No summary available.
በሚያዝያ 28 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ታፈሰ ይርጋ መድኀን ኪሮስ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- Eነ Aቶ ዋለልኝ ንጉሱ - ወራሽ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- Eነ Aቶ Aለሙ ወንድሙ - ጠበቃ Aቢይ ወርቁ - ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በAዲስ Aበባ ከተማ Aስተዳደር የከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን ተጠሪዎች በAመልካቾች ላይ ባቀረቡት ክስ በወረዳ 7 ቀበል 32 ቁጥር A74 የሆነውን ቤት ከAዋጅ 47/67 በፊት የሰራነው ሲሆን በAዋጁም Aልተወረሰም። በዚሁ ቤት በስማችን የንግድ ፈቃድ Aውጥተን በኃይለስላሴ ጊዜ ተከሣሾችን በግል ድርጅታችን Eንዲሰሩ 333 334 Aስጠግተናቸው ነገር ግን Eንዲለቁ ተጠይቀው ፈቃደኛ ስላልሆኑ Eንዲለቁ ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
ተከሳሾችም ቀርበው ክስ የቀረበበት ቤት በAዋጁ ተወርሶ የAከራይ ተከራይ ግንኙነታችን ተቋርጧል። ኪራይም ለቤቱ ባለቤት ለቀበልው Aስተዳደር Eየከፈልን ስለሆነ ከሣሾች ቤቱ ይለቀቅልን በማለት ያቀረቡት ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትን የከተማ ነክ የመ/ደ/ፍ/ቤት ክርክር የቀረበበትን ቤት ማኀደር Aስቀርቦ በመመልከት ቤቱ የተወረሰ ስለመሆኑ Aልተረጋገጠም በማለት ተከሳሾች ይህንኑ ክስ የቀረበበትን ቤት ላያስረክቡ ይገባል ሲል ውሣኔ ሰጥቷል።
ከዚህ በኋላም ጉዳዩ በይግባኝና በሰበር ለከተማው ፍ/ቤት ቀርቦ ቤቱ ላመለስ ይገባል ተብሎ በበታች ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ በAብላጫ ድምጽ ጸንቷል።
የሰበር Aቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ችሎትም በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ይህ ችሎት በቅድሚያ የተመለከተው የክርክሩን Aመራር በተመለከተ ነው።
የሥር ከሳሾች የAሁን ተጠሪዎች ዳኝነት የጠየቁት የግል የሆነ ቤታችን በሥር ተከሳሾች በAሁን Aመልካቾች ያለAግባብ የተያዘብን ስለሆነ Eንዲመለስልን ይወሰንልን በማለት ነው።
ተከሳሾችም በበኩላቸው ቤቱ በመንግሥት በመወረሱ ምክንያት ከከሣሾች ጋር የነበራቸው የኪራይ ውል ተቋርጦ ከቤቱ ባለቤት ከቀበልው Aስተዳደር ጋር የኪራይ ውል በመዋዋል ኪራይ Eንደሚከፍሉ ገልፀው ክሱ ላሰረዝ ይገባዋል ብለዋል።
ከሳሾች በAንድ በኩል የቤቱ ባለቤት ነን የሚሉ ከሆነና በልላ በኩልም ቤቱ በAዋጅ በመንግሥት ተወርሷል ከተባለ ክርክሩ ባለቤትነትን የመፋለም /Petitory action/ ስለሚሆን ቤቱን በውርስ ይዞ በማስተዳደር ላይ ይገኛል የተባለው የቀበልው Aስተዳደር ለክርክሩ Eጅግ Aስፈላጊ ወገን /Indispensable Party/ Eንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። ምክንያቱም ለክርክሩ Eጅግ Aስፈላጊ የሆነው ወገን በልለበት የሚሰጥ ውሣኔ መብቱን፣ ጥቅሙን ላነካ Eንደሚችል ስለሚታመን ነው። ይህ ለክርክሩ Eጅግ Aስፈላጊ የሆነው ወገን በከሳሾች በኩል በተከሳሽነት Eንዲጣመር ባይደረግም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 4A/2/ ላይ ለፍርድ ቤቱ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ወደ ክርክሩ Eንዲገባ ማድረግ ነበረበት።
ስለሆነም በየደረጃው ባሉ የከተማ ነክ ፍ/ቤቶች ለጉዳዩ Eልባት የተሰጠው ለክርክሩ Eጅግ Aስፈላጊ የሆነው የቀበልው Aስተዳደር የክርክሩ ተካፋይ ባልሆነበት ሁኔታ ስለሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
ይፃፍ።
የሚመለከተው የቀበል Aስተዳደር ለጉዳዩ Eጅግ Aስፈላጊ ወገን /indispensable party/ ስለሆነ የከተማ ነክ የመ/ደ/ፍ/ቤት ይህንኑ ወገን ወደ ክርክሩ በማስገባት Aከራክሮ Eንዲወስን ጉዳዩ ተመልሶለታል።
ግራ ቀኙ ወጭና ክሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.