No summary available.
መጋቢት 23 ቀን 2000 ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aብዱልቃድር መሐመድ ደስታ ገብሩ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- ወ/ት ዓለምነሽ ዋቅቶላ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡-
Aቶ ይልቃል ጌጤ Aልቀረቡም።
ካጀ I/ል ኃ/የ/የ/ኩባንያ Aልቀረበም።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በምEራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን Aመልካች በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ ንብረትነቱ የ2ኛ ተጠሪ የሆነውን መኪና 1ኛ ተጠሪ ሲያሽከረክር ጉዳት የደረሰብኝ ስለሆነ ካሣ Eንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
የከሳሽ ክስና ማስረጃ ለተከሣሾች Eንዲደርስና መልስ Eንዲሰጡበት ታዞ 2ኛ ተከሣሽ የAሁን 2ኛ ተጠሪ ባቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከሳሽና 2ኛ ተከሣሽ ባደረጉት ስምምነት ከሳሽ በደረሰባቸው የAካል ጉዳት ብር 3A ሺህ ከAዋሽ Iንሹራንስ ኩባንያ ለመቀበል በተስማሙት መሰረት ገንዘቡን ከኩባንያው የተቀበሉ ስለሆነ ክስ ያቀረቡት በEርቅ ባለቀ ጉዳይ ስለሆነ ፍ/ቤቱ Aቤቱታውን ውድቅ ላያደርገው ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤትም በዚህ ረገድ የቀረበውን መቃወሚያ መርምሮ ከሳሽና 2ኛ ተከሣሽ ጉዳዩን በEርቅ መጨረሳቸውን የቀረበው ማስረጃ ሰለሚያረጋግጥ Aቤቱታው ተቀባይነት የለውም በማለት በብይን ሳይቀበለው ቀርቷል። ከሣሽ በዚሁ ብይን ቅሬታ Aድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሰርዟል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ችሎት Aቤቱታውን መርምሮ Aመልካች ክስ ያቀረቡበት ጉዳይ በEርቅ ያለቀ ነው ተብሎ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተጠሪዎች ባሉበት ለሰበር ችሎት ቀርቦ መጣራት የሚገባው መሆኑን በማመኑ ተጠሪዎችን ጠርቷል። ሆኖም 1ኛ ተጠሪ በAድራሻው ባለመገኘቱ በጋዜጣ ተጠርቶ ስላልቀረበ መልስ የመስጠት መብቱ የታለፈ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ ግን ቀርቦ የበኩሉን የጽሁፉን የቃል ክርክር Aቅርቧል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን የሰበር Aቤቱታው ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ Aኳያ Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
የምEራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክሱ በብይን ተቀባይነት የለውም ወደሚል መደምደሚያ ለመድረስ የቻለው Aመልካች የካቲት 29 ቀን 1997 ዓ.ም. ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ባደረጉት ውል ለደረሰባቸው ቋሚ የAካል ጉዳት ካሳ የሚሆን ብር 3A ሺህ የተቀበሉ ስለሆነና ከዚህ በላይ 2ኛ ተጠሪንም ሆነ መድን ሰጭውን Aዋሽ Iንሹራንስ ኩባንያን ላለመጠየቅ ስምምነት ላይ የደረሱ በመሆኑ ክስ ያቀረቡበት ጉዳይ Aስቀድሞ በስምምነት Eልባት Aግኝቷል በማለት ነው።
ይሁንና የካቲት 29 ቀን 1997 ዓ.ም. ተደርጓል የተባለው ውል ይዘት ሲታይ Aዋሽ Iንሹራንስ ኩባንያ 2ኛ ተጠሪን በመወከል በካሣ Aከፋፈሉ ረገድ ከመልካች ጋር ውሉን Eንደተዋዋሉ መገንዘብ የሚቻል ከመሆኑም በላይ በስር ፍ/ቤትም ሆነ ለዚህ ችሎት ግራ ቀኙ ሲከራከሩ Aዋሽ Iንሹራንስ ኩባንያ 2ኛ ተጠሪን በመወከል ይህንኑ ውል ከAመልካች ጋር Eንደተዋዋለና በውሉ ላይ የተጠቀሰውንም ብር 3A ሺህ Iንሹራንስ ኩባንያው ለAመልካች መክፈሉ የተረጋገጠ ስለሆነ Iንሱራንስ ኩባንያው 2ኛ ተጠሪን በመወከል ከAመልካች ጋር ውሉን መዋዋል የሚችለው ለ2ኛ ተጠሪ በሰጠው የመድን ሽፋን ልክ Eንጂ ከዚያ በላይ ላሆን ስለማይችል የጉዳት Aድራሹ መኪና ባለንብረት 2ኛ ተጠሪ ከብር 3A ሺህ በላይ የተጠየቀውን የካሣ ክፍያ Aስመልክቶ የቀረበበት ክስ በEርቅ Aልቋል ላባል ስለማይችል የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩ በAጠቃላይ በEርቅ Aልቋል በማለት ክሱን ሳይቀበል መቅረቱ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህንኑ ስህተት ሳያርም መቅረቱ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተግኝቷል።
ው ሣ ኔ
348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
No topics extracted.
በAመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል ያለው ክርክር በEርቅ Aልቋል ለማለት ስለማይቻል የምEራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ክርክር መርምሮ የበኩሉን ውሣኔ Eንዲሰጥበት ጉዳዩ ተመልሶለታል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
353 354 4. መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።