No summary available.
ታህሣሥ 15 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- Eነ Aቶ ተክል ደግፍ /2 ሰዎች/ የ2ኛ Aመልካች ወራሽ ቀረበ።
ተጠሪዎች፡- Eነ Aቶ በፍቃዱ ኃይል /2 ሰዎች/ - ጠ/ዳንኤል ቀረበ።
ለሰበር Aቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ የጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ነው። የAሁን ተጠሪዎች በሥር ፍ/ቤት የፍርድ ባለመብቶች ሲሆኑ 1ኛ Aመልካች ደግሞ የፍርድ ባለEዳ ነበሩ። በሥር ፍ/ቤት በተያዘው Aፈፃፀም የፍርድ ባለEደ የሆኑት የAሁኑ 1ኛ Aመልካች ቤት የፍርድ ባለመብቶቹ Eንዲረከቡት የተሰጠውን ትEዛዝ የAሁኑ 2ኛ Aመልካች ተቃውመው ቀርበዋል። 2ኛ Aመልካች ቤቱን ከውሣኔ በኋላ የገዙት መሆኑን ገልፀው Aፈፃፀሙ Eንዲቋረጥ ጠይቀዋል። ነገር ግን ፍ/ቤቱ 2ኛ Aመልካች ቤቱን የገዙት ከውሣኔ በኋላ ከመሆኑም ልላ የሽያጩን ውል ያደረጉት ከፍ/ባለEዳው ጋር Eንጂ ከፍርድ ባለመብቶች ጋር ባለመሆኑ ጥያቄያቸው ተቀባይነት የለውም በማለት Aፈፃፀሙ Eንዲቀጥል ትEዛዝ ሰጥቷል።
በዚህ ትEዛዝ ላይ Aመልካቾች ለፍ/ከፍ/ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ ያቀረቡ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን ባለመቀበል ሰርዞታል።
የAሁኑ የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ነው።
Aመልካቾች በቅሬታቸው ላይ ነሐሴ 13 ቀን 1996 ዓ.ም በተደረገ የEርቅ ስምምነት፣ 2ኛ Aመልካች በ1ኛ Aመልካች ስም ብር 30‚000 (ሰላሳ ሺህ) ለ1ኛ ተጠሪ በራሣቸውና በ2ኛዋ ተጠሪ ስም ፈርመው ገንዘብ ተቀብለው ታርቀው በዚሁ Eርቅ ስምምነት መሰረት Aፈፃፀሙ Eንዲቋረጥ ለፍ/ቤቱ የቀረበውን ጥያቄ ፍ/ቤቱ ያለምንም ምክንያት ውድቅ በማድረግ Aፈፃፀሙ Eንዲቀጥል ማድረጉ ስህተት ነው በማለት Aቤቱታ Aቅርበዋል።
ይህ ችሎትም ጉዳዩ በEርቅ ማለቁ ለፍ/ቤት ቀርቦ Eያለ Aፈፃፀሙ Eንዲቀጥል መደረጉ በAግባቡ መሆን Aለመሆኑን ለመመርመር Aቤቱታው ለሰበር ችሎት ቀርቦ Eንዲታይ Aድርጓል። በዚህም መሰረት ተጠሪዎች ቀርበው መልሣቸውን በጽሁፍ Aቅርበዋል። በመልሳቸውም 1ኛ ተጠሪ ስምምነቱን የፈረሙት በሽማግልዎች ከፍተኛ ተጽኖ Eና ጫና Eንጂ በነፃ ፈቃዳቸው ካለመሆኑም በላይ ከ2ኛ ተጠሪ የተሰጣቸው ውክልና ሣይኖር በመሆኑ በፍርዱ መሰረት Eንዲፈጽሙ መደረጉ ስህተት የለውም ብለዋል።
ችሎቱም መዝገቡን Eንደሚከተለው መርምሯል።
ከክርክሩ ሂደት በ1ኛ Aመልካችና በተጠሪዎች መካከል በነበረው ክርክር ተጠሪዎች የ1ኛ Aመልካችን ቤት Eንዲረከቡ ተወስኖላቸው Eንደነበር፣ ከውሣኔው በኋላ 1ኛ Aመልካች ይህንኑ ቤት ለ2ኛ Aመልካች መሸጣቸውን፣ ተጠሪዎች ይህንን ቤት ለመረከብ በAፈፃፀም ላይ Eያሉ ደግሞ Aመልካቾችና ተጠሪዎች ነሐሴ 13 ቀን 1996 በተደረገ የEርቅ ስምምነት ጉዳያቸውን ለመጨረስ መስማማታቸውን ተረድተናል።
ተከራካሪ ወገኖች በAንድ ወይም በልላ ምክንያት በፍ/ቤት የጀመሩትን ክርክር በፍርድ ሂደት ከመቋጨት ይልቅ በEርቅ ስምምነት ለመጨረስ ላመርጡ ይችላሉ። ክርክሩ በማናቸውም ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም በፍ/ቤት ወይም ከፍ/ቤት ውጪ በEርቅ ወይም በግልግል ጉዳያቸውን ጨርሰው በፍ/ቤት የጀመሩትን ክርክር ለማቋረጥ Eንደሚችሉም ከፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 274/1/ Eና 275/1/ መገንዘብ ይቻላል። ፍ/ቤቱም ይህን የEርቅ ስምምነት በጽሁፍ ሲቀርብለት Eርቁ ለሕግ ወይም ለሞራል የማይቃረን መሆኑን Eስካረጋገጠ ድረስ ስምምነቱን ተቀብሎ በፍርድ ቤት የተያዘውን ጉዳይ ማቋረጥ Eንደሚገባው ከፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 277/1/ ያመለክታል።
በተያዘው ጉዳይ 1ኛ ተጠሪ በራሣቸውና በ2ኛ ተጠሪ ባለቤታቸው ስም ሆነው የEርቁን ስምምነት መፈረማቸውን Aልካዱም። የሚያነሱት ክርክር ስምምነቱን በተጽኖ ነው የፈረምኩት ከ2ኛ ተጠሪም የተሰጠኝ የውክልና ስልጣን Aልነበረም የሚል ነው።
1ኛ ተጠሪ ውሉን ከነፃ ፍላጎታቸው ውጪ በሆነ ሁኔታ Eንደፈረሙ ይግለፁ Eንጂ በዚህ ሁኔታ ለመፈረማቸው ያስረዱት ነገር ካለመኖሩም ልላ ውሉ Eንዲሰረዝላቸው Aላደረጉም። በመሆኑም በዚህም ምክንያት በስምምነቱ መሰረት ላፈፀም Aይገባም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም።
በልላ በኩል ከAመልካቾች Aቤቱታ 1ኛ Aመልካች ከተጠሪዎች በወሰዱት ብድር ምክንያት Eዳው ካልተከፈለ ለEዳው በመያዣ የተያዘው ቤት ተጠሪዎች Eንዲረከቡት መወሰኑን ተገንዝበናል። ነገር ግን ተጠሪዎች ቤቱን በመያዣ የያዙበት Eዳ ተከፍሐቸው ቤቱን ለመልቀቅ ተስማምተዋል። ነሐሴ 13 ቀን 1996 ዓ.ም. ግራ ቀኙ ካደረጉት ስምምነትም ተጠሪዎች ይህ ስምምነት ከመደረጉ በፊት የወሰዱት ገንዘብ ስላነሣቸው ተጨማሪ ገንዘብ Eንዲሰጣቸው ያቀረቡትን ጥያቄ Aመልካቾች ተስማምተውበት ተጨማሪ ገንዘብ ለተጠሪዎች መከፈሉን ተገንዝበናል። በመሆኑም ተጠሪዎች ቤቱን በመያዣ የያዙበት Eዳ ከተከፈላቸው በኋላ በድጋሚ ቤቱን ለመረከብ Aፈፃፀሙ ላቀጥል ይገባል በማለት የቀረቡት ክርክር ከቅን ልቦና ውጪ ከመሆኑም በላይ ለAንድ Eዳ ሁለት ጊዜ ክፍያ Eንዲፈፀምላቸውና Aላግባብ Eንዲበለጽጉ የሚያደርግ ነው።
ፍ/ቤቱም ቢሆን ግራ ቀኙ ያቀረቡት ለEርቅ ስምምነት ለሕግ ወይም ለሞራል ተቃራኒ መሆን Aለመሆኑን መርምሮ ካልሆነ Eርቁን በመመዝገብ Aፈፃፀሙን ማቋረጥ ሲገባው በውሣኔው መሰረት ቤቱን ተጠራዎች Eንዲረከቡ ትEዛዝ መስጠቱ የEርቅ ስምምነት ጉዳይን ስለመጨረስ የሚደነግጉትን የሥነ ስርዓት ድንጋጌዎች ያላገናዘበ ሆኖ Aግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፍ/መ/ደረጃ በመ/ቁ A5393 ኀዳር 7 ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ Eና የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 43A87 በታህሳሥ 11 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጡት ትEዛዞች ተሽረዋል።
ግራ ቀኙ ነሐሴ 13 ቀን 1996 ዓ.ም. ያደረጉት ስምምነት ሕግና ሞራልን የማይቃረን በመሆኑ በEርቁ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 277 የተመዘገበ በመሆኑ የተጀመረው Aፈፃፀም ተቋርጦ በEርቁ መሰረት Eንዲፈጸም ታዟል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ
No topics extracted.