No summary available.
ጥር 23 ቀን 1999 ዓ.ም. በሰጠው ፍርድ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
መዝገቡ ይመለስ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ የሰበር መ/ቁ. 3A298 ጥር 2A ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- Aቶ የሺወንድም Aቡሐይ ተጠሪ፡- Aቶ Aየነው ማለደ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው በተጠሪ ላይ ተሰጥቶ የነበረው የመጥፋት ውሣኔ ሲሰረዝ Aመልካች ለ3ኛ ወገን በሽያጭ Aስተላልፈውታል የተባለውን ቤት ለተጠሪ ላመለሱ ይገባል የሚሉት በበታች ፍ/ቤቶች የተሰጡት ውሣኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል ሲሉ Aመልካች የሰበር Aቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ ተጠሪ ለሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት Aቤቱታ በAመልካች ጠያቂነት ቀደም ሲል በወረዳ ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ በተሰጠው የመጥፋት ውሣኔ የተነሣ መሆኑን ገልፀው የግል ንብረቴ የሆነውና የዋጋ ግምቱም ብር 5A.AAA (ሃምሣ ሺህ) የሆነው ቤት Aመልካች ለ3ኛ ወገን በሽያጭ ያስተላለፈው ስለሆነ Eንዲመለስ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
Aመልካችም ቀርበው በሰጡት መልስ ተጠሪ ከEናቴ ጋር ጋብቻ መሥርቶ Eያለ Eናቴን ጥሎ በመጥፋቱ በሽተኛ ስለነበረች Eሷን ለማሣከም ገንዘብ በማስፈለጉ ቤቱ የተሸጠ ሲሆን የሽያጩ ዋጋም በከሣሽ Eንደተጠቀሰው ብር 5A,000 /ሃምሣ ሺህ/ ሣይሆን ብር 25,000 /ሃያ Aምስት ሺህ/ ነው በማለት ክሱ ላሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክሩን ከቀረበው ማስረጃ Aኳያ መርምሮ ተከሣሽ ለክሱ ምክንያት የሆነው ቤት የከሣሽና የEናቴ የጋራ ሀብት ነው የሚል ክርክር ቢያቀርብም ከጎንደር ከተማ Aገልግሎት ጽ/ቤት የቀረበው የሰነድ ማስረጃና Eንደዚሁም በከሣሽ በኩል የቀረቡት ምስክሮች በሰጡት ቃል ከሣሽ ከተከሣሽ Eናት ጋር ጋብቻ ከመመሥረታቸው በፊት የሰሩት ቤት Eንደሆነ ስለሚያረጋግጥ ተከሣሽ ቤቱ የጋራ ንብረት ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም ካለ በኋላ ጠፍቷል የተባለ ሰው ከመጣ ጠፍቷል መባሉ ተሰርዞ ወደ ልላ ሰው ተላለፎ የሚገኝ ንብረትም ላመለስለት Eንደሚገባ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 171(1) ላይ የተመለከተ በመሆኑ በዚሁ መሰረት ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ለከሣሽ ላመለስ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተከሣሽ በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ ቅሬታቸውን ለAማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሣይቀበለው ቀርቷል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችሎትም የቀረበለትን Aቤቱታ መርምሮ Aመልካች ተጠሪ ጠፍተዋል በማለት የመጥፋት ውሣኔ ካገኙ በኋላ ወራሽነታቸውን Aረጋግጠው የተጠሪን ቤት ለ3ኛ ወገን መሸጣቸው በተረጋገጠበት ሁኔታ ተጠሪ ሲመለሱ ላመለስላቸው የሚገባው የቤቱ ሽያጭ ዋጋ ወይንስ ቤቱ Eራሱ የሚለው ነጥብ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 171 Aኳያ Aቤቱታው ለሰበር ቀረቦ ተጣርቶ ላወሰን የሚገባው ሆኖ በማግኘቱ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ነጥብ ከላይ የተመለከተው ሲሆን የሰበር Aቤቱታው ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ Aኳያ Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
በተጠሪ ላይ የመጥፋት ውሣኔ ከተሰጠ በኋላ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በሽያጭ ወደ 3ኛ ወገን Eንደተላለፈ ግራ ቀኙን Aላከራከረም።
የመጥፋት ውሣኔን ውጤት ቀሪ ከሚያደርጉ ምክንያቶች /effects of termination of absence/ ጠፍቷል የተባለው ሰው መመለስ Eንደሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
171 ላይ ተመልክቷል። በዚህ ድንጋጌ መሰረትም ጠፋ የተባለው ሰው በተመለሰ ጊዜ ንብረቶቹን በሚገኙበት Aኳኋን መልሶ የመረከብ Eንደዚሁም የተሸጡትን ንብረቶች ዋጋ የማግኘት መብት Eንዳለው በግልጽ ተመልክቷል።
በተያዘውም ጉዳይ ንብረትነቱ የተጠሪ የሆነው ቤት መሸጡ ከተረጋገጠ ከላይ ከተጠቀሰው ድንጋጌ Aኳያ ተጠሪ ላረከቡ የሚገባቸው የተሸጠውን ቤት ሣይሆን የሽያጩን ዋጋ ነው ማለት ነው። የሽያጩን ዋጋ በተመለከተም Aመልካች በብር 25,000 /ሃያ Aምስት ሺህ/ መሸጡን ሲገልፁ ተጠሪ ዋጋው ብር 5A.AAA (ሃምሣ ሺህ) Eንደሆነ ከመግለጽ በስተቀር በዚህ ዋጋ የተሸጠ መሆኑን ማስረጃ Aቅርበው Aልተከራከሩም።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
ስለሆነም የበታች ፍ/ቤቶች በሽያጭ የተላለፈው ቤት ለተጠሪ ላመለስላቸው ይገባል በማለት የሰጡት ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በብር 25.AAA (ሃያ Aምስት ሺህ) ስለመሸጡ የተረጋገጠ ስለሆነ የህንኑ የሽያጭ ገንዘብ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ተከፍሎ Eስካለቀ ድረስ ከሚታሰብ 9% (ዘጠኝ በመቶ) ወለድ ጋር Aመልካች ለተጠሪ Eንዲከፍሉ ተወስኗል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።