No summary available.
ግንቦት 18 ቀን 1997 ዓ.ም.
የሰጠው ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ጸንቷል። ከዚህ በፊት የተሰጠው የEግድ ትEዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ የሰበር መ/ቁ. 2127A ሐምል 3A ቀን 1999 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ Aሰግድ ጋሻው ሒሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ Aመነው Aመልካች፡- የIትዮጵያ ልማት ባንክ መልስ ሰጪ፡- ወ/ሮ ወይንሸት Aበራ በልለችበት የሚታይ መዝገቡን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር Aቤቱታ የቀረበው የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የEግድ ይነሳልኝ ጉዳይ Aስመልክቶ በሰጠው ውሣኔ ላይ ነው።
የAሁን መልስ ሰጭ በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ከሣሽ ሆነው በወ/ሮ Aስናቀች ቶለሣ ላይ ክስ Aቅርበዋል። የዚህም ክስ ውጤት Eስከታወቀ ድረስ የተከሳሽ የወ/ሮ Aስናቀች የሆነው ንብረት በማናቸውም መንገድ ቢሆን ወደ ሦስተኛ ወገን Eንዳይተላለፍ ታግዶ ይቆይ ዘንድ ክሱ በቀረበለት የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 154 መሰረት የEግድ ትEዛዝ Eንዲሰጥ Aድርገዋል።
Aመልካችም የIትዮጵያ ልማት ባንክ ለወ/ሮ Aስናቀኝ ቶለሣ በሰጠው የብድር ገንዘብ ምክንያት ይህንኑ የEግድ ትEዛዝ የተላለፈበትን ንብረት Aስቀድሞ በመያዣ የያዘው መሆኑንና የብድር ገንዘቡ Eንደ ውሉ ባለመመለሱ፤ ተበዳሪ Eዳውን ለመክፈል ባለመቻሐ ምክያት በAዋጅ ቁጥር 97/9A በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ይህንኑ በመያዣ የተያዘውን ንብረት ለSሸጥ Eንቅስቃሴ ሲያደርግ ከላይ በተገለፀው Aኳኋን በፍ/ቤት የEግድ ትEዛዝ የተሰጠበት መሆኑን በመረዳቱ Aስቀድሞ በመያዣ የያዘው መሆኑን 21 22 በመግልጽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 158 መሰረት የተሰጠው የEግድ ትEዛዝ Eንዲነሳለት ጠይቋል።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤትም ጉዳዩን ተመልክቶ ንብረት በፍ/ቤት ትEዛዝ ታገደ ማለት የEግድ ትEዛዝ የተሰጠበት ወገን በንብረቱ ላይ መብት Aግኝቷል ማለት Aይደለም።
የቀረበውም የEግድ ይነሳልኝ ጥያቄ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት በAፈፃፀም ጊዜ ከቅድሚያ መብት ጋር ተያይዞ የሚታይ Eንጂ በዚህ መዝገብ የሚስተናገድ Aይደለም በማለት ውድቅ Aድርጎ ወስኗል።
የይግባኝ Aቤቱታ የቀረበለት የከፍተኛው ፍ/ቤትም በጉዳዩ ላይ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ Aጽንቶታል።
የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም ከላይ በAጭሩ በተመለተው Aኳኋን በየደረጃው ባሉት ፍ/ቤቶች የተሰጠው ዳኝነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ይታረምልን የሚልበትን ክርክር በማቅረቡ ነው።
በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የተሰጠው የEግድ ትEዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 158 መሰረት ላነሳ Aይገባም የመባሉን Aግባብነት መልስ ሰጭ ባለበት ለማጣራት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት Eንዲቀርብና መልስ ሰጭም የበኩላቸውን ክርክር Eንዲያቀርቡ ጥሪ ቢያደርግላቸውም በጥሪው መሰረት ባለመቅረባቸው ጉዳዩ በልሉበት Eንዲታይ ተደርጓል።
Eኛም ጉዳዩን Aግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
ከሣሽ የሆነ ወገን ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ንብረትም ይሁን ወይም ደግሞ የባለመብቶችን ጥቅም ለመጉዳት ሲል ንብረቱን ለልላ ሰው Aሳልፎ ለመስጠት ያቀደ ወይም ያሰበ መሆኑን ያረጋገጠ Eንደሆነ ይኸው ንብረት በማናቸውም መንገድ ቢሆን ለሦስተኛ ወገን ሳይተላለፍ ታግዶ Eንዲቆይ የማስደረግ መብት Eንዳለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 154/ሀ/ Eና /ለ/ ተደንግጓል።
ከዚህም ድንጋጌ የምንረዳው በዚህ Aኳኋን የሚሰጠው የEግድ ትEዛዝ ንብረቱ ከመታገዱ በፊት ወደ ልላ ሦስተኛ ወገን ያልተላለፈ ከሆነ ወይም ደግሞ በማናቸውም ምክንያት ሦስተኛ ወገኖች በንብረቱ ላይ መብት ከማግኘታቸው በፊት ላሆን ይገባል።
የዚሁ ድንጋጌ ዓላማም ከሳሽ ያቀረበው ክስ ወደ ፊት ውጤት ¾T>Áገ˜ለት ከሆነ በAፈፃፀም ጊዜ ለማሸጥ ወይም በመረከብ Eንደ ፍርዱ ይፈፀምለት ዘንድ የተሰጠው የሕግ ጥበቃ ነው። Eንደ ሕጉ ሐሳብ የEግድ ትEዛዙ ውጤት ላያገኝ የሚችለው ይኸው ንብረት በልላ Eዳ ምክንያት በልላ ወገን ያልተያዘ መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም ደግሞ በዚህ ንብረት ላይ መብት ያገኙ ሰዎች የልሉ Eንደሆነ ብቻ ነው።
በዚህ በተያዘው ጉዳይ በዚህ ንብረት ላይ የEግድ ትEዛዝ በፍ/ቤት ከመስጠቱ በፊት የAሁን Aመልካች በሰጠው የብድር ገንዘብ ምክንያት በመያዣ Aስቀድሞ ይዞት የነበረ ስለመሆኑ የተካደ ጉዳይ Aይደለም።
ይህም ምክንያት በፍ/ቤት የተሰጠውን የEግድ ትEዛዝ ለማስነሳት በቂ ምክንያት ሆኖ ስለሚገኝ Aመልካች Eግዱን ለሰጠው ፍ/ቤት ቅሬታውን ማሰማቱ Eንደታወቀ ከላይ በተገለፀው ዝርዝር ምክንያት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
No topics extracted.
158 መሰረት የሰጠውን Eግድ ላያነሳ ሲገባ ለጉዳዩ Aግባብነት የልለውን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418ን በመጥቀስ ጥያቄው በAፈፃፀም ጊዜ ከቅድሚያ ክፍያ ጋር ተያይዞ የሚታይ Eንጂ በዚህ መዝገብ የሚስተናገድ Aይደለም፤ ንብረት Aሳገደ ማለት በንብረቱ ላይ መብት Aገኘ ማለት Aይደለም በማለት የAመልካችን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ Eና Eንዲሁም ባንክ በሰጠው የብድር ገንዘብ ምክንያት በመያዣ የያዘውን ንብረት ተበዳሪው Eዳውን መክፈል በተሳነው ጊዜ በሐራጅ Aሽጦ የብድሩን ገንዘብ የማስመለስ ስልጣን በAዋጅ ቁጥር 97/9A የተሰጠው በመሆኑና ይህ ክርክር የተነሳበት ንብረት በፍ/ቤት ትEዛዝ ከመታገዱ በፊት ባንኩ በመያዣ ይዞት የነበረ መሆኑ Eስከተረጋገጠ ድረስ በሕግ በተሰጠው መብት መገልገል ይችል ዘንድም የሥር ፍ/ቤት ይህንኑ ተገንዝቦ የሰጠውን የEግድ ትEዛዝ ማንሳት ሲችል ያለ ሕጋዊ ምክንያት 23 24 ጥያቄውን ውድቅ uማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የፈፀመ መሆኑን ተገንዝበናል።
ው ሣ ኔ
በከፍተኛ A1 ቀበል A6 የቤት ቁጥር A29 በሆነውና በወ/ሮ Aስናቀች ተሎሣ ስም ተመዝግቦ በሚገኘው ካፍቴሪያ ላይ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት መዝገብ ቁ. 26A2 በታህሣሥ 16 ቀን 1991 ዓ.ም. የሰጠው የEግድ ትEዛዝ ተነስቷል።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 26A2 በታህሣሥ 28 ቀን 1995 የሰጠው ትEዛዝ Eንዲሁም የፍ/ከ/ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ A1359 ሰኔ 3A ቀን 1997 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። መዝገቡ ተዘግቷል።