ Aቤቱታውን ለOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት Aቅርቧል።
የጠ/ፍ/ቤትም በጉዳዩ ላይ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 32A/3/ መሰረት uዳኝነት ክፍያ ክርክር ላይ ይግባኝ ላቀርብ Eንደማይችል ስለሚደነግግ ወይም ጊዜያዊ Aገልግሎት ያለውን ትEዛዝ መስጠት በመሆኑ በEንደዚህ ዓይነት ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ውሣኔ ከተሰጠ Eንጂ በትEዛዝ ላይ ይግባኝ መጠየቅ የሚቻል ባለመሆኑ የይግባኝ Aቤቱታው የሕግ Aካሄድን ጠብቆ የቀረበ Aይደለም በማለት ጥያቄውን ውድቅ Aድርጎታል።
Eኛም ጉዳዩን መርምረናል።
Eንደመረመርነውም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 32A/3/ የተመለከተው ድንጋጌ Ÿፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ዓላማና Aስፈላጊነት ጋር ተገናዝቦ ላታይ ይገባዋል።
Aንድ ፍ/ቤት የቀረበለትን ጉዳይ ሙሉ የክርክር Aካሄድን ተከትሎ የመጨረሻ ውሣኔ ለመስጠት በEያንዳንዱ የክርክር ደረጃ የሚሰጣቸው ትEዛዞች“ ብይኖች ይኖራሉ። በዚህ Aኳኋን በክርክር ሂደት መካከል ትEዛዞችና ብይኖች በመስጠት ይግባኝ Eንዲቀርብ ቢፈቀድ በAንድ ጉዳይ ምክንያት በተለያ¾ ፍ/ቤት የተለያ¾ ክርክር Eንዲኖር የሚጋብዝ Aሰራር ይሆናል። ይህ ደግሞ ክርክርን ፍትሃዊ በሆነ Eና ሥርዓት ባለው መንገድ በመምራት በAፋጣኝ Eና በAነስተኛ ወጭ መቋጨት ይገባል ለሚለው ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ገዥ ዓላማ ጋር የሚፃረር ነው።
ለዚህም ነው ማናቸውም ፍ/ቤት ክርክሩን በሚሰማበት ጊዜ በጉዳዩ ላይ ጊዜAዊ Aገልግሎት ያለው ትEዛዝ ሲሰጥ ከሥረ ነገሩ ፍርድ በፊት ይግባኝ ለማለት Aይቻልም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 32A/3/ የተደነገገው።
ጊዜያዊ Aገልግሎት ያላቸው ትEዛዞች የትኞቹ ናቸው? የሚለውን ለማመልከት ከተዘረዘሩት የትEዛዝ ዓይነቶች ዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ለመክሰስ Eንዲፈቀድ የሚቀርብ ጥያቄ Aንዱ የትEዛዝ ዓይነት Eንደሆነ በዚሁ ድንጋጌ ሥር ተመልክቷል።
ዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ለመክሰስ Eንዲፈቀድ በቀረበ ጥያቄ ላይ ላሰጥ የሚችለው ትEዛዝ Eንደነገሩ ሁኔታ ሁለት ዓይነት ነው። Aንደኛው ከሣሽ የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችለው የገንዘብ Aቅም የልለው ስለሆነ Eንደ ጥያቄው የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍል በነፃ ፋይል ከፍቶ ክሱን ለማቅረብ ይችላል የሚለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ከሣሹ ድሃ ያለመሆኑ ስለተረጋገጠ ተገቢውን የዳኝነት ገንዘብ ካልከፈለ በቀር በነፃ ፋይል ከፍቶ ክሱን ለማቅረብ Aይችልም የሚለው ነው።
49 50 በመጀመሪያው Aኳኋን ትEዛዝ በተሰጠ ጊዜ በዚህ ትEዛዝ መሰረት ፋይሉ ተከፍቶ ክርክሩ የሚቀጥል ነው። የክርክሩ ውጤት የሚታወቀው ግራ ቀኙ በሚያቀርቡት የፍሬ ነገርና የሕግ ክርክር ማስረጃ መሰረት ነው።
በመጨረሻው የክርክር ውጤት ተከሣሹ ባይስማማ ክርክሩ ከመጀመሩ በፊት ክሱ ዳኝነት ሳይከፈልበት በነፃ Eንዲከፈት መደረጉ የሕግ ድጋፍ Aልነበረውም የሚለውን Eንደ Aንድ የይግባኝ ምክንያት በማድረግ በውሣኔው ላይ ካለው p_ ጋር Aዳምሮ Tቅረብ ይኖርበታል Eንጂ ከሥረ-ነገሩ ፍርድ በፊት የይግባኝ Aቤቱታ የማቅረብ መብት Aይኖረውም። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 32A/3/ የተመለከተው ድንጋጌም በዚህ Aኳኋን በሚቀርበው የይግባኝ Aቤቱታ ላይ ክልከላ ለማድረግ ነው።
በልላ በኩል ድሀ ያለመሆንህ ተረጋግጧል። የዳኝነት ገንዘብ ካልከፈልክ በቀር ፋይል Aይከፈትም ለተባለው ከሣሽ ግን ይህ ዓይነቱ ትEዛዝ የመጨረሻ ነው:: ልላ የሚጠበቅ የሥረ-ነገር ፍርድ የለውም። ስለሆነም የዳኝት ገንዘብ ለመክፈል AቅU ሳይኖረኝ ክርክሬና ማስረጃዬ በAግባቡ ሳይታይ Aቅም Eንዳለኝ ተቆጥሮ የዳኝነት ገንዘብ ክፈል መባል ተገቢ Aይደለም የሚል ከሆነ የተሰጠው ትEዛዝ የመጨረሻ Eንደመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 32A/1/ መሰረት የይግባኝ Aቤትታ የማቅረብ መብት Aለው።
No topics extracted.
ስለሆነም የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 32A/3/ … ዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ለመክሰስ Eንዲፈቀድ በሚቀርብ ጥያቄ ላይ በሚሰጠው ውሣኔ ወይም ትEዛዝ የሚለውን Aነጋገር ከላይ በተመለከተው መሰረት ከሁለት ማEዘን Aንፃር ሳይመለከት በደፈናው ጊዜያዊ Aገልግሎት ያላቸው ትEዛዞች ናቸው በሚለው ድንጋጌ ሰፍሮ የሚገኝ መሆኑን ብቻ በማየት Aመልካች በጉዳዩ ላይ ይግባኝ የማቅረብ መብት የለውም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የፈፀመ መሆኑን ተገንዝበናል።
ው ሣ ኔ
የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት Aመልካች የዳኝነት ገንዘብ መክፈል Aለበት ወይስ የለበትም? የሚለውን ነጥብ Ÿeር ፍ/ቤት የመዝገብ ግልባጭ ጋር Aገናዝቦ ጉዳዩን መርምሮ ላወሰን ይገባል በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341/1/ መሰረት መልሰናል።
የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በጥር 3A ቀን 1998 የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።