No summary available.
ግንቦት 26 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ መስፍን Eቁበዮናስ ታፈሰ ይርጋ መድኀን ኪሮስ Aመልካች፡- የIትዮጵያ መድን ድርጅት - ነ/ፈጅ ቀረቡ።
ተጠሪ፡-
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በሶማል ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት በጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን ተጠሪዎች በሥር 1ኛ ተከሣሽ በመከላከያ ሚኒስቴር የምድር ጦር 1A3ኛ ሰራዊትና በ2ኛ ተከሣሽ Aቶ ገ/EግዚAብሕር ገ/ሕይወት ላይ ባቀረቡት ክስ ንብረትነቱ የ1ኛ ተከሣሽ የሆነውን መኪና 2ኛ ተከሣሽ ሲያሽከረክር ሆድል በተባለ ቦታ መስመሩን ጥሎ በመውጣት የ1ኛ ከሣሽን መኪና በመግጨት ከጥቅም ውጭ ያደረገ ስለሆነ የመኪናውን ግምት ብር 219 ሺህ Eንዲከፍል፣ Eንደዚሁም በዚሁ ግጭት ምክንያት ከጥቅም ውጭ በሆነው ንብረትነቱ የ1ኛ ከሣሽ በሆነው መኪና የ2ኛ ከሣሽ ልጅ ተሳፍሮ ሲጓዝ የሞት Aደጋ የደረሰበት ስለሆነና ሟችም KAካለመጠን ያላደረሱ የ2 ሕፃናት ልጆች Aባት ስለነበር Eነዚህ 2 ሕፃናት Aካለመጠን Eስከሚደርሱ Eነሱን ለማሳደግና ለመንከባከብ በድምሩ ብር 65,52A /ስልሣ Aምስት ሺህ ›Ueƒ መቶ ሃያ ብር/ Eንደዚሁም ካሣ ብር 74,AAA /ሰባ Aራት ብር/ በAጠቃላይ ብር 139,52A /መቶ ሰላሣ ዘጠኝ ሺህ Aምስት መቶ ሃያ/ Eንዲከፈላቸው የጠየቁ ሲሆን 3ኛ ከሳሽም በዚሁ ግጭት የAካል ጉዳት Eንደደረሰባቸው ዘርዝረው በድምሩ ብር 14A,AAA ካሣ ላከፈለኝ ይገባል በማለት ሶስቱም ከሣሾች በዚህ መልኩ ክሱን ያቀረቡ ሲሆን ተከሣሾች ቀርበው ጉዳቱን Aድርሷል የተባለው ተሽከርካሪ በIትዮጵያ መድን ድርጅት በኩል የመድን ሽፋን የተገባለት መሆኑን ገልፀው በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 43 መሰረት በክርክሩ ጣልቃ ይግባልን በማለት Aመልክተው የIትዮጵያ መድን ድርጅት ጣልቃ ገብቶ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና ሙሉ መልስ በመስጠት ተከራክሯል።
የIትዮጵያ መድን ድርጅት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሳው ክርክር ከተከራካሪ ወገኖች መካከል Aንደኛው የፍድራል መንግሥት Aካል በሆነ ጊዜና ክስ የቀረበበት የገንዘብ መጠን ከብር 5AA ሺህ /Aምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ጉዳዩን የማየት ሥልጣን ያለው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ስለሆነ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለውም የሚል ነው።
በፍሬ ጉዳዩ ክርክር ረገድም ጣልቃ ገብ የደንበኛው ተሽከርካሪ በ3ኛ ወገን ንብረት ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት ብር 1AA ሺህ /Aንድ መቶ ሺህ ብር/ Eንደዚሁም በሰው ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት የሰጠው ሽፋን Eስከ ብር 3A ሺህ /ሰላሣ ሺህ ብር/ ሲሆን በተያዘው ጉዳይ ጉዳት በ2 ሰዎች ላይ ስለደረሰ በድምሩ ብር 6A /ስልሳ ሺህ/ ሺህ Eንደዚሁም በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት በተሰጠው የመድን ሽፋን ልክ ብር 1AA ሺህ /Aንድ መቶ ሺህ/ ስለሚሆን በAጠቃላይ ብር 16A ሺህ /መቶ ስልሣ ሺህ/ ጣልቃገብ ካሣ ከሚከፍል በስተቀር በክስ የተጠየቀውን በሙሉ ለመክፈል Aይገደድም በማለት ተከራክሯል።
ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የፍ/ቤቱን የሥረ ነገር ሥልጣን Aስመልክቶ በተነሳው መቃወሚያ ላይ ብይን ሳይሰጥ በቀጥታ በፍሬ ጉዳ¿ LÃ የተነሣውን ክርክር መርምሮ 1ኛ ከሣሽን በተመለከተ በግጭቱ ምክንያት መኪናው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ የሆነ ስለሆነ የመኪናውን የዋጋ ግምት ብር 217 /ሁለት መቶ Aስራ ሰባት ብር/ ሺህ 2ኛ ከሣሽን በተመለከተም በAደጋው ምክንያት ልጁ ስለሞተ ብር 91,52A /ዘጠና Aንድ ሺህ ብር Aምስት መቶ ሃያ ብር/ Eንደዚሁም 3ኛ ከሣሽን በተመለከተ ለደረሰበት የAካል ጉዳት ብር 6A ሺህ /ስልሳ ሺህ ብር/ Eንዲከፈለው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ጣልቃ ገብ በዚህ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት Aቅርቦ ፍ/ቤቱም በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት Aጽንቶታል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ ውሣኔ ለማስለወጥ ሲሆን ይህ ችሎት Aቤቱታውን መርምሮ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህን ጉዳይ ለማየት የሥረ ነገር ሥልጣን ነበረው? ወይንስ Aልነበረውም? ሥልጣን Aለው ቢባልስ የካሳ ክፍያውን Aስመልክቶ የሰጠው ውሣኔ Aግባብነት Aለውን? የሚለው በመሆኑ በዚሁ መሰረት Aቤቱታው ተመርምሯል።
No topics extracted.
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተም የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንን ጉዳይ ለመመልከትና ለመወሰን የሥረ ነገር ሥልጣን የለውም ተብሎ መቃወሚያ የቀረበው በAንድ በኩል ጣልቃ ገብ /Aመልካች/ የፍድራል መንግሥት Aካል ነው በሚልና በልላ በኩልም የክርክሩ የገንዘብ መጠን ከብር 5AA ሺህ /Aምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ስለሆነ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለውም በማለት ነው።
ይሁንና የፍድራል ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በክልሎች ካልተቋቋመ የፍድራል ጉዳዮችን ክልሎች መመልከት Eንደሚችሉ በሕገ መንግሥቱ Aንቀጽ 78/2/ ላይ የተመለከተ ከመሆኑም በላይ የክርክሩ የገንዘብ መጠን ከብር 5AA ሺህ /Aምስት መቶ ሺህ/ የማይበልጥ ስለሆነ የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን ለማየት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን ስላለው በዚህ ረገድ የቀረበው Aቤቱታ የሕግ ድጋፍ የልለው በመሆኑ ችሎቱ Aልተቀበለውም።
Aመልካች መክፈል የሚገባውን የካሣ መጠን በተመለከተም በንግድ ሕግ ቁጥር 665/2/ ላይ Eንደተመለከተው የመድን ገቢው ኃላፊነት በፖላሲው ላይ ከተመለከተው የገንዘብ መጠን በላይ ላሆን Eንደማይችል የተመለከተ ሲሆን Aመልካችም በሰው ላይ ለሚደርስ ጉዳት Eስከ ብር 3A ሺህ በ3ኛ ወገን ንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ደግሞ Eስከ ብር 1AA ሺህ /Aንድ መቶ ሺህ/ ካሣ ለመክፈል ለሥር 1ኛ ተከሣሽ የመድን ሽፋን መስጠቱን ተገንዝበናል። በዚሁ መሰረትም በAደጋው ጉዳት የደረሰው በ2 ሰዎች Eንደመሆኑ መጠን ለEያንዳንዱ ተጎጂ በሽፋኑ መጠን ልክ Eንደዚሁም በ3ኛ ወገንም ንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት በመድን ሽፋኑ ልክ ታይቶ ውሣኔ መስጠት ሲገባው ከመድን ሽፋኑ በላይ Aመልካች Eንዲከፍል በሥር ፍ/ቤቶች መወሰኑ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
Aመልካች በመድን ውሉ መሰረት በ1ኛ ተጠሪ ንብረት ላይ ለደረሰ ጉዳት ብር 1AA,AAA /Aንድ መቶ ሺህ/ Eንደዚሁም ለ2ኛ Eና 3ኛ ተጠሪዎች ለደረሰው የሞትና የAካል ጉዳት ለEያንዳንቸው ብር 3A,AAA /ሰላሣ ሺህ/ በድምሩ ብር 16A,000 /Aንድ መቶ ስልሳ ሺህ/ የሥር 1ኛ ተከሣሽን በመተካት ይክፈል በማለት የሥር ፍ/ቤቶችን ውሣኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት Aሻሽለን ወስነናል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።