No summary available.
ሚያዝያ 2 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሒሩት መለሰ መድኅን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- የAቶ ብሩ ቆርቾ ወራሽ ብርቅነሽ ብሩ ቀረቡ ተጠሪ፡- Aቶ ክፍል ሐብደታ ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
መዝገቡ የቀረበው Aመልካች የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጳጉሜ 4 ቀን 1995 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 10 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ይታረምልኝ በማለት 341 342 ስላመለከተ ነው። የክርክሩ መነሻ ተጠሪው Aመልካች በAዲስ Aበባ ከተማ በወረዳ 25 ቀበል 01 ቁጥሩ 292 የሆነውን ቤት ብር 4500 /Aራት ሺ Aምስት መቶ ብር/ የሸጡልኝ ስለሆነ ቤቱን Eንዲያስረክቡ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
Aመልካች በበኩላቸው ጉዳዩ ግንቦት 27 ቀን 1992 ዓ.ም ባደረጉት Eርቅና ግልግል ያለቀ ስለሆነ ቤቱን ያስረክቡኝ የሚለው ክስ ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱ Aመልካች ግንቦት 27 ቀን 1992 ዓ.ም በተስማሙት መሰረት የተቀበሉትን የቤቱን ዋጋ ብር 760 /ሰባት መቶ ስልሣ ብር/ Eና የገደብ መቀጫ ብር 2000 /ሁለት ሺ ብር/ ለተጠሪ Aሟልተው ያልከፈሉ ስለሆነ በቤት ሸያጭ ውሉ መሰረት ቤቱን Eንዲያስረክቡ በማለት ወስኗል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤትም በይግባኝ የሚያስቀርብ ነጥብ የለውም በማለት ዘግቶታል። Aመልካች ይኸ ውሣኔ ግንቦት 27 ቀን 1992 ዓ.ም ያደረግነውን ስምምነት ወደ ጐን በመተው የተወሰነ ስለሆነ መሰረታዊ የህግ ስህተት Aለበት በማለት የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪው በበኩል Aመልካቹ በEርቁ ውል መሰረት ያልፈፀመ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል።
ከሥር የክርክሩ Aመጣጥና በሰበር የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን Eኛም መዝገቡን መርምረነዋል። መዝገቡን Eንደመረመርነው Aመልካችና ተጠሪው ግንቦት 27 ቀን 1992 ዓ.ም የግልግል ውል ያደረጉ መሆኑ Aልተካደም። Aመልካችና ተጠሪ ያደረጉት የግልግል ስምምነት Aመልካች ከተጠሪው የተቀበለውን ብር 760 /ሰባት መቶ ስልሣ ብር/ Eና የቤት ሺያጭ ውሉ በመቅረቱ መቀጫ ብር 2000 /ሁለት ሺ ብር/ ሲከፍል ተጠሪው ደግሞ Aመልካች ቤቱን ያስረክበኝ የሚለውን ክስ ለመተው የተስማሙ መሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሣኔ ያሣያል።
ይህ በAመልካችና በተጠሪው መካከል የተደረገው የግልግል ስምምነት በመጀመሪያ የተደረገውን የቤት ሽያጭ ውል የማስቀረት ውጤት Eንደሚኖረው በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 3308 ንUስ Aንቀጽ 1 ይደነግጋል። ይህም በመሆኑ ተጠሪው Eና Aመልካች ግንቦት 27 ቀን 1992 ዓ.ም ያደረጉት የግልግል ስምምነት በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 3312 ድንጋጌዎች መሰረት Eንደመጨረሻ ፍርድ የሚቆጠር በመሆኑ ይኸው በግልግል ውላቸው ላይ የተስማሙበት ጉዳይ ማለትም Aመልካች በስምምነታቸው መሰረት ብር 2760 / ሁለት ሺ ሰባት መቶ ስልሣ ብር/ Eንዲከፍል ከሚጠይቁ በስተቀር ቤቱን ሸጦልኛልና ያስረክበኝ በማለት በግልግል ውል ቀሪ የሆነውን ጉዳይ የማንቀሣቀስ Eና የመጠየቅ መብት የላቸውም። ስለሆነም የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት Aመልካች በቤት ሽያጭ ውሉ መሰረት ቤቱን ለተጠሪው Eንዲያስረክቡ በማለት የሰጠው ውሣኔ ከላይ የተገለፁትን የሕግ ድንጋጌዎች ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጳግሜ 4 ቀን 1995 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
የፍድራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 10 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ ተሽሯል ይፃፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻሉ ብለናል።
ይህ ፍርድ ሚያዝያ 2 ቀን 2000 ዓ.ም በሙሉ ድምጽ ተሰጠ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ቤ/ኃ 343 344
No topics extracted.
የካቲት 25 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ወ/ሮ ወለላ ተሰማ - ጠበቃ ሽፈራው Aመኑ ተጠሪ፡- Eማሆይ በላይነሽ መለሰ - ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን ተጠሪ በAሁን Aመልካች ላይ ባቀረቡት Aቤቱታ ሟች ልጄ Eመቤት ለገሰ ከሟች Aባቷ Aቶ ለገሰ ቢነግድ በውርስ ማግኘት የሚገባትን ንብረት ተጠሪ ይዘው ስለሚገኙ በዓይነት Eንዲያካፍሉኝ የማያካፍሉኝ ከሆነም ንብረቶቹ ተሸጠው ድርሻ ገንዘቤን Eንዲሰጡኝ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ተጠሪም የAሁን Aመልካች ቀርበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና ሙሉ መልስ በመስጠት ተከራክረዋል። በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሱት ክርክርም የሟች Eመቤት ለገሰ Aውራሽ Aቶ ለገሰ ቢነግድ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ከ27 ዓመት በፊት በመሆኑ የቀረበው ክስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1AAA/1/ መሰረት በይርጋ የሚታገድ ነው። ሟች Eመቤት ለገሰ በሕይወት በነበረችበት ጊዜ የሟች Aባቷን የAቶ ለገሰ ቢነግድን የውርስ ንብረት ክፍፍልን በሚመለከት በስምምነት ለመካፈል ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት ሽማግልዎች ንብረት ለይተውና Aጣርተው ድርሻዋን ወስዳለች። በዚህ ዓይነት በግልግል ያለቀ ጉዳይ ይግባኝ ሳይኖረው የመጨረሻ ፍርድ ሆኖ Eንደሚቆጠር በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3312/1/ ላይ የተመለከተ በመሆኑ በሟች Eመቤት ለገሰና በተከሣሽ መካከል የነበረው የንብረት ክፍፍል በስምምነት የመጨረሻ ውሣኔ ያገኘና ያለቀለት ጉዳይ በመሆኑ የቀረበው ክስ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 244/2/ረ/ መሰረት ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል ነው።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት Aመልካች የወራሽነት መብታቸውን ያረጋገጡት ሰኔ 22 ቀን 1991 ዓ.ም. ሲሆን ልጃቸው Eመቤት ለገሰ የሞተችው ጥር 16 ቀን 1991 ዓ.ም. ነው። መብት በተረጋገጠበትና ክስ በቀረበበት ጊዜ መካከል 3 ዓመት ያልሞላ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1AAA/1/ መሰረት Aቤቱታው በይርጋ ቀሪ ሆኗል ተብሎ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በAግባቡ የቀረበ Aይደለም በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል።
ጉዳዩ Aስቀድሞ በግልግል Aልቋል ተብሎ የቀረበውን መቃወሚያ በተመለከተም መስከረም 3 ቀን 1984 ዓ.ም. ከተደሪገው የዘመድ ዳኞች ውሣኔ ጋር Aቶ ተሾመ ተሰማ የሟች Eመቤት ለገሰ ወኪል ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ስላልተያያዘ ውክልናው በAግባቡ ተሰጥቷል ለማለት Aይቻልም። በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1A8A/1/ መሰረት ከወራሾች Aንዱ ሳይኖር የቀረ ወይም በሚገባ ወኪል ያላዳረገ Eንደሆነ የንብረት ክፍፍሉን ዳኞች ካላፀደቁት 345 346 በቀር ፈራሽ Eንደሆነ የተመለከተ ስለሆነ ጉዳዩ Aስቀድሞ በግልግል Eልባት Aግኝቷል ተብሎ የቀረበውም መቃወሚያ ተቀባይነት የለውም ብሐል።
ፍ/ቤቱ በቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ብይን ከሰጠ በኋላ በሟች Aቶ ለገሰ ቢነግድ ወራሽና በባለቤታቸው መካከል ይገኛል የተባለን የጋራ ንብረት ለይተውና Aከፋፍለው ውጤቱን በሪፖርት መልክ ለፍ/ቤቱ Eንዲገልጹ በማለት ውርስ Aጣሪ ሾሞ Aጣሪውም የማጣራቱን ሥራ Aጠናቀው ሪፖርቱን ለፍ/ቤቱ Aቅርበው ፍ/ቤቱም የውርስ Aጣሪው ሪፖርት ለሕግም ሆነ ለሞራል ተቃራኒ ያልሆነ ስለሆነ ተቀባይነት Aለው በማለት ይህንኑ በመዝገቡ ላይ Aስፍሯል።
የሥር ተጠሪ ፍ/ቤቱ በሰጠው ብይንና ትEዛዝ ላይ ቅሬታ Aድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት Aቅርበው ፍ/ቤቱም በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የሥር ፍ/ቤትን ትEዛዝ Aጽንቷል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመወቃም ሲሆን ይህ የሰበር ችሎት Aቤቱታውን መርምሮ Aመልካች Aቤቱታው በይርጋ ቀሪ ሆኗል፤
ጉዳዩም Aስቀድሞ በግልግል Eልባት Aግኝቷል በማለት ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በበታች ፍ/ቤቶች ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተጣርቶ ላወሰን የሚገባው መሆኑን በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ ተጠሪ በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል ወይስ Aልሆነም ሲሆን Aልሆነም የሚባል ቢሆን ጉዳዩ Aስቀድሞ በግልግል Eልባት Aግኝቷል? Aላገኘም? የሚለው በመሆኑ በዚህ መሰረት Aቤቱታው ከሕጉ ጋር ተገናዝቦ ተመርምሯል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ የAሁን Aመልካች ክሱ በ3 ዓመት ይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ክርክር ያቀረቡት በፍ/ብሕ/ቁ. 1AAA/1/ የተመለከተውን በመጥቀስ ነው።
ችሎቱም በቅድሚያ የተመለከተው የፍ/ብሕ/ቁ. 1AAA/1/ ተፈፃሚነት ከዚህ ጉዳይ ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑን ነው።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1AAA/1/ ላይ የተቀመጠው የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚነት Aንድ ወራሽ የሆነ ሰው የውርስ ሀብትን በያዘ በልላ ወራሽ ላይ ክስ በሚያቀርብበት ጊዜ Eንደሆነ በመ/ በመጥቀስ ይህ ሰበር ችሎት የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በተያዘው ጉዳይ የAሁን Aመልካች የሟች Eመቤት ለገሰም ሆነ የAቶ ለገሰ ዲነግድ ወራሽ ባለመሆናቸውና ንብረቱንም የያዙት በወራሽነት ስላልሆነ በተጠቀሰው ሕግ ላይ የተቀመጠው የይርጋ ጊዜ ለጉዳዩ Aግባብነት Aይኖረውም።
ይህ ድንጋጌ ለጉዳዩ Aግባብነት የለውም በማለት ግን Aቤቱታው ጭራሽ የይርጋ ጊዜ የለውም ማለት ስላልሆነ የይርጋ ክርክሩ ከልሎች Aግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር መታየት የሚገባው ነው።
የሟች Eመቤት ለገሰ Aባት የነበሩት ሟች ለገሰ ዲነግድና የAሁን Aመልካች ባልና ሚስት Eንደነበሩ፣ በመካከላቸው የነበረውም ጋብቻ በAቶ ለገሰ ዲነግድ ሞት ምክንያት በነሐሴ ወር 1967 ዓ.ም. Eንዲፈርስ ሟች Eመቤት ለገሰም ግንቦት 25 ቀን 1969 ዓ.ም. የሟች Aባታቸው ወራሽ መሆናቸውን Aረጋግጠው ነገር ግን የንብረት ክፍፍል ሳይደረግ በጥር ወር 1991 ዓ.ም.
ሟች Eመቤት ለገሰ Eንደሞቱ ከመዝገቡ መረዳት ይቻላል።
ከባልና ከሚስት በAንዳቸው ሞት ምክንያት ጋብቻ በሚፈርስበት ጊዜ ከተጋቢዎቹ Eያንዳንዱ የግል ሀብቱ መሆኑን Aስረድቶ የEራሱን ድርሻ የመውሰድ መብት Eንዳለው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 684 ላይ ተመልክቷል። በEርግጥ ይህ ድንጋጌ ጥያቄው በምን ያህል ጊዜ መቅረብ Eንዳለበት ባይደነገግም በጋብቻ ጊዜ የተፈራ የግልም ሆነ የጋራ ንብረት ሳይከፋፈል ለረጅም ጊዜ ቆይቶ ጥያቄውን ከረጅም ጊዜ በኋላ ለማቅረብ የሕጉ ዓላማ ላሆን Aይችልም።
ግንኙነቱን የሚገዛው የቤተሰብ ሕጉ የይርጋ ድንጋጌን በዚህ ረገድ ካላካተተ ወደ ልሎች ድንጋጌዎች መሄድ ግድ ስለሚል በዚሁ መሰረትም ሲታይ ግድታዎች ከውል የተገኙ ባይሆንም የጠቅላላ የውል ሕግ ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት Eንዳላቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1677/1/ ላይ የተመለከተ ሲሆን የውል ሕግ ደግሞ ዋናው የይርጋ ደንብ በቁጥር 1845 ላይ የተመለከተው የ1A ዓመት የይርጋ ጊዜ ነው።
በተያዘው ጉዳይ Aመልካች በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ መቃወሚያ ያቀረቡት የሟች Eመቤት ለገሰ Aባት Aቶ ለገሰ ዲነግድ ከሞቱበት ከ1967 ዓ.ም. ጀምሮ ያለውን ጊዜ በመቁጠር ነው። ነገር ግን ተጠሪ ክስ ያቀረቡት በAቶ ለገሰ ዲነግድ Eግር ተተክተው ሳይሆን በሟች ልጃቸው በEመቤት ለገሰ Eግር በመተካት Eንደመሆኑ መጠን ሟች Eመቤት ለገሰ ደግሞ የሞቱት ጥር 16 ቀን 1991 ዓ.ም. ሆኖ የልጄ ድርሻ ንብረት ይገባኛል በማለት ክስ ያቀረቡት ለጉዳዩ Aግባብነት ባለው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1845 ላይ የተመለከተው የ1A ዓመት የይርጋ ጊዜ ከማለፉ በፊት በ1994 ዓ.ም. ስለሆነ ክሱ በይርጋ ቀሪ Aልሆነም ተብሎ በበታች ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ ከውጤት Aኳያ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ Aልተገኘም።
ጉዳዩ በይርጋ ቀሪ Aልሆነም ከተባለም ቀጥሎ መታየት የሚገባው ጭብጥ ክርክሩ Aስቀድሞ በግልግል Eልባት Aግኝቷል ወይስ Aላገኘም የሚለው ጭብጥ ነው።
በፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ ሟች Eመቤት ለገሰ በሕይወት Eያሉ ከAመልካች ጋር በዘመድ ዳኞች Aማካይነት መስከረም 3 ቀን 1984 ዓ.ም. የንብረት ክፍፍል Aድርገው ድርሻቸውን የወሰዱ ስለሆነ በግልግል ባለቀ ጉዳይ ላይ የቀረበው ክስ በAግባቡ Aይደለም በማለት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.
244/2/ረ/ ላይ የተመለከተውን በመጥቀስ Aመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ Aቅርበዋል።
የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት መቃወሚያውን ሳይቀበለው የቀረው በAስረጂነት ከቀረበው የሽምግልና ዳኞች ውሣኔ መገንዘብ የሚቻለው ክፍፍሉ የተደረገው የሟች ወኪል ናቸው በተባሉት በAቶ ተሾመ ተሰማ Aማካይነት Eንደሆነ ሲሆን ነገር ግን Aቶ ተሾመ ተሰማ የሟች ወኪል ናቸው ተብሎ በውሣኔው ላይ ከመጠቀሱ በስተቀር ከውሣኔው ጋር የውክልና ሥልጣኑ Aልተያያዘም። በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1A8A/1/ መሰረት ከወራሾች Aንዱ ሳይኖር የቀረ ወይም በሚገባ ወኪል ያላደረገ Eንደሆነ የንብረት ክፍያውን ዳኞች ካላፀደቁት በስተቀር ፊራሽ Eንደሆነ የተመለከተ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ የተደረገውም የንብረት ክፍፍል ፍ/ቤት ቀርቦ ያልፀደቀ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም በማለት ነው።
የውርስ ሀብት ክፍፍልን Aስመልክቶ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1A79 Eና ተከታዮቹ ላይ የተመለከተው በዚህም ጉዳይ ላይ ተፈፃሚነት Eንዳለው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 689/2/ የተመለከተ ቢሆንም በቁጥር 1A8A/1/ ድንጋጌ መሰረት ከወራሾች Aንዱ ባልተገኘበት ወይም በሚገባ ባልተወከለበት የተደረገን የንብረት ክፍፍል ዳኞች ካላፀደቁት በስተቀር ፈራሽ ነው ላባል የሚችለው በዚሁ Eንቀጽ በንUስ Aንቀጽ /2/ ሥር Eንደተመለከተው በልለበት ክፍያው የተፈጸመበት ወራሽ በሚያቀርበው Aቤቱታ መነሻነት Eንደሆነ የተመለከተ ከመሆኑም በላይ የዚህ ዓይነቱንም ጥያቄ ወራሹ ማቅረብ የሚችለው የንብረት ክፍፍል በልለበት መደረጉን ባወቀ በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ Eንደሆነና ነገር ግን ሟች ከሞተ 10 ዓመት ያለፈለው ከሆነ በማናቸውም ምክንያት ጥያቄውን ማቅረብ Eንደማይቻል በዚሁ Aንቀጽ በንUስ Aንቀጽ /3/ ሥር ተመልክቷል። በተያዘው ጉዳይ የተጠሪ Aውራሽ መስከረም 3 ቀን ተደርጓል የተባለው የንብረት ክፍፍል በልለሁበት ስለሆነ ላፈርስ ይገባል በማለት ከላይ የተጠቀሰው ድንጋጌ መሰረት Aቤቱታ Aቅርበው ክፍፍሉ ፈራሽ ነው ተብሎ ያልተወሰነ ከመሆኑም በላይ ተጠሪም ክስ የመሰረቱት ከሟች ልጄ በውርስ የተላለፈልኝ ንብረት ይገባኛል በማለት Eንጂ ክፍፍሉ Eንዲፈርስ ዳኝነት ያልጠየቁ በመሆኑ በዚህ ሁኔታ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ክፍፍሉ ፈራሽ ነው በማለት የሰጠው ብይን Eንደዚሁም የፍ/ከ/ፍ/ቤት ይህንኑ ብይን በማጽናት የሰጠው ፍርድ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸው ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
በAመልካችና በተጠሪ Aውራሽ መካከል በግልግል ዳኞች Aማካይነት መስከረም 3 ቀን 1984 ዓ.ም. የንብረት ክፍፍል መደረጉ የተረጋገጠ ስለሆነ ተጠሪ ድርሻ ንብረቴ ይገባኛል በማለት ያቀረቡት ክስ ከፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 244/2/ረ/ መሰረት ተቀባይነት የለውም ተብሎ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።